Sunday, August 23, 2015

አስገራሚዋ ብላቴና (The Miracle Teenager)

By: Remzi Akibaw
በምስሉ የምትመለከቷት አስገራሚዋ እንስት ስምረት ይታይህ ትባላለች፡፡ ቃለ ምልልስ ያደረገላት ረምዚ አክባው የተባለ የማህበራዊ ድህረገፅ ጓደኛዬ ነው፡፡ ቃለ ምልልሱ ከያዘው አጅግ አሳዛኝ፣ አስገራሚና አስተማሪ ታሪክ የተነሳ እሱን አስፈቅጀ በዚህ ገፅ ለጥፌዋለሁ፡፡ ረምዚ አክባውን በአንባቢያን ስም ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
                ቃለምልልሱ ይቀጥላል….. መልካ ንባብ!!!
«እሽ እህታችን በመጀመሪያ ስምሽን ብታስተዋውቂን?…»
«ስምረት ይታይህ እባላለሁ
«እስኪ ካለን ሰዓት አንፃር ያሉትን ነገሮች አሳጥረን እናውራናእንዴት ነው ስራ ? እንዴትስ ወደዚህ ስራ ልትገቢ ቻልሽ
«ስራ ጥሩ ነውከጥሩነቱ በላይ ደግሞ ፈታኝ ነው። ወደዚህ ስራ የገባሁት ያው እናቴ ከኔ ውጭ ልጅም ሆነ ቤተሰብ ስላልነበራት ማንም የሚረዳት የለምለዛ ነው!( ፈገግታ…)»
«
ማለት ከመቼ ጀምሮ ነው አንቺ የምታስተዳድሪያት ? ትምህርት አትማሪም ወይስ ?…»
«ትምህርት እንኳን እማር ነበር……… (ከትንሽ ዝምታ በኋላ…) አምና በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ አመት water engeneering ተማሪ ነበርኩያው እንዳልኩህ ከእናቴ ውጭ የሚረዳኝ ዘመድ ምናምን አልነበረኝም። እናቴም ከእድሜዋ ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ድካምና በሽታዎች ስለተጋለጠች ይሄን ከማድረግ ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም።»

«ትምርትሽ ላይ ያለሽ ውጤትስ እንዴት ነበር…»
«ሃይስኩል በነበርኩበት ወቅት ተሸላሚ ተማሪ ነበርኩ… (ከትንሽ ዝምታ በኋላ… )… ግቢ ከገባሁ በኋላ ግን ለኔም እስኪገርመኝ ድረስ ነበር ውጤቴ ያሽቆለቆለው…»

«ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ ? ምክንያት አለሽ
«እንግዲህ ምክኒያት ከተባለአስባለሁ፣ በተለይ የእናቴን ነገር ሳስብ በጣም እጨናነቅ ነበር፣ የሚገርምህ ላይብረሪ እያጠናሁ የነበርኩት ልጅ ራሴን ሆስፒታል አልጋላይ ያገኘሁባቸው ጊዜያቶች ሁሉ ነበሩበተደጋጋሚ ሌሊት ከእንቅልፌ ስባንን ስምረትን እያለቀሰች ነበር የማገኛት…»
«
ስምረት ? ማን ናት እሷ
«ስምረት እባላለሁ ብዬህም አልነበር ?… (ሳቅ……)
