Monday, July 6, 2015

ግብረ ሰዶም ወ አሜሪካ



የሰዶምና ገሞራ የጥጋብ ኃጢያት፣ የምዕራባውያን የስልጣኔ ዝቅጠት፣ የዓለማችን ታላቁ የተፈጥሮ ክህደት የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ሌዝቢያን፣ ጋይ፣ ባይሴክሽዋል እና ትራንስጀንደር” (LGBT)፡፡ እነሆ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ .. ሰኔ 29 2015 ግብረሰዶምን የሚፈቅድ አዋጅ በይፋ በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች ማፅደቃቸውን ተከትሎ ምዕራባውያን የደስታ ሲቃ ተናንቋቸው ሰንብቷል፡፡1 ናይጀሪያን በመሳሰሉ አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች የሚገኙ ዜጎችም ይህንን ዜና ወደ ሀገራቸው ማስተጋባት ጀምረዋል፡፡ በሌላ በኩል የዙምባቡዌው ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ ግብረሰዶምን በመቃወም ከምዕራባውያን ጋር ቀዝቃዛ ጦርነት ከፍተው የዓለም መነጋገሪያ ሁነው ሰንብተዋል፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያም ደስታውን መስቀል አደባባይ ወጦ የገለጠ ወራዳ ባይኖረም በማህበራዊ ሚዲያ አደባባይ ግን ኢትዮጵያዊና ሀበሻዊ ባልሆነ ቃና ይህንን እርኩስ ተግባር ደግፈው የውስጣቸውን የተነፈሱ አልጠፉም፡፡
 ጥንተ ታሪክ፡ ግብረ ሰዶም የሚለው መጠሪያ የተገኘው ከመፅሐፍ ቅዱስ ነው:: የሰዶም ስራ እንደ ማለት ነው:: ሰዶም እና ገሞራ በመፅሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 19 ላይ የተጠቀሱ የጥንት መንደሮች ናቸው:: በዚያም ጊዜ በነዚህ መንደሮች ወንድ ከወንድ: ሴት ከሴት ጋራ ይዳራ ነበር: እግዚአብሔርም ይህን አይቶ ከተማዋን በእሳት አጠፋት:: የሎጥ ሚስትም ከተማዋ ስትቃጠል ዞራ በማየቷ እንደ ሐውልት ደርቃ ቀረች፡፡ 2
 
ሰዶም                                                                      የሎጥ ሚስት
እነሆ ዓለም ከብዙ ሺ ዓመታት በኋላ ወደ ጥንተ ኃጢያቷ ተመለሰች፡፡ ግብረ ሰዶምም በይፋ በመንግስታት አዋጅ ፀደቀ፡፡ እንደ አሜሪካ ያሉ ሃገራት ጉዳዩን በይፋ ሲፈቅዱ፤ አንዳንድ ሀገራት ደግሞ ፈፅሞ የተገኘውን በስቅላት እንዲቀጣ የሚያደርግ ህግ አፅድቀዋል፡፡ መሃል ሰፋሪወች ደግሞ አይሞቀንም አይበርደንም በሚል መልኩ ዝምታን መርጠዋል፡፡
                           Fig: Distribution of Guy and Lesbian rights in the world, May 2013
በተለይ የስልጣኔ ቁንጮ ወጣች በምንላትና መሪዎቿ የእግዜርን ስም ደጋግመው በሚጠሩባት አሜሪካ ጉዳዩ በይፋ በአዋጅ ፀደቀ፡፡
NOW, THEREFORE, I, BARACK OBAMA, President of the United States of America, by virtue of the authority vested in me by the Constitution and the laws of the United States, do hereby proclaim June 2015 as Lesbian, Gay, Bisexual, and Transgender Pride Month.  I call upon the people of the United States to eliminate prejudice everywhere it exists, and to celebrate the great diversity of the American people.

IN WITNESS WHEREOF, I have hereunto set my hand this twenty-ninth day of May, in the year of our Lord two thousand fifteen, and of the Independence of the United States of America the two hundred and thirty-ninth.
                       BARACK OBAMA                    ” 1
የዚህ እኩይ ተግባር ግበረ አበሮችም መለያ ሰንደቃላማቸውን በማውለብለብ የአሜሪካን ጎዳናዎች ቦረቁባቸው፡፡               
 

 

