በህልም ዓለም ጉዞ ታች ላይ እያልሁኝ
የቀኑ እሩጫየ እንቅልፍ አሳጥቶኝ
አንድ ጊዜ ሲያከብረኝ አንዴ ሲያደኸየኝ
በድንገት ስከብር ከእነቅልፌ ነቃሁኝ፤
ደግሜ እንደገና ከአልጋየ ጋደም ስል
ከማንቀላፋቴ
ታየኝ አንድ ምስል፤
አንድ የሃብታም ልጅ ከብር ላይ ተኝቶ
አይኖቹን ጣራው ላይ ወደላይ ሰክቶ
ላይ ታች ይባዝናል በሃሳብ ባዘቶ
ህሊና ሚያሳርፍ ሰላም እንቅልፍ አጥቶ፤
ሌላው
የኔ ቢጤ ከትቢያ ላይ ወድቆ
ግማሽ
አካላቱን በእራፊ ጨፍልቆ
ብርድና
ሙቀቱን ከምንም ሳይቆጥር
የሰላሙን
እነቅልፍ ተኝቶ ይነጫል፡፡
አሁን
ከዚህ መሃል የቱ ነው ደግ ነገር
የትኛው
ይሻላል ሳላም ነው ወይስ ብር
እያልሁኝ ለራሴ ነገር ስመረምር
ድንገት
ሰው ቀስቅሶኝ ከእንቅልፌ ብንን ስል
ለካስ
የኔም አካል ከትቢያ ላይ ነበር፡፡
No comments:
Post a Comment