«ተጫዋች ልጅ ነሽ ስምረትታዲያ እንዴት ነው ስራሽ አይከብድሽም ? በተለይ በሴትነትሽ ምክንያት ብዙ የምትቸገሪ ይመስለኛልእናትሽስ በምን ሁኔታ ላይ ትገኛለች
«እግዚአብሄር ይመስገን እናቴ ቢያማትም የኔ ከሷ ጋር መሆን ብቻ ለሁለታችንም ትልቅ ነገር ነው። እንዳልከው ስራዬ በጣምና በጣም አስቸጋሪ ነውብዙ ታለቅሳለህ፣ ብዙ ታዝናለህ፣ ብዙ ብዙ ብነግርህ የማታምነኝ «ሰው ይሄን ያህል መጥፎ ነው ወይ» ሊያሰኙህ የሚችሉ አይነት ፈተናዎች ያጋጥሙኛልተሰድቤም ተተንኩሼም የሁለት ብር ቆሎ ከሸጥኩ «ሳይደግስ አይጣላም» እያልኩ ራሴን በማፅናናት ደሞ ወደሌለ ተሳዳቢ ሩጫ ነው…… (ብዙ ሳቅ…)
«እንደዚህም ሁኖ ደስተኛ ልጅ ትመስያለሽምን ይሆን ሚስጥሩ ስምረት?… እስኪ ከሚያጋጥሙሽ ነገሮች አንድ ሁለቱን አጫውችን
«ደስተኛ ነኝሁሌም ከኔ በታች የሆኑ ሰዎችን ሳገኝ ራሴን አፅናናለሁ፣ ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ ራሴን ላለማጨናነቅ እጥራለሁያው እንዳልኩህ በስራዬ አማካኝነት ብዙ ፈተናዎች ይገጥሙኛልማንሳቱ አስፈላጊ ባይሆንም ካልከኝ አይቀር ግን አንዱን ላጫውትህሃይስኩል አብረውኝ ይማሩ የነበሩ ሁለት ጓደኞች አሉኝማርታ እና ትግስት ይባላሉ። እነዚህ ልጆች የአስራ ሁለተኛ ክፍል የመልቀቂያ ውጤት ስላልመጣላቸው፣ እኔ ወደ ዩኒቨርሲቲ ስገባ እነሱም «አብረን ስራ ነገር እንሞክር» ተባብለው እንደቡና ቤት ነገር ከፈቱእኔም ሁለተኛው አመት ላይ ትምርቴን ትቼ ስመጣ እነሱም ጥሩ እየተንቀሳቀሱ በሚገርም ሁኔታ ከተማው አካባቢ ትልቅ ቤት ተከራይተው ምግብም መጠጥም በመሸጥ ገበያቸው ደርቷል። ቤተሰቦቻቸውንም በጥሩ ሁኔታ ይረዳሉ። ወዲያውም ይሄን ስራ (ቆሎ መሸጥ) ስጀምር ሌላ አማራጭ አቀረቡልኝይሄም «ቆሎ በመሸጥ የምታተርፊውን ያህል እኛ እንከፍልሻን እኛ ጋር ስሪ» የሚል ነበር
እኔም ይሄን ነገር ለእናቴ ሳማክራት እሽ አላለችኝም… «የምትጨነቂው ለኔ ብለሽ ከሆነ፣ ትምርትሽን ያቆምሽው የኔ ነገር አሳስቦሽ ከሆነ በፍፁም እንደዚህ አይነት ቦታ እንድትገቢብኝ አልፈልግም።» ብላ ከለከለችኝ፣ ጓደኞቼም እቤታችን ድረስ መጠው ለመኗትበጭራሽ አልተስማማችም !!
እነሱ ግን አሁንም እኔን ለመርዳት ስለሚፈልጉ አልተውኝምእኔም ያለእናቴ ፈቃድ ምንም ነገርእንደማላደርግ ቁርጥ አድርጌ ስነግራቸው የማዘጋጀውን ቆሎ በሙሉ የሚረከበኝ ሰው እንዳገኙልኝናምሽት ምሽት ላይ መስሪያ (ምግብና መጠጥ) ቤታቸው ድረስ እየሄድኩ እንዳደርስላቸው አዘውኝ ይሄን ማድረግ ጀመርኩ። ይሄ ነገር በምሽት መሆኑና ቆሎውን አድርሼ ስመለስ ጨለምለም ስለሚል መጥፎ ነገር እንዳያጋጥመኝ የፈራችው እናቴ ነገሩ ሁሉ እንዳልጣማት እና እንደውም እሷው እየሄደች ቆሎውን ማድረስ እንደምትፈልግ ጠየቀችኝ… (ፈዛዛ ፈገግታ…)
