Thursday, July 2, 2015

የመምህራን ቀልዶችና ምሳሌዎች

መምህራን አንዳንዴ ተማሪ ለጠየቀው ጥያቄ መልስ መስጠት ሲያቅታቸው ወይም ሲደብራቸው ቀልድ አዘል የሆነ መልስ ይመልሳሉ፡፡
ቀልድ አንድ፡ እስኪ አንደኛ ደረጃ /ቤት የሂሳብ መምህር ከነበሩትና ተማሪው ትዕቢተኛ ናቸው ከሚላቸው ከጋሽ _______እንጀምር፡፡
ተማሪ ጋሸ
መምህር አቤት
ተማሪ የሜትርና የኪሎ ሜትር ዝምድናቸው ምንድን ነው፡፡
መምህር አታውቀውም እንዴ፣ የአክስትና የአጎት ልጆች ናቸው፡፡

ቀልድ ሁለት፡ ይህ ደግሞ የህብረተሰብ ሳይንስ የዲፕሎማ ተማሪ ነው፡፡ ለልምምድ ወደ አንድ አንደኛ ደረጃ /ቤት ተላከ፡፡  አንድ ተማሪ የዝናብን አፈጣጠር ለማወቅ ካለው ጉጉት አንፃር አንዲህ ሲል ጠየቀ፡
ተማሪ ጋሸ ጥያቄ አለኝ
መምህር እሺ ምንድን ነው ጥያቄህ ቀጥል፡፡
ተማሪ ዝናብ እንዴት ነው የሚዘንበው
መምህር እንደማዳመን እንደማዳመን ብሎ ለቆ ለቆ ይተወዋል፡፡  ብሎ መለሰ፡፡ እንግዲ አሱንም ያሰተማረው መምህር እንደዚህ ብሎ አስተምሮት ይሆናል፡፡
ቀልድ ሶሰት፡ እኒህ ደግሞ የአንድ ዩኒቨርሲቲ የማይክሮባዮሎጂ መምህር ናቸው፡፡ ባክቴሪያ በሽታ የሚለዩ ጀግና ናቸው ተብሎ ይፎከርላቸዋል፡፡ አንድ ቀን አንድ ተማሪ ጠየቃቸው፡፡
ተማሪ ይህ ባክቴሪ በብዛት ጉዳት የሚያመጣው የት ነው፡፡
መምህር ልጆች ይህ የባክቴሪያ ዝርያ ባለጌ፣ ወስላታና ስራፈት ነው፡፡ እንደዘመኑ ዲያስፖራዎች ወደ ጭን መካከል ብቻ ነው ሚመለከተው፡፡  የመራቢያ አካሎችን ነው ብዙ ጊዜ ሚጎዳው፡፡
ምሳሌ አንድ፡ The course was chemistry. The teacher was Mr Gebre. Now, he is not alive. He was really outstanding Teacher. RIP
Student: How positive and negative ions/charges attract each other?
Mr. Gebre: It is simple. When male and female come together, they hold each other…opposite charges are like this. However, male and male….female and female repel each other…similar charges are like this.
If Mr. Gebre is alive today, he may said like this: “Dear students, my previous example disproved by America since homosexuality is legalized there, so please try to understand without example.
ምሳሌ ሁለት፡ ይኸኛው የአራተኛ ክፍል የባዮሎጂ መምህር ናቸው፡፡ ስለ ባለአንድ ክክና ባለሁለት ክክ ፍሬዎች እያስተማሩ ነው፡፡ መመህሩ ጠየቁ፡፡
መምህር፡ አስኪ ባለ ሁለት ክክ የሚያፈሩ አዝርዕቶችን የሚነግረኝ ተማሪ አለ፡
ተማሪ ጋሸ እኔ፣ ጋሸ እኔ
መምህር እሺ አንተ ፊትህን ያልታጠብኸው፡፡
ተማሪው አተር ብሎ ሊናገር የነበረው ተማሪ ፊቱን ባለመታጠቡ ተሸማቆ በቆሎ ብሎ መለሰ፡፡
መምህር አልመለስህም፡፡
መምህሩ ለሌሎች እድል መስጠት አልፈለጉም፡፡ ብዙ ተማሮችም ተሸማቀው እጃቸውን መሰብሰብ ጀመሩ፡፡ የተወሰኑት ንፍጣቸውን በሹራባቸው እየጠረጉ  ጋሸ እኔ፣ ጋሸ እኔ…….ማለት ጀመሩ፡፡
መምህርፀጥታ ልጆች ይህ በቀላሉ አይመለስም፡፡ ሁላችሁም ነገ የባቄላ፣ የስንዴ፣ የገብስ፣ የአተር፣ የሽንብራና የበቆሎ እሸት  ይዛችሁ ኑ፡፡ ያገኛችሁትን አምጡ፡፡ በደንብ ያመጣ አስሩ አስር ያገኛል፡፡ብለው አሰናበቷቸው፡፡ ተማሪዎች እንደተባሉት ወንዶች በፎጣቸው፣ ሴቶች በፀጉር መሸፈኛቸው የቻሉትንና ያገኙትን ይዘው መጡ፡፡
መምህር አመጣችሁ ልጆች፡፡ ጎበዞች፡፡ ይህ ባለ አንድ ነው፣ ይህ ደግሞ ባለሁት ነው፣ አሉ ሁለት በቆሎና ባቄላ ከአንዱ ልጅ ተቀብለው በጠፍራቸው ፈርቅተው እያሳዩ፡፡ አሁን በድንብ ገባችሁ አይደል ልጆች አሉ የፈረቁትን እሸት ለአነዱ ተማሪ እንዲበላው እየሰጡት
ተማሪዎች አዎ መምህር፡፡ የተወሰኑ ልጆች ቀድሞም ገብቶናል ብለው አጉረመረሙ፡፡
መምህርበሉ ተማሪዎች ያመጣችሁትን አሸት ማርክ ስላልሞላሁ፣ ተስልፋችሁ እያስመዘገባችሁ ቢሮየ አስቀምጣችሁ ትሄዳላችሁ፡፡ተማሪዎች በጣም ተናደዱ፡፡ እርቧቸዋል፡፡ ጎምዥተዋል፡፡ እንዳይበሉ፣ ማርክ ይቀንስባቸዋል፡፡ ከዚያም አንዳንዶች የጓደኞቻቸውን መብላት ጀመሩና ጠብ ተፈጠረ፡፡ መምህሩም የተጣሉትን ተቆጥተው፣ የመጣውን እሸት ተማሪዎች ለእጅ ስራ ትምህርት ብለው በሰሩት ቅርጫት ላይ ካስከመሯቸው በኋላማርኩን ሞልቸ ነገ አሳያችኋለሁብለው አሰናበቷቸው፡፡ ከዚያም መምህራን እሸቱን እየጠበሱና እየቆሉ ለአንድ ሳምንት እንትን በእንትን (ቃሉ አይነኬ ነው፣ ነቄ ያለ ይወቀው) ሁነው በድግስ ሰነበቱ፡፡ መምህሩም ማርኩን ከአምስት ብቻ ያዙት፡፡ የዛሬ ተማሪ አምጣ ቢባል ያመጣ ይሆን? ደግ ዘመን፡፡ ከተማሪው ተርፎ ለመምህሩ የሚሆንስ እሸትስ አለ ብላችሁ ነው?





No comments:

Post a Comment