(ፀሐፊ፡ ጦቢያ ዓለም): Tobyaalem@gamil.com
እኔ ጦቢያ ተነሳሁ! አለከልካለሁ፡፡ ድክም ብሎኛል፡፡ የሆነ ዳገት እየወጣሁ…የሆነ ትልቅ ተራራ ላይ እየዳሁ ያለሁ ይመስለኛል፡፡ ደግሞ በህልም ወይንም በቅዥት ውስጥ ያለሁም ይመስለኛል፡፡ ጉዋደኛየ ይጠራኛል….አቤት…..ና….ምን?….ከደቂቃዎች
በፊት ወደ አንድ ያ'ጥንት ህክምና ተቋም እንደ ወሰደኝ አስታውሳለሁ፡፡ እንዴውም በጣም የሚያምረውን የተቋሙን ወለለ ስረግጥ አድጦኝ ወድቄ ዲስኬ እንዳይንሸራተት እያልሁ በፍርሀት በጥፍሬ እየቆነጠጥሁ (ደግሞ ጥፍሬ ለጉድ ነው..ለዚህ አጋጣሚ ተብሎ የተሰራ መሰለኝና…ዝቅ ብየ አየሁት) ደረጃዎቹን እንደ ወጣሁ አልረሳም፡፡ አንተ ጦቢያ…ጦቢያ…ጦቢያ አለም፡፡ አልሰማው ስል የናቴን ሰም ጨመረው፤ አለም፡፡ በጣም ስለምወዳት አሻፈረኝ ብዬ በናቴ ስም ነው የምጠራው፡፡ የናቴ ስም ሲጠራ ሞቼ ራሱ ምነሳ ይመስለኛል፡፡ አቤት ብየ ብድግ አልሁ…….የሆነ ጫጫታ ተሰማኝ፡፡