Showing posts with label ጤና (Health). Show all posts
Showing posts with label ጤና (Health). Show all posts

Friday, June 17, 2016

“Save Antibiotics…”

Drugs are not chocolate
Don’t use to change your taste
Drugs may cause life loss
If not taken in the right dose
…………………
If you go to drugs more
They will become very far
If no action today
No more drugs you will die
See the life on your hand
Don’t abuse drugs as you had

Monday, July 6, 2015

ግብረ ሰዶም ወ አሜሪካ



የሰዶምና ገሞራ የጥጋብ ኃጢያት፣ የምዕራባውያን የስልጣኔ ዝቅጠት፣ የዓለማችን ታላቁ የተፈጥሮ ክህደት የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ሌዝቢያን፣ ጋይ፣ ባይሴክሽዋል እና ትራንስጀንደር” (LGBT)፡፡ እነሆ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ .. ሰኔ 29 2015 ግብረሰዶምን የሚፈቅድ አዋጅ በይፋ በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች ማፅደቃቸውን ተከትሎ ምዕራባውያን የደስታ ሲቃ ተናንቋቸው ሰንብቷል፡፡1 ናይጀሪያን በመሳሰሉ አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች የሚገኙ ዜጎችም ይህንን ዜና ወደ ሀገራቸው ማስተጋባት ጀምረዋል፡፡ በሌላ በኩል የዙምባቡዌው ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ ግብረሰዶምን በመቃወም ከምዕራባውያን ጋር ቀዝቃዛ ጦርነት ከፍተው የዓለም መነጋገሪያ ሁነው ሰንብተዋል፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያም ደስታውን መስቀል አደባባይ ወጦ የገለጠ ወራዳ ባይኖረም በማህበራዊ ሚዲያ አደባባይ ግን ኢትዮጵያዊና ሀበሻዊ ባልሆነ ቃና ይህንን እርኩስ ተግባር ደግፈው የውስጣቸውን የተነፈሱ አልጠፉም፡፡