Monday, March 5, 2018

የተዘነጋው ሌላኛው የኢትዮጵያውያን የድል በዓል (የካቲት 26)

Colonel Mengistu H/Mariam                     Victory Momentum 
የኢትዮ-ሶማሊ ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው የኦጋዴን ጦርነት ሶማሌ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ጋር ሀምሌ 1968 . ተጀምሮ የካቲት 1970 . የተጠናቀቀ ጦርነት ነው፡፡ መጀመሪያ በሶቪዬት ህብረት ቀጥሎም ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ኢትዮጵያን የወረረው የሰይድ ባሬ (ዚያድባሬ) ጦር ‹‹የእናት ሀገር ጥሪ›› እያለ ከመላው የኢትዮጵያ ምድር በተሰባበሰበ ጀግናው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ድባቅ ተመታ፡፡ 
 Siad Barre
የካቲት 26 1970 . የኢትዮጵያ ሰራዊት በመልሶ ማጥቃት ካራማራ ተራራ ላይ ከባድ ውጊያ አካሄደ፡፡ ከዚያም ጅግጅጋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ፡፡ አራት ቀናት በኋላ ሁኔታው ያስፈራው ሰይድ ባሬ የሶማሊያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ምድር ሙሉ በሙሉ ለቆ እዲወጣ ጥሪ አስተላለፈ፡፡ ኢትዮጵያውያንም በድል ተመለሱ፡፡ በጦርነቱ ኩባ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር ድጋፍ አድርጋለች፡፡ 16,000 በላይ የኩባ ወታደሮችም የታሪኩ ተካፋይ ናቸው፡፡ ታላቋ ሶማሊያም ፈራረሰች፡፡ የዚያድባሬ የመጨረሻ ቃልም ‹‹ Nothing is permanent on this world’’ በሚል ተቋጨ፡፡

Friday, March 2, 2018

¶አድዋ¶


አድዋ ታሪክ ብቻ አይደለም
አድዋ ትዝታ ብቻ አይደለም፡፡
አድዋ ህልም ነው፣ በከንቱ ቅዠት ያልተረታ
አድዋ ቅኔ ነው፣ በጥቁር ጀግኖች የተፈታ፤
አድዋ መዶሻ ነው፣ የዘር አጥርን የሰበረ
አድዋ ፍትህ ነው፣ ሰውን በእኩል ያስከበረ፤
አድዋ እምነት ነው፣ ታምራት የነገሰ 
አድዋ ምናብ ነው፣ በአጥር ብዛት ያልፈረሰ፤
አድዋ ብርሃን ነው፣ ለጭቁኖች የበራ
አድዋ ተስፋ ነው፣ ትውልድን የሚመራ፤
አድዋ መንፈስ ነው፣ሰውመሆንን ያስወደደ
አድዋ ሀረግ ነው፣ አንድ ኢትዮጵያን ያዋሃደ፤
አድዋ ……….አድዋ (122x)…….ዋዋዋዋ!
=========================
Zelalem T 
123ኛው በዓል በሰላምና በአንድነት ያድርሰን!
=========================