(ፀሐፊ፡ ጦቢያ ዓለም): Tobyaalem@gamil.com
እኔ ጦቢያ ተነሳሁ! አለከልካለሁ፡፡ ድክም ብሎኛል፡፡ የሆነ ዳገት እየወጣሁ…የሆነ ትልቅ ተራራ ላይ እየዳሁ ያለሁ ይመስለኛል፡፡ ደግሞ በህልም ወይንም በቅዥት ውስጥ ያለሁም ይመስለኛል፡፡ ጉዋደኛየ ይጠራኛል….አቤት…..ና….ምን?….ከደቂቃዎች
በፊት ወደ አንድ ያ'ጥንት ህክምና ተቋም እንደ ወሰደኝ አስታውሳለሁ፡፡ እንዴውም በጣም የሚያምረውን የተቋሙን ወለለ ስረግጥ አድጦኝ ወድቄ ዲስኬ እንዳይንሸራተት እያልሁ በፍርሀት በጥፍሬ እየቆነጠጥሁ (ደግሞ ጥፍሬ ለጉድ ነው..ለዚህ አጋጣሚ ተብሎ የተሰራ መሰለኝና…ዝቅ ብየ አየሁት) ደረጃዎቹን እንደ ወጣሁ አልረሳም፡፡ አንተ ጦቢያ…ጦቢያ…ጦቢያ አለም፡፡ አልሰማው ስል የናቴን ሰም ጨመረው፤ አለም፡፡ በጣም ስለምወዳት አሻፈረኝ ብዬ በናቴ ስም ነው የምጠራው፡፡ የናቴ ስም ሲጠራ ሞቼ ራሱ ምነሳ ይመስለኛል፡፡ አቤት ብየ ብድግ አልሁ…….የሆነ ጫጫታ ተሰማኝ፡፡
አይኔን ስገልጥ ደግሞ የህዝብ ትርምስ አየሁ…. የገበያ አዳራሽ ውስጥ ማን አመጣኝ?…..በእውኔ ጉዋደኛየ እጄን ይዞ ወደ ትርምሱ መሀል ወሰደኝ፡፡ አንድ ዲስኩ ተንሸራቶበት ቀዶ ጥገና የተደረገለት ሰው አልጋ ክፍሉን አልለቅም….እልወጣም ብሏቸው የተፈጠረ ትርምስ አንደሆነ ሰማሁ….(ዲስኬን ዳበስኋት ደህና ናት…ኦፍ ተገላገልሁ)
“ዉጡልኝ….ልቀቁ
ክፍሉን…..ቤታችሁ አደረጋችሁት እኮ…..”
“በድንብ አላገገመም! ወጠንስ የት! መንቀሳቀስ የማይችል ሰው ይዤ…፡፡ ገንዘብም በእጄ የለ….” ማገገሚያ ቤት የሚል ታፔላ የተለጠፈባቸው ተቋማት ናፈቁኝ …..ዞሬ ለመፈለግ ስል የብሎኬት አጥር ውስጥ መሆኔን ተረዳሁ፡፡
“አላውቅልህም
ትወጣለህ ትወጣለህ…..አንተ ገንዘብ ስላለህ…ዘላለም ልትተኛ ..…ሌላው በሽተኛስ….”
“ሰውነቱን አላፍታታም… ደግሞም የሰራለት ሀኪም እንዳትንቀሳቀስ ብሎታል….”
“መንቀሳቀስ
ይችላል…”
“የሰራለት ሀኪም እኮ ከ አንድ ወር በፊት በዊልቸር እንኳ መንቀሳቀስ እንዳትሞክር ብሎታል….”
“አሁኑኑ
ውሰደው……ሲገባም ይህንን በደንብ ተረድቶ ነው የገባው….አሳይኃለሁ ፈርሟል….”
