ስንዝር መቃብርህ~በቁም የተማሰው 
እባክህን ስማኝ 
አንድ ምክር አለኝ 
በነጋ በጠባ የሚወሰውሰኝ፤
በ አይሁዳውያን መሃል~ክርስቶስን ማግኘት
ልክ እንደ ጲላጦስ~ሰቃይ ፊት መዳኘት
እንደ አገሬ አርበኛ~ስለ እውነት መሞት
እንዲከብድ አውቃለሁ
ግን ደግሞ ወገኔ፡
አእምሮ ስላለህ
አንተም አንደሌላው~ስጋ ስለለበስህ
የሁሉን ቻይ ጀርባ~በገራፊዎች ግፍ
እንደ አቫዬ በሬ~ሳይደማ በ ጅራፍ 
ምስኪን ክርስቶስን~ከመስቀልህ በፊት 
ግዴለም አትቸኩል~ደግመህ አስብበት

 
 
No comments:
Post a Comment