Showing posts with label ሐይማኖት (Religion). Show all posts
Showing posts with label ሐይማኖት (Religion). Show all posts

Friday, November 16, 2018

የሊቀ ስዩማን መዝገቡ ጉዳይ እና የአዊ ሀገረ ስብከት ውዝግብ-ክፍል ሁለት



በሐይማኖትና በዘር ጉዳይ ከእንግዲህ አልፅፍም ብዬ ለራሴ ቃል ብገባም፣ የጉዳዩ አሳሳቢነት ህሊናዬን ሰላም ነሳኝ መሞነጫጨር ጀመርሁ፡፡ ትናንት ማታ 8 ሰዓት ላይ ይህን ጉዳይ በገፄ ከለጠፍሁ በኋላ ብዙ መልክቶች በተለያዬ መልኩ ወደእኔ ደርሰዋል፡፡ ብዙዎቹ ቅንነት የሞላባቸው ናቸው፡፡ ሊቁን ለማገዝ የሚጠይቁም አሉ (መጨረሻ ላይ ሂሳብ ቁጥራቸውን አስቀምጣለሁ፣ ዘላቂ መፍትሔ ባይሆንም)፡፡
ወደ ጉዳዩ ከማምራታችን በፊት፣ ሁላችንም ከአሸናፊው እውነት ጋር እንሆን ዘንድ፣ ዛሬ ጥዋት አንድ ወዳጄ በአስተያይት ማስፈንጠሪያው ላይ ያስቀመጣትን የማህተመ ጋንዲን ጥቅስ አይተን እንለፍ፡
በምድር ላይ ብቻህን ብትቀር እንኳን ከግፈኞች ጋር አትተባበር። ዓለም ዓይኗን ብታቀላብህ አንተ ግን ፈገግታህን ለግሳት፡፡ አትፍራ፡፡ በልብህ ውስጥ ያለውን የእውነት ድምፅ ብቻ ታመን፡፡ ድምጽ እንዲህ ይላል:- ባለንጀራህ፣ ሚስትህ፣ ዘመዶችህ፣ ጳጳስህ ሁሉም ቢተውህ ለምትኖርለትና ልትሞት ለተዘጋጀህበት እውነት ብቻ መስክር፡፡ የመኖር ትርጉሙ ይህ ነውና›› ማኅተመ ጋንዲ

Sunday, November 4, 2018

ባቀኑት ሀገር ስደተኛ የሆኑት ሊቅ እና የአዊ ሀገረ ስብከት ውዝግብ

                              (የአቡነ ቶማስ የመጀመሪያው በትር ያረፈባቸው ሊቀ ስዩማን መዝገቡ እስከዚያ)
‹‹ አንተን ምዕመኑ ስሚያምንህ መድረክ ላይ ወጠህ ማኅበረ ቅዱሳንን እያወገዝህ ስበክ››-----ብፁዕ አቡነ ቶማስ ለሊቁ
‹‹ እርስዎ ምን አሰቡ ኤኔታ››------እኔ
‹‹ላድርገው ብል እንኳን ህሊናዬ እንዴት ይቀበለዋል፡፡ በአይኔ ያየሁትን የማኅበሩን ስራ እንዴት እክዳለሁ፣ እንዴት እዋሻለሁ››----ሊቀ ስዩማን መዝገቡ
‹‹ታዲያ በምን መልኩ መቀጠል አሰቡ››----እኔ
‹‹ እስከሚያባርሩኝ ድረስ እሰራለሁ፣ ከተባረርሁም ፍትህን ከእግዚአብሔር እጠብቃለሁ››--ሊቀ ስዩማን መዝገቡ
-----------------------------------------------------------------------------------------------------
ማን ነበር ‹‹ብሸሸው ብሸሸው አለቀቀኝም›› ያለው፡፡ በአዊ ሀገረ ስብከት፣ ከሀገረስብከት አስተዳደርና ከሃይማኖት አስተምሮ ጋር ተያይዞ ስለተነሳው ውዝግብ ከማንሳቴ በፊት፣ የነገሩን ስረ መሰረት ለመረዳትም ያግዝ ዘንድ የኤንታ መዝገቡን ጉዳይ ላስቀድም፡፡ ከላይ መግቢያ ላይ የጠቀስሁት ‹‹ቃለ ምልልስ›› ከሊቁ ጋር ያደረግነው ልክ የዛሬ ዓመት (2010 ዓ.ም) ለጥቅምት ሲኖዶስ ወደ አዲስ አበባ መጠው ከእኔ ዘንድ ባረፉበት ወቅት ነበር፡፡ የኤኔታን እና የእኔን ግንኙነት ብዙ ሰው ያውቀዋል፡፡ ከላይ ያነሳሁትም አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ወደ ጉዳዩ በጥልቀት ከመግባቴ በፊት፣ እስካሁን ስለጉዳዩ ያልጻፍሁበትን ምክንያት ልናዘዝ፡፡ ሶስት ምክንያቶች ነበሩኝ፡-

Friday, September 22, 2017

የጋሽ በጋሻው ነገር!