ግበረሰዶም አፅራረ ተፈጥሮና በሀይማኖት አስተምህሮ አጅግ የተወገዘ ከመሆኑ በተጨማሪ በስነ ልቦና፣ በማህበራዊ ጉዳዮች፣ በኢኮኖሚና በጤና ላይ ከፍተኛ የሆነ ችግር ያመጣል፡፡ ለጊዜው በጤና ላይ የሚያመጣውን ችግር ጥናትን መሰረት አድርገን በጨረፍታ እንይ፡፡ ግብረሰዶም የሚከተሉትን የጤና ችግሮች ያመጣል፡፡
1.     በግብረ ስጋ ለሚተላለፉ በሽታዎች ያጋልጣል (ኤች አይ ቪ፣ ጉበት፣ ቂጥኝ፣ ከርክር፣ ጨብጥ)
2.    የምግብ የመንሸራሸር ሥርዓትን ያዛባል
3.    የክብደት መቀነስ
4.    ከፍተኛ የሆነ የአንጀትና የፊንጢጣ ህመም
5.    የፊንጢጣና የአንጀት ካንስር ያመጣል (በ 37 ዕጥፍ ይጨምራል)
6.    ተላላፊ ለሆኑ ባክተሪያዎች፣ ቫይረሶችና ፈንገሶች የመጠቃት ዕድልን ይጨምራል
7.    ከፍተኛ የሆነ የአዕምሮ ችግር ያመጣል
8.    የባህሪ ለውጥ (ወደ ሱስ እንዲገቡ ይገፋፋል)
9.    የዕድሜ ዘመንን ያሳጥራል
10.  ራስን የማጥፋት ዝንባሌን ይጨምራል

የችግሩን አሳሳቢነት ለማሳየት እስኪ ግብረሰዶምና ኤች አይ ቪ ያላቸውን ቁርኝት ዘርዘር አድርገን እንመልከት፡፡ እንደ ጎርጎሪዎሳውያን አቆጣጠር ሰኔ 1 2001 . የበሽታ መቆጣጠርና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) የህመምና የሞት ሳምንታዊ ሪፖርት (CDC Morbidity Mortality Weekly Report) የለቀቀው መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ የኤች አይቪ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው ሰኔ 5 1981 ግብረሰዶማውያን ከነበሩ አምስት የሎሳንጀለስ ነዋሪዎች ነው፡፡3

ግብረሰዶማውያን ለማሳመን ከሚያነሱዋቸው ነገሮች አንዱ ግብረሰዶም የኤች አይ ቪን ስርጭት ይቀንሳል የሚለው ነው፡፡ እውነታው ግን ይህ አይደለም፡፡ በሲዲሲ በተለያየ ጊዜ አሜሪካ ውስጥ የተደረገው ጥናት የሚያሳው የበሽታው ስርጭት በግብረሰዶማውያን ላይ እጅግ የበረታ መሆኑን ነው፡፡
“The greatest impact of the epidemic is among men who have sex with men (MSM) and among racial/ethnic minorities. In the late 1990s, Male-to-male sex has been the most common mode of exposure among persons reported with AIDS (46%), followed by injection drug use (25%) and heterosexual contact (11%) in USA.” 3
MSM account for nearly half of all people living with HIV in the United States, despite making up approximately 2% of the general population (CDC 2010).4
Table: Trends in Diagnoses of HIV Infection in the United States, 2002-2011 5
እንግሊዝ አገር የተደረገ አንድ ጥናት የሚያሳየውም ይህንኑ ነው፡፡
HIV positive homosexual men attending a London outpatient clinic commonly reported sexual behavior with a high risk of HIV transmission6
                 ይህን ኢ-ሰባዊ ዝቅጠት ሁሉም ሰው ሊዋጋው ይገባል፡፡
                             ሻሎም!
References (ዋቢ መረጃወች)
2.   ኦሪት ዘፍጥረት፡ ምዕራፍ 19 1-26
4.   HIV among gay, bisexual, and other men who have sex with men (MSM). CDC. 2010. Available from: http://www.cdc.gov/hiv/topics/msm/pdf/msm.pdf
5.   Trends in Diagnoses of HIV Infection in the United States, 2002-2011: JAMA. 2014;312(4):432-434. doi:10.1001/jama.2014.8534
J Stephenson, et al, 2003) Is use of antiretroviral therapy among homosexual men associated with increased risk of transmission of HIV infection? Sex Transm Infect. 2003 Feb; 79(1): 7–10. doi:  10.1136/sti.79.1.7

7 comments:

  1. egziabher aemiro libona yistachew!!!

    ReplyDelete
  2. gebre sedom ekawemalew.

    ReplyDelete
  3. ኦ አምላ ሆይ ህዝቦችህን አንተዉ በቸርነትህ ጎብኘን።

    ReplyDelete
  4. ተባረክልን ውድ ወንድሜ
    ጥሩ ትምህርት ሆነኝ።

    ReplyDelete
  5. ጥሩ ትምህርት ነው

    ReplyDelete