«የእውነት ማዘን ወይስ መሳቅየቱን እንደምመርጥ ግራ ገብቶኛልእባክሽን ጨዋታሽን ቀጥይ ስምረት…»
«እኔም የእናቴ ፍራቻ ቢገባኝም እንኳን ምንም የሚያስፈራ ነገር ባለመኖሩ ሃሳቧን ችላ ብዬ ስራዬን ቀጠልኩበአስራ አምስተኛው ምሽት ይመስለኛል እንደልማዴ ቆሎውን  አድርሼላቸው በስራም ትንሽ ረድቻቸው ተጨዋውተን መሸት ስላለብኝ ወደቤት ልሄድ ስነሳ ትግስት የተባለቸው አንድኛዋ ጓደኛዬ የምታሳየኝ ነገር እንዳለና እንድከተላት ነግራኝ ወደውስጥ ገባች
እኔም ተከትያት ሂጀ የአንዳንድ እቃዎች ማስቀመጫና መኝታ ቤት ነገር የሚመስል ክፍል ገባንየትህርቴ ነገር ሁሌም እንደሚያብሰለስለኝ ሁሌም ስለማጫውታት የሆነ ደስተኛ በሚመስል አነጋገር ትምህርቴን መቀጠል የምችልበት አጋጣሚ እንዳመቻቸችልኝየእናቴም ነገር በፍፁም እንደማያሰጋኝ ነግራኝ «መጣሁ ጠብቂኝ» ብላ ከክፍሉ ወጣችከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ ግን የመጣው ሌላ በሃምሳዎቹ ውስጥ ያለና ከዚህ በፊትም የማውቀው፣ በተደጋጋሚ ብዙ ብዙ ቆሎ የሚገዛኝና ሊያናግረኝ ይፈልግ የነበረ ሰውዬ ነበር
ሰውዬውን እፈራዋለሁሰዓቱም ስለመሸ በጣም ደንግጬ ተስፈንጥሬ በመነሳት ወደኋላ ለመሸሽ ሞከርኩሰውዬው ግን ፍፁም በተረጋጋ መንፈስ ሁኖ «አይዞሽ አትደንግጭ ሳምሪስላንቺ ብዙ ነገር አጥንቻለሁታላቅ ሰው መሆን የምትችይ ሴት ነሽቅር ካላለሽ ተቀመጭና እናውራ፣» ብሎ ተቀመጠ። ሲቀመጥ በሩንም ክፍት አድርጎ ስለነበርና አነጋገሩም ረጋ ያለ ስለሆነ ፍርሃቴ በመጠኑም ቢሆን የተወገደልኝ ቢመስለኝም አብሬው ለመቀመጥ አልደፈርኩም…! «መሄጃዬ ሰዓት አልፏል፣ ሰፈሬም ሩቅ ነውይመሽብኛል፣ እናቴ ደሞእናቴ ብቻዋን …» አልኩት እግሬ መቆም እያቃተው፣ ከዚህ ጉድ ለመውጣት ይረዱኛል ያልኳቸውን ምክኒያቶች እየዘረዘርኩና የቱን ማስቀደም እንዳለብኝ ግራ ገብቶኝዝብርቅርቄ ወጧል…!
«በፍፁም አይመሽም፣ የምናወራው ለአምስት ደቂቃ ያህል ነውደሞም በመኪናዬ እሸኝሻለሁ…» አለ ተቀምጦ አጆቹን እያሻሸ ቀና ብሎ እያየኝ።
«በመኪናዬ» ሲለኝ የሆነ ቅፍፍፍ አለኝ… «አይ በቃ ማውራት ካለብንም ነገ ይሻላል። አሁን እዚህ መሆን አልችልም። በጣም እየፈራሁ ነውነገ እናውራ?…ይሄን እያልኩት
ለራሴ «በቃ አለቀልኝ እንግዲህ» እያልኩ ወደተከፈተው በር በቀስታ ስራመድ ቀደም ብሎ በሩን ዘጋና ፊት ለፊቴ ቆመታውቃለህ…? በድንጋጤ «ስንጥቅ!!» ነው ያልኩት!!»