‹‹ ሳይማር ያስተማረና ሳይተርፈው የደገሰ ትርፉ ፀፀት ነው››
                    መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
ሰሞኑን የማህበራዊ ሚዲያዎች ‹‹ጋሽ በጋሻው ለምዱን ገፎ በገሃድ ኦርቶዶክስ ይደለሁም አለ››…….አንዳንዶች ደግሞ ‹‹እምነት የለኝም አለ›› ሌሎች ደግሞ ‹‹ፕሮቴስታንት ነኝ አለ›› ይላሉ፡፡ ነገ ደግሞ ይህ ሰውዬ ‹‹ሰው አይደለሁም›› ብሎ እንዳይመጣ እፈራለሁ፡፡
አንድ ሰው የየትኛውም እምነትና ሐይማኖት (ሁለቱ የተለያዩ ናቸው) አማኝና ተከታይ ከመሆኑ በፊት ሰው መሆን አለበት፡፡ አንድ ሰው ‹‹ሰውነት›› ከተላበሰ ያውም በሐይማኖት ስም ለብዙዎች መሰናከያና መወናበጃ ምክንያት መሆን የለበትም፡፡ የሚያምንበትን ነገር ከስር መሰረቱ ግልፅ አድርጎ የፈለገውን ሃይማኖት መከተል መብቱ ነው፡፡ በሌሎች ጓዳ እየገቡ መፈትፈት ግን ኢሞራላዊ ነው፡፡

Wednesday, March 30, 2016

በ እንተ “ማኅበረ ቅዱሳን”: ክፍል_2


 በ ፒዲኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ


እውን ማኅበረ ቅዱሳን ለ ቤተክርስቲያን  ስጋት ወይስ አቃቤ?
በቤተክርስቲያኗ ህግ መሰረት ማህበረ ቅዱሳን ተፈቀደለት መስመር ከወጣ፤ መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አውጥቶ ማየትና የእርምት እርምጃ መውሰድ የሲኖዱሱ ጉባኤ ስልጣን ነው፡፡ ይህ ከሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተክርስቲያኗ ስጋት የሚሆንበት አንዳችም መንገድ አይታየኝም፡፡ ከዚህ ባለፈ ከ ሲኖዶሱ እውቅና ውጭ በተለያዩ አካላት “ሾላ በድፍን” የሚደረጉ ዘመቻዎች የምዕመናንን ሰላም ከማወክ ያለፈ የረባ  ፋይዳ ይኖራቸዋል ብዬ አላስብም፡፡ በሌላ በኩል ግን ጥንታዊ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለማደስ በሚል ተልዕኮ በየቀኑ ለሚፈለፈሉ ምዕራብ ወለድ ሃይማኖቶች ከሆነ አሁንም ቢሆን ማኅበረ ቅዱሳን ስጋት ነው፡፡

Monday, March 28, 2016

በ እንተ “ማኅበረ ቅዱሳን”: ክፍል_1

(ትዝብትና ነፃ አስተያየት)
                  ( ዘላለም ጥላሁን_ zelatilahun@yahoo.com)
ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? መች ተመሰረተ? ዓላማው ምንድን ነው? ቤተክርስቲያን ምን አበረከተ?   ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ለምን ጠሉት? የሁሉም ቀስትስ ለምን ወደ ማኅበረ ቅዱሳን አነጣጠረ? እውን ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተክርሰቲያን ስጋት ወይስ አቃቤ?
(የውጭ አካላትን ጣልቃ ገብነት ለጊዜው ተወት አድርገን እስኪ መረጃ እያጣቀስን ወደ ውስጥ እንመልከት)
ቅድመ ታሪክ (ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው?): መተከልና ጋምቤላ መንደር ምስረታ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የፅዋ ማኅበራትና የብላቴ ዘመቻ ማኅበረ ቅዱሳን መመስረት ትልቅ ድርሻ ቢኖራቸውም ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ እና ብፁዕ / አቡነ ገብርኤል ወጣቶችን ሰብስቦ ከማስተማር ወደ አንድ የማኅበር ስያሜ እስከ ማምጣት ድረስ ያደረጉት ተጋድሎ ለማኅበሩ ቀጥ ብሎ መቆም መሰረት መሆኑን በጊዜው የነበሩ አባላት ሁሌም የሚናገሩት ሃቅ ነው1፡፡ በተለይ እምነቱን በእነ ሌሊንና እስታሊን ፍልስፍና ቀይሮ ሶሻሊስት አብዮት ጨርቁን ጥሎ በከነፈው ትውልድ መሃከል ስለ አብያተ እምነት የሚቆረቆር ትውልድ መኖሩ ነበር እኒህን አባቶች  “ ልጆቼ እኛ እናንተን መፈለግ ሲገባን እናንተ እኛን ፈልጋችሁ መጣችሁ፣ ንፍሮ ቀቅለን፣ አዳራሽ ባይኖረንም ድንኳን ጥለን እናስተምራችኋለን1,2,3,4 ብለው እንዲቀበሏቸው ያደረጋቸው፡፡