በምስሉ የምትመለከቷት አስገራሚዋ እንስት ስምረት ይታይህ ትባላለች፡፡ ቃለ ምልልስ ያደረገላት ረምዚ አክባው የተባለ የማህበራዊ ድህረገፅ ጓደኛዬ ነው፡፡ ቃለ
ምልልሱ ከያዘው አጅግ አሳዛኝ፣ አስገራሚና አስተማሪ ታሪክ የተነሳ እሱን አስፈቅጀ በዚህ ገፅ ለጥፌዋለሁ፡፡ ረምዚ አክባውን በአንባቢያን ስም ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
ቃለ–ምልልሱ
ይቀጥላል….. መልካ ንባብ!!!
«እሽ እህታችን በመጀመሪያ ስምሽን ብታስተዋውቂን?…»
«ስምረት ይታይህ እባላለሁ!»
«እስኪ ካለን ሰዓት አንፃር ያሉትን ነገሮች አሳጥረን እናውራና… እንዴት ነው ስራ ? እንዴትስ ወደዚህ ስራ ልትገቢ ቻልሽ ?»
«ስራ ጥሩ ነው… ከጥሩነቱ በላይ ደግሞ ፈታኝ ነው። ወደዚህ ስራ የገባሁት ያው እናቴ ከኔ ውጭ ልጅም ሆነ ቤተሰብ ስላልነበራት ማንም የሚረዳት የለም… ለዛ ነው!( ፈገግታ…)»
«ማለት ከመቼ ጀምሮ ነው አንቺ የምታስተዳድሪያት ? ትምህርት አትማሪም ወይስ ?…»
«ማለት ከመቼ ጀምሮ ነው አንቺ የምታስተዳድሪያት ? ትምህርት አትማሪም ወይስ ?…»
«እ… ትምህርት እንኳን እማር ነበር……… (ከትንሽ ዝምታ በኋላ…) አምና በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ አመት water engeneering ተማሪ ነበርኩ… ያው እንዳልኩህ ከእናቴ ውጭ የሚረዳኝ ዘመድ ምናምን አልነበረኝም። እናቴም ከእድሜዋ ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ድካምና በሽታዎች ስለተጋለጠች ይሄን ከማድረግ ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም።»