በእውቀቱ ስዩም ትክክለኛው የጥበብ ሰይጣን ከለከፋቸው ጥቂት ኢትዮጵያውያን
መካከል አንዱና የወቅቱ ፈርጥ ነው፡፡ ክቡር ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ (በዕውቀቱ እንደሚለው ‘አዲስ ህልም አየሁ’) ምን አልባት ፍቅር
እስከ መቃብርን ሲፅፉ የመቼታቸው መነሻ የሆነውን ማንኩሳን ከአንዴም ሁለት ሶስቴ መጎብኘታቸው አይቀርም፡፡ በእርግጥ ማንኩሳ ከትውልድ
ቦታቸው ከእንዶደም ኪ/ምህረት በእግር ጉዞ ቀናትን የሚፈጅ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግን በመኪና የ ሰዓት ጉዞ በቂ ነው፡፡ ወደ መላምቴ
ልምጣና፣ ክቡር ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ በወቅቱ ማንኩሳን ሲጎበኙ ከቤተክርስቲያኑ ጎን ቁጭ ብለው ስለ ቦጋለ መብራቱ፣ ውድነሽ በጣሙ
እና ስለበዛብህ ሲያሰላስሉ ከዚያ ቦታ ወደፊት አንድ የጥበብ ሰው እንዲነሳ አምጠዋል (ወይም በዩኒቨርስ ህግ ሃይል አጋርተዋል
(energy sharing)::
▼
Sunday, January 24, 2016
Monday, January 18, 2016
+መንታ መንገዱ ላይ...+
እንደ ዘበት ወርደን~ከ ትናንት አቀበት
ለመውጣት ስንጀምር~የዛሬን ቁልቁለት
ነገን መዳረሻ~መንታ መንገዱ ላይ
አንዲት እርጉዝ አለች~ከርቀት የምትታይ
ከመንታ ተወልዳ~መንታ በማርገዟ
መንታ መንገዱ ላይ~የበዛ መዘዟ፤
እነዚያም ልጆቿ፡
በማይታይ ህልም~በሰነቁት ተስፋ
ሰፊ ማህፀን ውስጥ~አንዱ አንዱን ሲገፋ
መቻቻል ተረግጦ~ጥላቻ ሲፋፋ
በመን’ቶ’ች ሽኩቻ~ነጠፈ ሰላሟ
በቃር በሲቃ ድምፅ~በረታ ህመሟ፤
እንዲህ እየሆነች
የስቃይን ፅዋ~በግፍ እየጠጣች
መንታ መንገዱ ላይ~ትውልድ ታምጣለች
በ ዘላለም ጥላሁን (የእናቱ ልጅ)
ጥር 09/ 2008 ዓ.ም