Friday, November 16, 2018

የአፄ ቴዎድሮስ የመጨረሻ ቃል


ባለቤታቸው / ጥሩወርቅ ልባቸው ፈራ፡፡ ንጉሱ ለእንግሊዞች እጁን ከሚሰጥ፣ እራሱን ማጥፋት እንደሚመርጥ ውስጣቸው ያውቃል፡፡ ከዚያም ወደ መቅደላ አምባ መልዕክት ላኩ፡፡ ምን ብለው? ‹‹ እባክህ በልዑል አለማየሁ ይሁንብህ፣ በራስህ ምንም እንዳታደርግ›› ብለው፡፡ የአለማየሁ ነገር እንደማይሆንላቸው ያውቃሉ፡፡ ቴዲ ግን በአለማየሁ እንኳን ጨከነ፡፡ ህልመኛው ተስፋ ቆረጠ፡፡ ዞር ሲል ሊያቆመው የሞከረውን ምሰሶ የሚገፉ፣ ግርግዳውን ለማፍረስ የሚለፉ ሰዎችን አዬ፣ አስተዋለ፡፡ ከሰው መሃል ሁኖ ብቻውን ሆነ፡፡
‹‹ተስፋ ባጣ ምድረ በዳ
ያንድ እምነት ይሆናል ዕዳ
››……እንዳለው ሎሬት ፀጋዬ /መድህን ከገብርዬ ሞት በኋላ ከቅርቡ ያለው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ ሽጉጥ፡፡

የሊቀ ስዩማን መዝገቡ ጉዳይ እና የአዊ ሀገረ ስብከት ውዝግብ-ክፍል ሁለት



በሐይማኖትና በዘር ጉዳይ ከእንግዲህ አልፅፍም ብዬ ለራሴ ቃል ብገባም፣ የጉዳዩ አሳሳቢነት ህሊናዬን ሰላም ነሳኝ መሞነጫጨር ጀመርሁ፡፡ ትናንት ማታ 8 ሰዓት ላይ ይህን ጉዳይ በገፄ ከለጠፍሁ በኋላ ብዙ መልክቶች በተለያዬ መልኩ ወደእኔ ደርሰዋል፡፡ ብዙዎቹ ቅንነት የሞላባቸው ናቸው፡፡ ሊቁን ለማገዝ የሚጠይቁም አሉ (መጨረሻ ላይ ሂሳብ ቁጥራቸውን አስቀምጣለሁ፣ ዘላቂ መፍትሔ ባይሆንም)፡፡
ወደ ጉዳዩ ከማምራታችን በፊት፣ ሁላችንም ከአሸናፊው እውነት ጋር እንሆን ዘንድ፣ ዛሬ ጥዋት አንድ ወዳጄ በአስተያይት ማስፈንጠሪያው ላይ ያስቀመጣትን የማህተመ ጋንዲን ጥቅስ አይተን እንለፍ፡
በምድር ላይ ብቻህን ብትቀር እንኳን ከግፈኞች ጋር አትተባበር። ዓለም ዓይኗን ብታቀላብህ አንተ ግን ፈገግታህን ለግሳት፡፡ አትፍራ፡፡ በልብህ ውስጥ ያለውን የእውነት ድምፅ ብቻ ታመን፡፡ ድምጽ እንዲህ ይላል:- ባለንጀራህ፣ ሚስትህ፣ ዘመዶችህ፣ ጳጳስህ ሁሉም ቢተውህ ለምትኖርለትና ልትሞት ለተዘጋጀህበት እውነት ብቻ መስክር፡፡ የመኖር ትርጉሙ ይህ ነውና›› ማኅተመ ጋንዲ

