Monday, February 17, 2020

#ውሸታሙ_ዓብይ ወይስ #ተመስገን?

 ከሰኔ 15 ማግስት ጄኔራል አሳምነውን በተመለከተ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ መፅሔት አንድ ሐተታ ፅፎ ነበር።ቃል በቃል ባይሆንም እንዲህ ይላል ተመስገን " ዝዋይ ማረሚያ ቤት ጄ/አሳምነው ጋር አብረን አንድ ክፍል ነበርን። እኛ ካርታ ጨዋታ እናበዛ ነበር። እኔ ሌሊት ተነስቼ ሁሉ እንጫወት ብዬ እቀሰቅስ ነበር። ጄ.አሳምነው ግን ፕሮግራም አውጥቶ ሌሎችን መፅሐፍ ቅዱስ ያስጠና ነበር። በጣም ይፆም ነበር። ለእኔ አሳምነው ይህንን ድርጊት ያደርጋል ብዬ ለማመን ይከብደኛል" በማለት የራሱን ብያኔ ያስቀምጣል።
ቀጥሎም አሳምነው ከአብይ ጋር ስለ ነበረው ግንኙነት እንዲህ ሲል ያትታል። ጄኔራል አሳምነው እስር ቤት እያለን ስለ አብይ አውርቶኝ ነበር። ቃል በቃል ያለውንም እንዲህ ሲል ያስቀምጣል
"ወደ እስር ቤት ከመግባቴ በፊት ወዳጆች ነበርን። አንድ ቀን የእኔን መኖሪያ አብይ በጓደኝነት ሰበቭ መጥቶ ሰለላት። እኔ ወደ እስር ቤት ስገባ የእኔ መኖሪያ ቤት አብይ መኖር ጀመረ" በማለት እንዳጫወተው ይገልፃል።