Monday, July 24, 2017

ይድረስ ለ 'ጃንሆይ'

እንዴት አሉ ጃንሆይ?
ሰላምታ አቅርበናል~ወደ አሉበት ሰማይ
ዓለም ለሚያከብረው~ ክቡር ልደትዎ
ኬኩ ባይቀምሱም~እንኳ አደረሰዎ
እንኳን የእኛ ሆኑ!

………እንኳን ተወለዱ!
ይህን ጭቁን ህዝብ~እንኳ እንደ ላም ነዱ!

Wednesday, July 19, 2017

የ ሲኦል ነፍሳት: ክፍል ፫

ማሪያና ትንሽ ሞቅ ብሏታል፡፡ ከለበሰችው ታኮ ጫማ ጋር ተዳምሮ ‹‹ደርደርደርደር›› ትላለች፡፡ ጠጋ ብዬ እጄ ጨበጥኋት፡፡ እጇ ያቃጥላል፡፡ አስፓልቱን ዳር ይዘን ባጃጅ መጠበቅ ጀመርን፡፡
ዝምታችንን ለመስበርይቅርታ ቅድም አስቀየምሁሽ አይደል አልኳት፡፡
‹‹ችግር የለም አንተ አልፈርድም፣ አልፏል እርሳው›› አለችኝ….ዝቅ ብላ መሬት መሬት እያየች፡፡
ማሪያና ወደ የት እንደምንሄድ እንኳን አልጠየቀችኝም፡፡ የምወስዳት ወደ ገነት እንዳልሆነ ልቧ ቢያውቅም፣ ሲኦል ወደ ባሰ ገሃነም ይሆን ብላ እንኳ አትጠይቅም….‹‹የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም›› ብላ ይሆን? አላውም ምን እያሰበች እንደሆነ ማወቅ ይከብዳል፡፡