ከዛ ወዲያው ከአልጋው ስር አነስ ያለ ማዳበሪያ አወጣና «ተመልከቺ……ይሄን ሁሉ ቆሎ የምገዛሽ እኔ ነኝ እሽ…» አለ ጆንያውን ዘቅዝቆ ቆሎውን እየዘረገፈ
«ትንሽ እንኳን አላሳዝንሽም ?… ስንት ጊዜ ላናግርሽ ሞከርኩ ጭራሽ ፈቃደኛ አልሆንሽምአሁን ግን በቃኝ፣ አንች ስታዝኚልኝ ብቻና ብቻ ነው እኔም ላዝንልሽ የምችለው…» እያለ ተጠጋኝ። ምንም ማለት ስላልቻልኩ እየተርበተበትኩ ወደኋላ መሸሽ.. ሸሸሁትሸሽቼ ከግድግዳው ማለፍ አልቻልኩምና በጀርባየ ተለጥፌ አይን አይኑን እያየሁ ሊያደርግ የሚችለውን ነገር ማሰብ ጀመርኩ፣ እንባዬ ፊቱን እንዳላይ ጋርዶኛል።
«እኔ ከሌላው ሰው በምን እለያለሁ ?… የምትፈልጊው ብር ነው፣ የተጠየኩትን ያህል ገንዘብም ለጓደኞችሽ ሰጥቻለሁላንች ክፈል ያሉኝን ገንዘብኮ ብፈልግ አስር ሴት እገዛበታለሁእኔ ግን በቃ ማንነትሽ ስለማረከኝ…»
ከዚህ በላይ መስማት አልቻልኩምበቆምኩበት ደርቂያለሁ፣ ብቻ ከእንቅልፌ ስነቃ ያየሁት በለቅሶ ብዛት የቀላውን የእናቴን አይን ነበርከዛ ነጭ ግድግዳአልጋሆስፒታል
ነው ያለሁት/ሰፈራችን ውስጥ ያለ አነስተኛ ሆስፒታል/
«ምን ሁኘ ነው እመዬአልኳት ገና አይኔን እንደገለጥኩ «ልጄ፣ ልጄ፣ ልጄ» ብላ እያለቀሰች ስታቅፈኝ ግራ ገብቶኝ… «አንቺማ ምን ትሆኛለሽ፣ እኔው ነኝ የሞትኩት፣ እኔው ነኝ እኔው ነኝእናቴ ዝም ልትልልኝ ስላልቻለች ከሷ ብሼ እዬዬየን አስነካሁት እልሃለውበስመዓብተወው ያን ነገር ማስታወስ ራሱ እንዴት ይከብዳል መሰለህበመቀጠል ያወኩት ነገር
ቢኖርወደክፍሉ ይዛኝ የሄደችው ትግስት እየተጣደፈች መጣ በመቆፍቆፍ የእናቴን መምጣት የነገረችው ሰውዬ ደንግጦ ጥሎኝ እንደሄደ ነበር…… እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን !!»
 (
ይሄንንሁሉ ስታጫውተኝ እምባዋ እየወረደ ነበርከብዙ ዝምታ በኋላ ጥያቄየን ቀጠልኩ…)
«ቃለመጠይቅ ላደርግልሽ የተነሳሁትም ይሄንኑ ታሪክሽን አንድ ሰው ስላጫወተኝ ነበርይሄን ያህል ውስብስብ መሆኑን አላወኩም ነበርእንኳን አላህ አተረፈሽ!!… ታዲያ ከዛ ታሪክ በኋላ «ስምረትን» ምን አልሻት…(ስምረት እሷው ነች
«ከዛ በኋላ ትምህርቴን የምቀጥልበትን ሁኔታ ማፈላለግ እንዳለብኝ ነበር የወሰንኩትበዚህ ሁኔታ ከቀጠልኩ ወደፊትም ከዚህ የከፋ ነገር ሊገጥመኝ እንደሚችልእነዚህን ፈተናዎች መጋፈጥ ደግሞ ለሴት ልጅ ቀላል ነገር አይደለም። ለስምረትም ይሄንኑ ነው ያልኳት…»
«እና ይሳካ ይሆን
«እግዚአብሄር ይመስገን፣ አዎ እየተሳከ ይመስላል።»
«እስኪ አብራሪልን ስምረት…»
