ከ ጦቢያው አለም
ከወሎ ከሀረር፣ ከወለጋ ከወላይታ….ወጥተን
የደንበልን ሸለቆ የሱዳንን ጥሻዎች
አቆራርጠን
በቀይ ባህር አዞዎች በየመን ግርዶሾች
ተውጠን
ሞተን ተርፈን ሳውዲ አረቢያ ገብተን
ጉልበታችንን ሽጠን በልተን
በእንባችን ልብስ እያጠብን
ወዛችን ሽቶ ሆኖን ለራሳችን የነጻን
ሲመስለን ለሌሎች ከርፍተን
በረሀ የበላው ጸጉራችንን ነጭተን
ማግደን ሳት አንድደን ሞቀን
ነደን አብስለን በልተን አብልተን
ሁሌ ሞት ሲፈረድብን