ለፍቅርሽ ጥልቀት
ለ ሰብዕናሽ ምጥቀት፤
ብራና ዳምጬ
ቃላትን መርጬ
ብዕሬን ጨብጬ፤
በሰከነ መንፈስ~ልፅፍ
አስብና
ፈዝዠ እቀራለሁ~ሐሳብ
ሁሉ
መና
ማይጨበጥ ነፋስ~የቅዠት
ደመና
ግራ ይገባኛል~ምን
ላድርገው
ደግሞ
እምባዬ ይፈሳል~ከብዕሬ
ቀድሞ፤
ቃላትን ላጣምር~የያዝኩት
ወረቀት
ቀለም እና እምባ~በ
አንድ
ተዋህዶበት፤
ባህርን ይፈጥራል
መናኛ ሐሳቤም~ሰጥሞ
ይጠፋኛል፤
ባህሩን አስሼ
አድማስ አዳርሼ፤
በ አንካሳ ፊደላት~ቃላትን ልቆጥር
ስለ ፍቅርሽ ልፅፍ
ፍ…ብዬ
ስጀምር፤
ደግሞ ከ ወደ
ውስጥ~ቁጣ
ይሰማኛል
ብኩን ህሊናዬ~እንደዚህ
ይለኛል፤
“ምንስ ጠቢብ
ብትሆን~ፊደላት
ቢተርፉህ
ፍቅርን በቃላት~እንዴት
ትገልፃልህ?”
እያለ ይለኛል
ግራ ይገባኛል፤
ግን እኮ አንቺን…….
ግን እኮ አንቺን…….
ቃላት ባይገልፁትም~የፍቅርሽን
ጥልቀት
ልብሽ ባያውቀውም~የእምባዬን
እውነት
አንድ እውነት ልንገርሽ
ካዳመጠኝ ጆሮሽ?
ፀሐይ ብትጨልም~ከዋክብት
ቢረግፉ
የ ምድር ባህሮች~አፍላጋት
ቢነጥፉ
ሰማይ እና መሬት~በ
አንድ
ቢዋሃዱ
ከሰማይ ‘ሳት ወርዶ~ፍጥረታት
ቢነዱ
ተፈጥሮ ቢከዳኝ~ሁሉም
ቢቀያየር
በ ዘመን አይከስምም~ለ
አንቺ
ያለኝ
ፍቅር
(ለ አንቺ…. ታህሳስ 28 & የካቲት29፣ 2008 ዓ.ም)
(ሳይኖሩ ለልጆቻቸው
ለሚኖሩ
ውድ
የ
ዓለም
ጀግና
እናቶች
መታሰቢያ
ይሁንልኝ)
No comments:
Post a Comment