Tuesday, December 25, 2012

ጌታ ሆይ ቅደመኝ



በአንድ በኩል ስሰፋ ሌላው ሲያፈስብኝ
ጥሬውን ስቆላ ብስሉ ሲያርብኝ
አንዱን አለፍኩት ስል ሌላው ሲያናቅፈኝ
ቀን በቁሜ ስቃዥ ሌሊት ሲያባንነኝ
አንድ ጊዜ ሲያስቀኝ ደሞም ሲያስልቅሰኝ
      ቀኜ ሲበረታ ግራዬ ሲደክም
      ራስ ፍልጠት ሲይዘኝ ጨጓራ ሲያገግም
      ምን ይሆን መፍትሔው ለዚህ ከንቱ አለም
      ጌታ ሆይ ቅደመኝ ሸክሙን አልቻልሁም

Saturday, December 22, 2012

ተረት ተረት



ተረት በሀገራችን ትልቅ ቦታ አለው፡፡ የማህበረሰቡን ብስለት፣ ኑሮ ፣መስተጋብርና አመለካክት የማሳየት አቅም አለው፡፡ እስኪ ከዚህ በታች ስለ አንድ ብልጥ ልጅ የሚተርክ የአፋር ተረት ላውራችሁ፡፡

ተረት ተረት ---የመሰረት/የላም በረት

በአንድ ወቅት በጣም ብልጥ የሆነ 15 ዓመት እድሜ ያለው የአፋር ተወላጅ ልጅ ነበር፡፡ ሆኖም ይህ ልጅ በቤቱ ውስጥ ይደረግ የነበረውን መጥፎ ነገር ያውቅ ስለነበረ ሁልጊዜ ያዝንና ይበሳጭ ነበር፡፡ አባቱ ከእናቱ ገረዶች ከአንድዋ ጋር በድብቅ ይባልግ ነበር፡፡

Friday, December 21, 2012

አንችን ሞት አይንካሽ



 
የቱን  ተናግሬ የትኛውን ልተው
ምን  ቋንቋ ልጠቀም በምን ቃላት ላውራው
ምን ምሳሌ ልፍጠር በምን ልመስለው
እንዴትስ ልዘርዝር ከየት ልጀምረው
እፁብ እፁብ ብዬ ዝም ልበል በአንክሮ
ዘላለም ይኖራል በውስጤ ተቀብሮ
    ለዚህ ያደረሰኝ የናትነት ፍቅርሽ
    ዛሬም ያፅናናኛል ብለይም ከፊትሽ
    የአንችን ክፉ አልስማ እናቴ እባክሽ
    በእኔ ዕድሜ ኑሪ አንችን ሞት አይንካሽ 

For my beloved mother,ኅዳር 2003

Sunday, November 25, 2012

አንድ ምስል





በህልም ዓለም ጉዞ ታች ላይ እያልሁኝ
የቀኑ እሩጫየ እንቅልፍ አሳጥቶኝ
አንድ ጊዜ ሲያከብረኝ አንዴ ሲያደኸየኝ
በድንገት ስከብር ከእነቅልፌ ነቃሁኝ፤
     ደግሜ እንደገና ከአልጋየ ጋደም ስል
     ከማንቀላፋቴ ታየኝ አንድ ምስል፤