«ይኸው የነገርኩህ አደጋ ተከሰቶ ከተረፍኩ በኋላ ሁለቱ ሴት ጓደኞቼም አደጋ ሊያደርሱብኝ የነበረው ውዬም ለህግ ቀርበው እንደነገሩ አመት እንኳን ያልሞላ ፍርድ ተፈረደላቸውበተለይ ሰውዬው ወዲያው ነበር በብር ዋስ የተለቀቀውጥሩነቱ አደጋውን ምክንያት አድርጎ ያስተምሩኝ የነበሩ የሃይስኩል መምህራን በየወሩ ከደሞዛቸው እየቆረጡ ሊያስተምሩኝ፣ እናቴንም ከኔ ጋር በደንብ እንግባባና፣ አይዞሽ እያለ ያበረታታኝ የነበረ የፊዚክስ መምህሬ እኔ ትምህርቴን እስከምጨርስ ድረስ ከቤተሰቦቹ ጋር ሊያኖራት ቃል ገብቶልኛል።»
«አይዞሽኢንሻ አላህ ከዚህ በኋላ እኛም ከጎንሽ ነን»
«እግዚአብሄር ይስጥልኝ፣ በወጣ ይተካ ብያለሁ (ፈገግታ…)
ይሄን ፎቶ መቸ ነበር የተነሳሽውበዚህ እድሜሽ ዩኒቨርሲቲ መግባትሽ ሰዎችን ያስገረመበት አጋጣሚ የለም
«አዎ ብዙ ሰዎች ይጠይቁኛል። ያው ከታች ክፍል በተከታታይ ዳብል አልፌ ስለነበር ነው። ባጠቃላይ ሦስት አመት አትርፊያለሁ… ( ፈገግታ…) ፎቶውን የተነሳሁት ባጋጣሚ መንገድ ላይ ነው። የማላውቀው ልጅ ነው ያነሳኝ፣ አምና ከዩኒቨርሲቲ መጥቼ ይሄንኑ ቆሎ
መሸጥ እንደጀመርኩ አካባቢ ነበርእንደዛሬው ሳልጠቁር ማለት ነው። (ፈገግታ…)»
«ይሄ ፎቶሽ በብዙ ሚዲያዎች ላይ ተወዳጅ ሁኗል፣ ገጣሚዎች ተቀኝተውበታል፣ ፀሃፊዎች ብዙ መልዕክት አስተላልፈውበታል፣ በቅርቡ እንኳን «ፌስቡክ» ላይ አንድ «Strong African Girls» የሚል ድረገፅ ለቆት ከስምንት ሚሊየን በላይ አስተያየቶች ተበርክተውልሻልባንቺ ፎቶ ምክኒያትም በጣም ብዙ አዲስ ደንበኞች እንዳፈራ ፅፏልአንች ግን አሁንም ችግር ውስጥ ነሽምን አስተያየት አለሽ
«አደራህን ፎቶየን ለለቀቀው ሰው «ግማሽ ግማሽ እንካፈል» ብላሃለሽ በልልኝ ( ሳቅ…) ይገርማልስለፌስቡክ ብዙ የማውቅ አይደለሁም። ይሄን ያህል ህዝብ የኔን ምስል ማየቱ ብቻ ለኔ ትልቅ ነገር ነው። እንግዲህ ድጋፋቸው ወደምድር ቢወርድና ስምንት ሚሊዮኑ ህዝብ የአንድ የአንድ ብር ቆሎ ቢገዛኝ እስበው…… (ረዥም ሳቅ
«ወደፊት ምን መሆንን ትመኛለሽ…»
«በተማርኩበት የትምርት ዘርፍ ውጤታማ እንደምሆን አምናለሁ። እርግጠኛም ነኝ። ያኔ ለሰዎች
በተለይ ለሴቶች ደራሽ፣ አለኝታ፣ ደጋፊ መሆን ነው የኔ ምኞት»
«በተጨማሪ አንችን መርዳት የሚፈልጉ ሰዎች አሉእንዴት ሊያገኙሽ ይችላሉ
«እግዚአብሄር ይመስገንእኔ አሁን እርዳታ የሚያስፈልገኝ ሴት አይደለሁም። ያው እንዳልኩህ መምህሮቼ ቃል በገቡልኝ መሰረት ቀጣይ አመት ትምርቴን እጀምራለሁነገር ግን
እናንተ አሰባስባችሁ የምትረዷቸው ደካማ ልጆች (ተማሪዎች) እንዳሉ ነግረኽኛልእኔንም ከማህበራችሁ ብትቀላቅሉኝ የቻልኩትን ልረዳ እችላለሁእኔን ለመርዳት የሚፈልጉ ሰዎችም ከኔ በላይ ለተቸገሩት ለነዚህ ልጆች የቻሉትን ነገር ቢያደርጉ መልካም ነው እላለሁ። ብዙ ጊዜ
የኛ ሰው መጀመሪያ ላሰበው፣ ላየው ነገር ብቻ ነው የሆነ ነገር ማድረግ
የሚፈልገው። እኔን ተቸግሬ ስላዩኝ፣ እድል ገጥሞኝ ባንተ በኩል ችግሬን