ጠቅላላ ሀኪሙ ነርሷና የተቋሙ ባለቤት ሆነው አስታማሚውን ያናውዙታል፡፡ ታካሚው አልጋ ላይ ነበር፡፡
ዛሬ ጆሮየ እየሰማ ታዛቢ አድርጎኛል፡፡ ስሰማቸው ስሰማቸው….. እይሰማሙም….አይስማሙም ፡፡
እኔ ግን ትዝብቴን አስቀምጣለሁ፡፡
ጠቅላላ ሀኪም ሰው አልመስልህ አለኝ›››››› ከቁጣው የተነሳ
አውሬ ሆኗል፡፡ የማንንም ሰው ድምጽ ሲሰማ ይናከሳል፡፡ ጉዳዩን ለማለሳለስ ሳናግረው ደንግጨ ወደ ኋላ ነው የተንደረደርሁት እንጀራ ምነክስበትን አፌን ቢነክስብኝ (ደግሞ ከሴቶች ጋር ሊያቆራርጠኝ…ፑፍ! ወንድ አያውቅም! ለዚህማ
እንጋደላለን!) ….እ….ሆዴ
በምኗ ልትሞላ…..ሆዴ ጎደለች ማለት ደግሞ ይች ቀፎ ሰውነቴ ወደቀች፡፡ አይ ሰው!….ሰው እኮ ሰው የሆነው ባፉ ነው……አስባችሁታል፡፡ ከአፍ...ከሆድ በላይ ለሰው ምን ዋስትና አለው፡፡ እንደ ተቆረጠ ቅጠል ወዲያው ነው ሚደርቀው… እንኳም ተጀመረ፡፡ ተመስገን ተመስገን ጨረቃውን መንግስታችንን ያኑርልን..እርሱ አይደል ይህን ያመጣው……እህሳ….መጀመሪያ ላ'ፌ …ከዛ ለሆዴ ነው ኢንሹራንስ ምገባው፡፡ ኢንሹራንሽ እስክገባላት ድረስ…. እንደ ምንም
ተፍገምግሜ አተረፍኳት፡፡ ግን እርሱን ማስረዳት ተራራ መውጣት መሰለኝ፡፡ ደከመኝና ተውኩት….ድምጤን ቆጥቤ ጉልበት ሚጠይቅ ስላልመሰለኝ በዝምታ ማሰብ ጀመርሁ፡፡
አስታማሚው ከዚህ በኋላ ሰውነቱ የተቆረጠውን ሰው ምን ማድረግ እንደሚገባው አያውቁም፡፡….ይዘለው….በሩቡላ…በመኪና….እንዴት አድርጎ….ምን ማድረግ አለበት…ምንስ አለማድረግ? ስነ ልቦናስ?…… ስለዚህ አልወጣም አለ፡፡
እያለከለክሁ ማሰቤን ቀጠልሁ… እዚህ ያሉ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ አንድ ነገር ይጎድላቸዋል፡፡ የጤና ምክር አግልግሎት አሰጣጥ እውቀት (Clinical counseling knowledge)፡፡
እኔ የደከምሁት ላንድ ሰው ይህን ለማስተማር ነው፡፡ እድሜ ይስጠውና ነርሲንግ ዲፒሎማ ስማር ኮርስ ያስተማረኝ
መምህር ግሩም ነው፡፡ ወንድ! (ሴቶች ሁሉ አ ብለው ይሰሙት ስለነበረ ነው)፣ ማለቴ ሰው! (ሰውማ ሁሉም ሰው ነው)፣ ማለቴ መምህር! (ማንም እርሱን አይመስልምና) …ብሎ ዝም፡፡ የጤና ምክር አግልግሎት ምን እንደሆነ በተግባር ነው ያስተማረን፡፡ እናማ ትንሽ እውቀት … ነበረችኝና..… እዚህ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ግን የእኔን ያህል…. ኧረ በጭራሽ፡፡
ያደከመኝ ዳገት ይህ መሰለኝ፡፡ እነዚህን ሰዎች በምክር አግልግሎት ማብቃት…እንኳንስ ዲስኩ ተንሸራቶ በህምክና ሽባ የሆነን ሰው ይቅርና…ማንኛውም ታካሚ የሙያውን ስነምግባር ያማከለ የምክር አገልግት ያስፈልገዋል፡፡ ሀገሬን ሳስባት ያደከመኝ ይህ ነው….. ይህን
