Wednesday, December 14, 2016

ለካስ እድሜ ማለት...

እንደ ኤሊ ጉዞ~እንዲህ እንደዋዛ
ሴኮንድ ተደማምሮ~ደቂቃ እየበዛ
የሰዓታት ውህደት~በቀናት ሲሰላ
ሳምንትና ወራት~አመት እየሞላ
ሰው የሚባል ፍጡር~ይኖራል በመላ
ሲደምር ሲቀንስ~ ቁጥር ሲጣላ


በትናንት ትውስታ~ከልጅነት ማዶ
ዛሬ ገፄን ሳየው~ እርጅና ተዋዶ
"ለካስ እድሜ ማለት~ጅረት ነው ፏፏቴ
ሽው ብሎ የሚሮጥ~አንዱ በአንዱ ኮቴ"
(Thank You My God)

1 comment:

  1. ለካስ እድሜ ማለት~ጅረት ነው ፏፏቴ
    ሽው ብሎ የሚሮጥ~አንዱ በአንዱ ኮቴ

    ReplyDelete