Sunday, November 4, 2018

ባቀኑት ሀገር ስደተኛ የሆኑት ሊቅ እና የአዊ ሀገረ ስብከት ውዝግብ

                              (የአቡነ ቶማስ የመጀመሪያው በትር ያረፈባቸው ሊቀ ስዩማን መዝገቡ እስከዚያ)
‹‹ አንተን ምዕመኑ ስሚያምንህ መድረክ ላይ ወጠህ ማኅበረ ቅዱሳንን እያወገዝህ ስበክ››-----ብፁዕ አቡነ ቶማስ ለሊቁ
‹‹ እርስዎ ምን አሰቡ ኤኔታ››------እኔ
‹‹ላድርገው ብል እንኳን ህሊናዬ እንዴት ይቀበለዋል፡፡ በአይኔ ያየሁትን የማኅበሩን ስራ እንዴት እክዳለሁ፣ እንዴት እዋሻለሁ››----ሊቀ ስዩማን መዝገቡ
‹‹ታዲያ በምን መልኩ መቀጠል አሰቡ››----እኔ
‹‹ እስከሚያባርሩኝ ድረስ እሰራለሁ፣ ከተባረርሁም ፍትህን ከእግዚአብሔር እጠብቃለሁ››--ሊቀ ስዩማን መዝገቡ
-----------------------------------------------------------------------------------------------------
ማን ነበር ‹‹ብሸሸው ብሸሸው አለቀቀኝም›› ያለው፡፡ በአዊ ሀገረ ስብከት፣ ከሀገረስብከት አስተዳደርና ከሃይማኖት አስተምሮ ጋር ተያይዞ ስለተነሳው ውዝግብ ከማንሳቴ በፊት፣ የነገሩን ስረ መሰረት ለመረዳትም ያግዝ ዘንድ የኤንታ መዝገቡን ጉዳይ ላስቀድም፡፡ ከላይ መግቢያ ላይ የጠቀስሁት ‹‹ቃለ ምልልስ›› ከሊቁ ጋር ያደረግነው ልክ የዛሬ ዓመት (2010 ዓ.ም) ለጥቅምት ሲኖዶስ ወደ አዲስ አበባ መጠው ከእኔ ዘንድ ባረፉበት ወቅት ነበር፡፡ የኤኔታን እና የእኔን ግንኙነት ብዙ ሰው ያውቀዋል፡፡ ከላይ ያነሳሁትም አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ወደ ጉዳዩ በጥልቀት ከመግባቴ በፊት፣ እስካሁን ስለጉዳዩ ያልጻፍሁበትን ምክንያት ልናዘዝ፡፡ ሶስት ምክንያቶች ነበሩኝ፡-

Thursday, November 1, 2018

‹‹ኧረ በህግ አምላክ…››



የልጅነቴ ስነ-ልቦና እና አሁን ያለንበት ሁኔታ ሁሌም ይጋጭብኛል፡፡ በልጅነቴ፣ ሰዎች ሌባን ወይም ጉልበተኛን ‹‹ኧረ በህግ አምላክ…›› ሲሉት ይቆማል፡፡ የዘረረውን በትር ወይም መሳሪያ ወደ ሰገባው ይመልሳል፡፡ ሌባውም ‹‹ኧረ በህግ አምላክ ቁም…› ሲባል ቀጥ ብሎ ይቆማል፡፡ ይህ የሚያሳየው ኢትዮጵያ ህገ-ሰብዕን ከህገ ህሊና ጋር አስተሳስራ ትኖር የነበረች ሀገር እንደሆነች ማሳያ ነው፡፡ ላለፉት ብዙ አስርት ዓመታት የሰማናቸውና ያየናቸው ‹‹አባቱ ዳኛ፣ ልጁ ቀማኛ›› አይነት ልሙጥ የሆነ የፍትህ ስርዓት ሂደት ሁላችንም ተስፋ ቆራጭ አድርጎናል፡፡ ‹‹ስልጣን እና ገንዘብ›› ኤልሻዳዮች ሁነው፤ ህግ ሲጣስ፣ ዳሃ ሲያለቅስ ማየት ብርቅ አይደለም፡፡ ፍትህ እውነትን የማስከበር ሂደት ነው፡፡ እውነት ደግሞ በአደባባይ ተረግጣ ነበር፡፡ በፍትህ ስርዓቱ ተስፋም ሆነ እምነት ካልነበራቸው ሰዎች አንዱ ነኝ፡፡  ይህን ስሜቴንም የዛሬ ሶስት ዓመት፣ ልክ በዚህ ወር ‹‹እውነትን ሰቀሏት›› በሚል አርዕስት የሚከተለውን ግጥም ከአባሪ የምስል ቅንብር ጋር በገፄ ለጥፌ ነበር፡፡