‹‹ ሳይማር ያስተማረና ሳይተርፈው የደገሰ ትርፉ ፀፀት ነው››
መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
ሰሞኑን የማህበራዊ ሚዲያዎች ‹‹ጋሽ በጋሻው ለምዱን ገፎ በገሃድ ኦርቶዶክስ ይደለሁም አለ››…….አንዳንዶች ደግሞ ‹‹እምነት የለኝም አለ››፣ ሌሎች ደግሞ ‹‹ፕሮቴስታንት ነኝ አለ›› ይላሉ፡፡ ነገ ደግሞ ይህ ሰውዬ ‹‹ሰው አይደለሁም›› ብሎ እንዳይመጣ እፈራለሁ፡፡
አንድ ሰው የየትኛውም እምነትና ሐይማኖት (ሁለቱ የተለያዩ ናቸው) አማኝና ተከታይ ከመሆኑ በፊት ሰው መሆን አለበት፡፡ አንድ ሰው ‹‹ሰውነት››ን ከተላበሰ ያውም በሐይማኖት ስም ለብዙዎች መሰናከያና መወናበጃ ምክንያት መሆን የለበትም፡፡ የሚያምንበትን ነገር ከስር መሰረቱ ግልፅ አድርጎ የፈለገውን ሃይማኖት መከተል መብቱ ነው፡፡ በሌሎች ጓዳ እየገቡ መፈትፈት ግን ኢሞራላዊ ነው፡፡
በ እርግጥ የጋሽ በጋሻው ‹ዳያሪ› ሲገለፅ የምናነበው ከ አንድ ሰባኪ ነኝ ከሚል አይደለም ከ አንድ ተራ ግለሰብ የማይጠበቅ በጣም አሳፋሪ ስራ ነው፡፡
በ እርግጥ የጋሽ በጋሻው ‹ዳያሪ› ሲገለፅ የምናነበው ከ አንድ ሰባኪ ነኝ ከሚል አይደለም ከ አንድ ተራ ግለሰብ የማይጠበቅ በጣም አሳፋሪ ስራ ነው፡፡
ጋሽ በጋሻው ገና በጥዋቱ ከመምህራን ጋር በፈጠረው አተካራና የሚጠበቅበትን ውጤት ማጣት ባለመቻሉ ከ ኮሌጅ ተባረረ፡፡ ከስህተቱ ተመልሶ ይቅርታ ተይቆ ከመማር ይልቅ ‹‹ የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች›› የሚል መፅሃፍ ፅፎ ሁሉንም የ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች በወል ሰደበ፡፡ እኔም ይህን በስድብ የሞላ መፅኃፍ በ 1999 ዓ.ም አንብቤአለሁ፡፡ ከፍፁም ትህትናና እውቀት በራቀ መልኩ የተፃፈ መጽሃፍ ነበር፡፡ ከዚያም በጋሽው የወጣቱን ስነ ልቦና መስለብ በመቻሉ በታላላቅ ሊቃውንቶች ፊት ሳይቀር ቆሞ ማስተማር ጀመረ፡፡ በወቅቱ ያሳይ የነበረውን ኢሞራላዊ፣ ኢ ስነምግባራዊና ኢ ሃይማታዊ የሆነ ተግባር ተመልክቶ የእርምት እርምጃ መውሰድ አማኟ ነኝ የሚላት ቤተክርስቲያን ሃላፊነት ነበር፡፡ ጎንደርን ጨምሮ ብዙ ከተሞች ላይ ያሳይ የነበረው ተግባርና ስብከት አማኝ ላለመሆኑ ማሳያ ነበር፡፡ ጎንደር በአንድ የሊቃውንት መፍለቂያ አውደ ምህረት ሲያሰተምር የነበረው ስነምግባርና ከ ስብከት መልስ ማታ ላይ የተናረውን ንግግር (እዚህ ማንሳት አያስፈልግም) ከሰማሁ በኋላ ከእሱና ከመሰሎቹ እራሴን እንዳሸሸሁ ትዝ ይለኛል፡፡ በ እኔ የማመዛዘን ችሎታ እንኳ ይህ ቀን እንደሚመጣ እጠብቅ ነበር፡፡
