Thursday, July 14, 2016

‹‹‹የ ኤደንብራው የሞት ጠላት›››


መሆንህን ቢያውቀው መከታ ሀገር
ህሙማን መሲህ ምሰሶና ማገር
ሞትማ ጨክኖ አይወስድህም ነበር
      (ዘላለም፣ 2008 .ም )
አንድ ትልቅ ዋርካ በስሩ ብዙ ነፍሳትን አስጠልሎ እንደኖረ ማን አስተውሎት ያውቃል፡፡ በቅርንጫፉ ያፈራቸው ፍሬዎችስ ለሌላ ዋርካ መሰረት እንደሆኑ ማን ይክዳል፡፡
ኢትዮጵያ በየ  ምህዳሩ ብዙ ዋርካዎች ነበሯት፣ አሏትም፡፡ ከነዚህ ቀደምት ዋርካዎች አንዱ ሸገር ተወልዶ፣ በረሃዋ ገነት ድሬዳዋ አቡጊዳ የቆጠረው፣ በኋላም ከተፈሪ መኮነን /ቤት እሰከ ግብፁ ቪክቶሪያ ኮሌጅ ቀጥሎም እስከ ታላቁ የእንግሊዙ ኤደንብራ ዩኒቨርሲቲ ብቃቱን ያስመሰከረው የሞት ጠላት ነው፡፡
ህፃንነቱ እናቱንና አባቱን የነጠቀውን ሞት ለመታገል የሞት መግቢያ ቀዳዳዎችን በዘመኑ ከነበሩ የኤደንብራ ