Sunday, December 24, 2017

አዲስ አበባ (በረራ)

እንዲህ ብሎ መጣፍ አሰኘኝ፡፡
የአዲስ አበባ ሰማይ ጎህ ሲቀድ፥ ካድሬም ቢሆን የሚያሳቅፈውን የታህሳስን ውርጭ እንደምንም ታግዬ ከምኝታዬ ታፋታሁ፡፡ፀጥ ባለው የአዲስ አበባ ሰማይ ስር፥ የሰንበት ቅዳሴ አድማሱን ተሻግሮ ከብርዱ ጋር የሚታገለውን የአማንያንን ልብ በሐሴት ይጠራል፡፡
"እምነ በሐ....ቅድስት ቤተክርስቲያን......አረፋቲሃ......"
;
ይቀጥላል፡፡
ከገደል ማሚቶው ቀጥሎ የሌላ ደብር ምስጋና የብርዱን ቆፈን እንደ ሰም ያቀልጣል፡፡ አማኒያን ነጠላቸውን መስቀለኛ አጣፍተው ውር ውር ይላሉ፡፡
አዲስ የሁላችንም ናት፡፡ የካድሬው፥ የወሬኛው፥ የሃብታሙ፥ የድሃው፥ የዘረኛው፥ የኢ-ዘረኛው፥ የለፍቶ አዳሪው፥ የአማኙ፥ የቀማኛው፥ የአሳሪው፥ የታሳሪው፥ የምሁሩ፥ የባዶ ጭንቅላቱ፥ የእግረኛው፥ የባለ ሐመሩ፥ የጦም አዳሪው፥ የሰክሮ አደሩ ከተማ ናት፡፡

Friday, December 8, 2017

የሰፊው ህዝብ ግጥሞች

➊አንቺን የለመዱ ብዙ ሰዎች ሳሉ
የቤቱ ሙሉ አዛዥ እንግዳ ነው አሉ
➋አንቺ አሽከር ነገርሽ ከኮሶ ባሰሳ
ያስቀምጠኝ ጀመር ሌሊት እያስነሳ
➌ አዋዜው በዛና ምላሴን ተኮሰው
አነካክቶ መብላት፥ መች አውቅና እንደ ሰው
➍አየሁ አዝመራሽን አውሬ ሲጨርሰው
እንዲህ ሆነሽ ቀሪ፥ ይመስለዋል ለሰው
➎አጎንብሰሽ መሄድ አላውቅ ብዬ እንደ ሰው
እቀና ብዬ ነው ቤቴ የፈረሰው
➏እኔን ከፋኝ እንጂ ሀገሬን ምን ከፋው
ግራር አበቀለ ዝሆን የማይገፋው

➐እኔ ልኮራመት እኔ ከሰል ልምሰል
ስቀሽ አታስቂኝ የደላሽ ይመስል
፡
፡
ሌላ ጨምሩ እስኪ?