(በቅዱስ ሃብት በላቸው)
ነሃሴ 9 ቀን በኢትዮጵያ የነፃ ፕሬስ ታሪክ ፋና-ወጊ ተብለው በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የሆነው የመብሩክ/መብረቅ ጋዜጣ አሳታሚና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ወርቁ ዓለማየሁ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየበት ዕለት ነው። “ትንሿ ትግራይ!” በሚል ርዕስ በአንድ መንግስታዊ ተቋም ውስጥ ከላይ እስከታች የተሰገሰጉትን የአንድ ብሔር ሰዎች በማስረጃ ማጋለጡን ተከትሎ ድንገት ታፍኖ እስር ቤት ተጥሎ የነበረው ጋዜጠኛ ወርቁ፣ ከእስር ቤት እንደወጣ ነበር እስከወዲያኛው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየን።Labels
- ሐይማኖት (Religion) (8)
- ማህበራዊ ጉዳይ (Social Affair) (42)
- ሳይንስና ቴክኖሎጂ (Science and Technology) (4)
- ባህል (Culture) (11)
- ታሪክ (History) (20)
- ከመፅሐፍት ዓለም (from books) (6)
- የጉዞ ማስታወሻ (Journey’s log) (4)
- ግጥም (Poam) (44)
- ጤና (Health) (3)
Showing posts with label ታሪክ (History). Show all posts
Showing posts with label ታሪክ (History). Show all posts
Thursday, August 16, 2018
Wednesday, July 4, 2018
ሻምበል አስረስ ገላነህ ብዙነህ [ጎጃሜው]
(የግፍ ጥግ የተፈፀመበት የጦር መኮንን)
ለመጀመሪያ ጊዜ በአማራ ህዝብ ላይ እየተሰራ ያለውን አሻጥር ፊት ለፊት የተጋፈጠ
የጦር መኮንን ይህ ሰው ይመስለኛል፡፡ ‹‹ሳሞራ››ን ፊት ለፊት የተጋፈጠ፣ ባህርዳር በተደረገው ስብሰባ ከእነ በረከት እና ህላዌ
ጋር ‹‹በአማራ ስም አትነግዱ›› ብሎ ፊት ለፊት የተፋጠጠ የመጀመሪያው ሰው ይህ ይመስለኛል፡፡ በዚህም ድርጊቱ ‹‹ ጎጃሜው››
የሚል ቅፅል ስም እንደተሰጠው ባለታሪኩ ይገልጻል፡፡ በዝሆኖች ጥርስ የተነከሰበት ይህ ቆፍጣና የጦር መኮንን የማታ ማታ ‹‹ የአልጋ
ቁራኛ›› የሚያደርገው ግፍ፣ እላዩ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ ፓርላማ ፊት ለፊት እራሱን እንዲያቃጥል ያስወሰነው መከራ ተፈፀመበት፡፡
ይህ ሰው ‹‹የካድሬው ማስታወሻ›› የተሰኘ ግለ ታሪክ 2005 ዓ.ም
አካባቢ ለንባብ አብቅቷል፡፡ መፅሃፍ አንብቤ ያለቀስኩበትን፣ ከመጠን በላይ ልቤ የተነካበትን ጊዜ አላስታውስም፡፡ የዚህን ጀግና
ግለታሪክ ሳነብ ግን አልቅሻለሁ፡፡ በማልቀስ ብቻ አላለፈም፣ ከውስጥ የሆነ ተስፋ ሲሰበር ይታወቀኝ ነበር፡፡ የጭካኔን ጥግ ያየሁበት
ትርክት ስለሆነ!
Monday, March 5, 2018
የተዘነጋው ሌላኛው የኢትዮጵያውያን የድል በዓል (የካቲት 26)
Colonel Mengistu H/Mariam Victory Momentum
የኢትዮ-ሶማሊ ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው የኦጋዴን ጦርነት ከ ሶማሌ ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ጋር ሀምሌ 1968 ዓ.ም ተጀምሮ የካቲት 1970 ዓ.ም የተጠናቀቀ ጦርነት ነው፡፡ መጀመሪያ በሶቪዬት ህብረት ቀጥሎም በ ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ኢትዮጵያን የወረረው የሰይድ ባሬ (ዚያድባሬ) ጦር ‹‹የእናት ሀገር ጥሪ›› እያለ ከመላው የኢትዮጵያ ምድር በተሰባበሰበ ጀግናው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ድባቅ ተመታ፡፡
የካቲት 26፣ 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሰራዊት በመልሶ ማጥቃት ካራማራ ተራራ ላይ ከባድ ውጊያ አካሄደ፡፡ ከዚያም ጅግጅጋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ፡፡ ከ አራት ቀናት በኋላ ሁኔታው ያስፈራው ሰይድ ባሬ ፣ የሶማሊያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ምድር ሙሉ በሙሉ ለቆ እዲወጣ ጥሪ አስተላለፈ፡፡ ኢትዮጵያውያንም በድል ተመለሱ፡፡ በጦርነቱ ኩባ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር ድጋፍ አድርጋለች፡፡ ከ 16,000 በላይ የኩባ ወታደሮችም የታሪኩ ተካፋይ ናቸው፡፡ ታላቋ ሶማሊያም ፈራረሰች፡፡ የዚያድባሬ የመጨረሻ ቃልም ‹‹ Nothing is permanent on
this world’’ በሚል ተቋጨ፡፡
Friday, March 2, 2018
¶አድዋ¶
አድዋ ታሪክ ብቻ አይደለም
አድዋ ትዝታ ብቻ አይደለም፡፡
አድዋ ህልም ነው፣ በከንቱ ቅዠት ያልተረታ
አድዋ ቅኔ ነው፣ በጥቁር ጀግኖች የተፈታ፤
አድዋ መዶሻ ነው፣ የዘር አጥርን የሰበረ
አድዋ ፍትህ ነው፣ ሰውን በእኩል ያስከበረ፤
አድዋ እምነት ነው፣ በ ታምራት የነገሰ
አድዋ ምናብ ነው፣ በአጥር ብዛት ያልፈረሰ፤
አድዋ ብርሃን ነው፣ ለጭቁኖች የበራ
አድዋ ተስፋ ነው፣ ትውልድን የሚመራ፤
አድዋ መንፈስ ነው፣ ‹ሰው› መሆንን ያስወደደ
አድዋ ሀረግ ነው፣ አንድ ኢትዮጵያን ያዋሃደ፤
አድዋ ……….አድዋ (122x)…….ዋዋዋዋ!
=========================
Zelalem T
ለ123ኛው በዓል በሰላምና በአንድነት ያድርሰን!
=========================
Subscribe to:
Posts (Atom)