ሁሉ የጤና ባለሙያ በዚህ ደረጃ ማሳለፍ፣ ማብቃት…እ…ሁሉም እንደዚህ ነው እንዳትለኝ?....የእነዚህን ባለሙያዎች
አፍ ስሰማ ግን ድፍን ጦቢያ ያው መስላ ታየችኝ….የሙያውን ስነ-ምግባር የተላበሰ የምክር አገልግሎት የትማ ያለ አይመስለኝም…..የትም፡፡ ለዛም ነው የደከምሁት›››› ኧረ ሌላ
አጋጣሚ አንድ ቀን የግል ክሊኒክ ገባሁ…..መዓት ምርመራ(ላቦራቶሪ) ታዘዘልኝ›››› ጌታዬ ይህ
ሁሉ ምንድን ነው? ማለቴ ለምን ለምን ያግዘኛል….. አልሁት (የተባለ ቡጨቅጫቂ ወረቀት እያገለባበጥሁ) ቀና ብሎ እጄ አካባቢ አየኝና…….በእጁ ያለን አንድ ደብተር አንስቶ እንደዚህ አይነት ደብተር ግዛና ወለጋ ዩኒቨርስቲ ገብተህ ተማር አለኝ፡፡ ይሄውና የምክር አግልግሎት!….እውቀት ማነስ ይሉኃል!››› ለካ እጄን
እጄን ሲያይ የነበረው….. ባዶ….ውን ሊሞላ ነበር፡፡ ይታያችሁ
በእጄ ከያዝሁት መጽሄት አርማ አይቶ ነው፡፡ ወለጋ ዩንቨርሲቲ የሚለውን የነገረኝ፡፡ የደከመኝ ይህንንም ሳስታውስ ነው›› ጦቢያውያን ድኃ ታካሚዎች ባለችው ድህነታቸው ላይ የስንቱን ባዶ…. ሞልተው ይችላሉ፡፡ ይህን ሳስበው ነው የማለከልከው›› ሁላችንም ድሆች ነን›› የገንዘብ ድሆች…..የእውቀት ድሆች››› የአመለካከት ድሆች››› የመልካም ስነምግባር ድሆች››……
አንድ የገጠር ሽማግሌ… ባልሰሳት ካለባበሱ ከጎጃም የመጣ ይመሰለኛል››.. እህ….በመጥረጊያ ነበር አለኝ…
ምን?
እልሁት
ሁሉንም በመጥረጊያ ነበር…..ሲል መለሰ፡፡ ሰውየውን ፈራሁት፡፡ ሁሉንም ሲል እኔንም ጨምሮኛላ….ሚጠርገኝ መሰለኝ፡፡ በምን ቀን ነው ጤና የተማርሁት… ያውም ዲፒሎማ እኮ ነው… በዚህችም ልጠረግ እንዴ…. ቢያንስ ላረጋጋው አልሁና ፈገግ አልሁለት፡፡ እርሱም ደስ አለው፡፡ ያሸነፍሁት ያህል ተሰመኝ….. ስንቱን ጠርገን….ከዚያ ይልቅ ለምን ቀስ እያልን አናስተካክላቸውም አልሁት….እኔን ለማትረፍ ብየ የተናገርሁት እኔኑ አደከመኝ…..ቁሜ አለከለክሁ….ዳገት የምወጣ ያህል ተሰማኝ….የሆነ ተራራ ላይ የምድህም መሰለኝ›…ስንቱ ይቀናል ጎበዝ? የትኛውስ ይቀላል? የእያንዳንዱን ሰው የገንዘብ ድህነት ማጥፋት ወይንስ የእውቀት…. የባለሙያውን የሙያና ስነምግር ድህነቱን ማጥፋት ወይንስ ጠብ ለማይል ነገር ደግሞ ደጋግሞ ለማስተማር ማውጣት? የእያንዳንዳችንን 'ያመላካከት ድህነትን መሙላት ወይንስ….ጆሯችን ሮሮ እንዳይሰማ ቡትቶ መሙላት?..... ይህን ሁሉ
ለመሙላት ትልልቅ ተራራ ተራራ የሚያክል
ድንጋይ የተሸከምሁ ያህል ተሰማኝና ማረፍ ፈለግሁ……ሳልሰራ በሀሳብ ብቻ ደከምሁ…….
እኔ ጦቢያ እንደተነሳሁ ተመልሸ
ተቀመጥሁ! ደክሞኛል ልረፍበት! ቻው እያንዳንድሽ!
ሐምሌ 02፣ 2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ
No comments:
Post a Comment