ስለነገርኳቸው ብዙዎቹ ከሃገር ውጭም ከሃገር ውስጥም ያሉ ወንድም እህቶቼ ሊረዱኝ ፈልገዋልአሁንም እኔ ሁኔታዎች ልለተመቻቹልኝ አይተው ሃሳባቸውን ሳይቀይሩ ለፍተውም ካገኙት ገንዘብ ትንሽምብትሆን ለነዚሁ ከኔ በላይ እርዳታ ለሚፈልጉ ልጆች ቢሰጡልኝ የተሰበረ
ልቤን እንደጠገኑ እቆጥራለሁ።»
«እሽ እህታችን ስምረትበመጨረሻ ማስተላለፍ የምትፈልጊው መልዕክት ካለ ዕድሉን ልስጥሽ…»

«
መልዕክቴ በቀጥታ ወጣቱን ይመለከታልበተለይ እኔ በምንቀሳቀስበት አካባቢ የማያቸው ወጣቶች ሁሉ ማለት እችላለሁ መዋያቸው ጫት ቤት ነው። ከሁሉ ደግሞ የሚያበግነኝ አልፎ አልፎ የማያቸው ሴቶችበስራቸው አጋጣሚ «ደንበኛ ለመሳብ» በሚል ምክኒያት ጉንጫቸውን በጫት ጎጥረው ስመለከት ውስጤ ይሰበራልየሴትነትን ክብር ከላያቸው ሳጣ ሰው የመሆኔ ትርጉም ይጠፋብኛል። ልረዳቸው ባለመቻሌ አዝናለሁ !! እንዳልፈርድባቸው ደግሞ የገንዘብን ችግር ጠንቅቄ አውቃለሁእንኳን ይሄን ሌላ ብዙ ነገር ውስጥ ያደርሳል፣ ግን ምንም ያህል ችግር ውስጥ እንግባ ከራሳችን ከነፍሳችን በላይ የሚበልጥ ምንም የለም። የወንዱን ነገር ተወው… «እከሌ ጫት አይቅምም» ነው የሚባለው ማለት ሌላው ሰው ሁሉ ሲያነፍጨው የሚውለው ያንኑ ማንነትን አሻምዶ ባዶ የሚያስቀር መርዛማ ቅጠል ነው። ይሄ እንግዲህ ይሄን ቆሎና ለውዝ በምሸጥበት አጋጣሚ የማየው ነውከዛ ውጭ ደግሞ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ፣ ማታ መገኛቸው የት እንደሆነ መገመት ቀላል ነው። መልዕክቴም ይኸው ነው። «እባካችሁ ወጣቶችራሳችንን ዞር ብለን እንመልከትከኛ በላይ ጠንካራ፣ ከኛ በላይ ማንኛውንም ነገር ለማድረግ በቂ ጉልበት ያለው የለም። ሱሳም መሆን ማለት በጣም ቀላልና ማንም ተራ ሰው ሊያደርገው የሚችል ማስጠያ ነገር ነው። ከባዱ ነገር ከሱስ መውጣት ነው። ከባዱ ነገር «ቤተሰቦቼ ከኔ ምን ይጠብቃሉ፣ እናቴ ምን እንድሆን ነበር የምትመኝልኝ ? ምን ደረጃ ላይ ብደርስ ነው ለሰዎች ምሳሌ፣ ለቤተሰቦቼ ኩራት መሆን የምችለውብሎ ሲያስብና ሲያስብ ብቻ ነውሰላም !!
*ስምረትን  ይህን ቃለመጠይቅ ያደረኩላት በ  2002 ነበር። ያቋረጠችውን ትምህርቷን በ 2003 · ወሎ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ  ቀጠለች…!! 
ከዚያስ ቀጣይ ህይወቷ ምን ይሆን? ትምህርቷን ጨረሰች ወይስ?  አሁን የት ናት? ምን እየሰራች ነው?          ……..ቀጣዩን  ክፍል ይጠብቁ 

                              ይቀጥላል…………
       © ፎቶ_From Remzi Akibaw facebook page

No comments:

Post a Comment