እኔ እንደሚመስለኝ የዚህ ሰውዬ ትልቁ ችግር አለመማመሩ ነው፡፡ ይህ የእኔ ግምት ብቻ ሳይሆን ታላቁ የቤተክርስቲያን መምህር መጋቤ ሐዲስ እሸቱ፣ በጋሻውን በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው መክረውት ነበር ይባላል፡
‹‹ …….ስብከቱ ይቆይህ፡፡ አረፍህ ትምህርትህን ተማር፡፡ ዛሬ ቆሞ ያጨበጨበልህ ህዝብ፣ ነገ ማንነትህን ሲያውቅ ድንጋይ አንስቶ ይወግርሃል……….››
ያሉት አልቀረም በአንድ ወቅት ይህ ነገር ደርሶበት ነበር፡፡ ይባሳ ብሎ ሳይማር የመምህራንን ካባ በማጥለቅ ‹‹መጋቤ ሐዲስ›› የሚል ማዕረግ አጣፍቶ ከመምህሮቹ እኩል መጠራት ጀምሮ ነበር፡፡ እንግዲህ ‹‹ከመጠምጠም መማር ይቅደም›› የሚሉት አባቶች ወደው አይደለም፡፡ የ በጋሻው ዕጣ ፈንታም ከዚያ የተለየ አልሆነም፡፡
በ 2004 ዓ.ም አካባቢ ይመስለኛል ሰውየው ከብዙ አቅጣጫ ነቀፋ በዝቶበት ነበር፡፡ በዚሁም ፀፀት ውስጥ እንደገባ የሚያሳዩ መረጃዎች ወጠው ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ይመስለኛል ከላይ የጠቀስኋቸው አባት ለአንድ መፅሔት በሰጡት ቃለ መጠይቅ ‹‹ ሳይማር ያስተማረና ሳይተርፈው የደገሰ ትርፉ ፀፀት ነው›› ብለው የተናገሩትን ማበቤ ትዝ ይለኛል፡፡
ጋሽ በጋሻው ዙሪያ ጥምጥም ዞሮ ከጠቅላይ ቤተክህነት አጥር መዋል ከጀመረ (ዝርዝሩ አስፈላጊ አይመስለኝም) በኋላ የቤተክርሰቲያኗን ራስ ለመዘወር ከሚራወጡት ሰዎች መካከልም አንዱ ነበር፡፡ ያን አጋጣሚ ተጠቅሞም በማኅበረ ቅዱሳንና መሰል የቤተክርስቲያን ተቋማት ላይ ቀስት ሲወረውር እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡
ከዚህ አልፎም ታዋቂው የማህበረሰብ ፈላስፋ ካርል ማርክስ “ታሪክ ራሱን ደገመ፣ መጀመሪያ አሳዛኝ ቀጥሎ ቧልት በሚመስል መንገድ” ብሎ እንደተናገረው የሐውልቱ ስራ ላይ በነበረው ንቁ ተሳፎ ተፍ ተፍ በማለቱ ምክንያት ‹‹የሐውልቱ ስር ቁማርተኞች›› የሚል መፅሃፍም ‹‹ ፈታሒ በጽድቅ›› በተባሉ ሰው በራሱና በመሰሎቹ ላይ እንደተፃፈበት እናስታውሳለን፡፡
ስንሸበልለው፣ በጋሻው በማያምንበት እምነት ገብቶ ሲፈተፍት እያየች ቤተክርስቲያኗ ዝም ማለት አልነበረባትም፡፡ አሁንም ቢሆን አስፈላጊውን ቀኖናዊና ሐይማኖታዊ እንዲሁም የህግ እርምጃ መውሰድ አለባት ባይ ነኝ፡፡ በዚሁ አጋጣሚ መሰል ሰዎችና የሐይማኖት ድርጅቶችም በሌሎች ሐይማኖቶች ጣልቃ ሳይገቡና የሰውን መብትና ነፃነት ሳይነኩ የራሳቸውን ሃይማኖት ማምለክና ማስፋፋት ሰብዓዊና ሞራላዊ ነው፣ ይሄ ብቻ አይደለም ህገ መንግስታዊም ነው ብዬ አምናለሁ-አምኜም እናገራለሁ፡፡
selam zelalem. I am Andinet. I like your blog and I link your blog with my blog. check my blog at http://ethio28.blogspot.com/
ReplyDelete