Sunday, October 28, 2012

ጡመራ (blogging)

ጡመራ blogging የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል የአማርኛ ፍች ሲሆን፤ ጦመረ ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ፃፈ፣ ከተበ ማለት ነው፡፡ በመፅሀፍት መልክ ሃሰቡን የሚፅፍ ሰው ደራሲ እንደሚባለው ሁሉ ሀሳቡን በማህበራዊ ድህረ ገፅ ለሁሉም የዓለም ወገኖች በሚደርስ መልኩ በራሱ ድህረ ገፅ የሚፅፍ ሰው ጦማሪ (blogger) ይባላል፡፡ እንግዲህ እኛም ያየነውን እንመሰክራለን፤የሰማነውን እናወራለን፤ የጠፋውን እንተቻለን፤ የለማውን እናደንቃለን፤ የመሰለንን እንናገራለን፡፡ ይህ ድህረ ገፅ በእኔ የግል ጥረት ያለ ማንም አጋዥነት የተሰራ ሲሆን ማንናውም ሰው ሃሰቡን ለሌሎች በዚህ ድህረ ገፅ ለማካፈል ከፈለገ በሚከተለው አድራሻ ቢልክልኝ ለማተም ሙሉ ፈቃደኛ መሆኔን በአክብሮት እገልፃለሁ፡፡
                            zelatilahun@gmail.com
                      በመረጃ ላይ የተመሰረተ ማህበረሰብ እንፍጠር፡፡
                         ሕዳር 19፣ 2005 ዓ.ም
                           ዘላለም ጥላሁን

                         አዲስ አባባ፣ ኢትዮጵያ