Showing posts with label ከመፅሐፍት ዓለም (from books). Show all posts
Showing posts with label ከመፅሐፍት ዓለም (from books). Show all posts

Wednesday, September 6, 2017

የአያ ሙሌ ነገር!

የአያ ሙሌ ነገር ግራ ነው! ሕይወቱም ሲበዛ ዥንጉርጉር ናት፡፡
ለምሳሌ ተራ ገጣሚ ነው እንዳንል እጅግ ተወዳጆቹ ሙዚቃዎች የርሱ አሻራ ያረፈባቸው ኾነው እናገኛለን፡፡ ብኩን ሰው ነው እንዳንል በኢህአፓ እሳት ፖለቲካ ዉስጥ ተወልዶ፣ በማርክሲዝም ሌኒኒዝም ነዶ፣ በብአዴን በስሎ፣ NGO ደመወዝ ከብሮ፣ በኢህአዴግ ላዕላይ ቤት ገብቶ፣ በጋዜጠኝነት ሠርቶ፣ ከመንግሥት አፓርታማ ተበርክቶለት የሴኮ ቱሬ ጎረቤት ኾኖ የኖረ ሰው ነው፡፡
ደግሞ ያን ሰምተን ለአንቱታ ስናዘጋጀው ድንገት ሥራውን ጥሎ ይጠፋል፡፡ ዘበኛ፣ ኩሊ፣ ወዛደር፣ ጎዳና ተዳዳሪ ይሆናል፡፡ ብቻ ያያ ሙሌ ነገር ለወሬም አይመች፡፡

Monday, June 19, 2017

እነሆ በ ክረምት-የቅኔ በረከት


በውቀቱ የ‹‹ኦሾ›› መፅሃፍ ከ እምነቱ ሳይሆን ከ ሃይማኖቱ እንዳቆራረጠው ‹‹ ከ አሜን ባሻገር›› ላይ ሹክ ብሎን ነበር፡፡ ምን አልባት በውቄ የ ‹‹ Der Antichrist›› ፀሐፊ የሆነውን የ ጀርመኑን ‹‹ፍሬዲሪክ ኒቼ››ን እጣ ፈንታ ካነበበ በኋላ ሃሳቡን የቀየረ መሰለኝ፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ከሁሉም በላይ የቀደመ ሃይማኖቱ ‹‹የማለዳ ድባብ›› ከተኛበት ቀስቀሶ፣ ከሄደበት መልሶ፣ የቅኔ ጣእሩን አስተንፍሶ ለመድብሉ የወል ስም እንዲሆን ያሰገደደው፡፡ በ ቆመበት ማን ይኖራል! በውቀቱ ገጣሚ መሆኑ ብቻ ሳይሆን እይታው በጣም ይገርመኛል፡፡ ለማኛውም እምነትህ የራስህ ነው፣ ግጥምህን በ ቶሎ ወዲህ በል!….ከፈለግህ በ ‹‹ኦሾ››…አሊያም በ‹‹ኒቼ›› ማመን ትችላህ፡፡ አይመለከተኝም! ይችን ነገር ልጠቀም መሰለኝ (lol)

አለ እንጂ ደግሞ ያ በላይ በቀለ ‹‹አንቅልፍ እና ሴት›› የሚለውን ክሽን ግጥም ሸበሌ መርቀን አጣጥመን ዓመት ሳይሞላን ‹‹ከ ሴተኛ አዳሪ የተኮረጀ ሳቅ›› ብሎ ሊያስቀን ይሁን ሊያሳቅቀን ከተፍ ብሏል፡፡  ይህ ብላቴና የራሱ የሆነ ድንቅ እይታና የ ግጥም ቆጠራ ዘዴ ያለው ልጅ ነው፡፡ ‹‹መልሱን ጠጣሁበት››፣ ‹‹እንቅስቃሴዎች ሁሉ ፖለቲካ ናቸው›› በጣም የመሰጡኝ ግጥሞች ናቸው፡፡ የግጥም ከራማው ይጠብቅህ!

