Friday, April 19, 2013

አዎን እኖራለሁ





ምላሴን ሲመረኝ በጨው እያጣፈጥሁ
ክፉውን ስሰማ በጎውን እያሰብሁ
ንዴት ሲያቃጥለኝ ሻወር እየወሰድሁ
ቀን ያለፋል እያልሁኝ ቀናት እየቆጠርሁ
        እንዲህ እጓዛለሁ
        እንዲህ እኖራለሁ
ህሊናየን ትቼ ለስጋ እያደላሁ
ነፃነቴን ትቸ ሆዴን እየሞላሁ