Sunday, January 24, 2016

“ከ አሜን ባሻገር”

እውቀቱ ስዩም ትክክለኛው የጥበብ ሰይጣን ከለከፋቸው ጥቂት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱና የወቅቱ ፈርጥ ነው፡፡ ክቡር ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ (በዕውቀቱ እንደሚለው ‘አዲስ ህልም አየሁ’) ምን አልባት ፍቅር እስከ መቃብርን ሲፅፉ የመቼታቸው መነሻ የሆነውን ማንኩሳን ከአንዴም ሁለት ሶስቴ መጎብኘታቸው አይቀርም፡፡ በእርግጥ ማንኩሳ ከትውልድ ቦታቸው ከእንዶደም ኪ/ምህረት በእግር ጉዞ ቀናትን የሚፈጅ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግን በመኪና የ ሰዓት ጉዞ በቂ ነው፡፡ ወደ መላምቴ ልምጣና፣ ክቡር ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ በወቅቱ ማንኩሳን ሲጎበኙ ከቤተክርስቲያኑ ጎን ቁጭ ብለው ስለ ቦጋለ መብራቱ፣ ውድነሽ በጣሙ እና ስለበዛብህ ሲያሰላስሉ ከዚያ ቦታ ወደፊት አንድ የጥበብ ሰው እንዲነሳ አምጠዋል (ወይም በዩኒቨርስ ህግ ሃይል አጋርተዋል (energy sharing)::

Sunday, June 7, 2015

›››የሐበሻ ጀብዶ›››የኢትዮጵያውን የነፃነት ተጋድሎ›››


                                        ለፒዲኤፍ ይህንን ይጫኑ
ኢትዮጵያዊ ነህ? ሐበሻ ነህ? ሐበሻ ከሆንክ መጀመሪያ የሐበሻ ጀብዶንና ቀይ አንበሳን አንብብ፡፡ የቅድመ አያትህ፣ የአያትህና የአባትህ ታሪክ ነው፡፡ ዘመን የማይሽረው የሀበሻ ወኔ፣ ችግር ማይበግረው ጀግንነት፣ ሀገር ወዳድነትና ዘላለማዊ የሆነ የወገን ፍቅር በቀይ ቀለም የተከተቡበት ድንቅ መፅሐፍ፡፡ ስለማንነትህና ስለ ዘርህ አትጨነቅ ብቻ ሀባሻ ሁን፡፡ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ትግሬ የትኛውንም የኢትዮጵያ ዘር ብትሆንም ይህ ያንተ የሀበሻው ታሪክ ነው፡፡ ቅድመ አያትህ፣ አያትህ፣ አባትህ ወይም ከወገኖችህ አንዱ አድዋ ነበር፤ ማይጨው ነበር፣ አቢ አዲ ነበር፣ መቀሌ ነበር፣ ኮረም ነበር፣ ተከዜ በረሃ ነበር፤ ኢትዮጵያን ከጠላት ሊታደግና ያልተበረዘ ማንነት ሊያወርስህ፡፡ አንተ የነዚያ ጀግኖች ውጤት ነህ፡፡ አጥንታቸውን ከስክሰው፣ ደማቸውን አፍሰው በከፈሉልህ መስዋትነት ቀና ብለህ የምትጓዝ ነፃ ትውልድ! አንበው ቢያንስ ማንነትህና ታሪክህ ነው! ማንነቱን በትክክል የተረዳና ታሪኩን የሚያውቅ ትውልድ ማንም በደነፋ ቁጥር አይበረግግም፤ ታሪክ ጠቅሶ መፅሐፍ አስደጉሶ ስለማንነቱ ይከራከራል እንጂ፡፡

የአሲምባ ፍቅር


ከውስጥ በገነፈለ ስሜት፣ በተመረጡ ውብ ቃላት፤ የተፃፈ ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የፍቅርና የትግል ታሪክ፡፡ ባለታሪኩ እንዲህ ብሎ ይጀምራል፡

“ከልብ በመነጨ ፍቅርና ቁርጠኝነት በለጋ እድሜየ የጀመርኩት ጉዞ አቅጣጫውን የቀየረው ባላሰብኩት ሁኔታና ወቅት ነበረ፡፡ ማንኛውም ሰው በሁኔታዎች አስገዳጅነት ያላሰበበትንና አልሞ ያልመረጠውን ሕይወት እንደሚቀበል ሁሉ እኔም እጣ ፈንታዬን ከተቀበልኩና በመራኝ ጎዳና መንገድ ከጀመርኩ በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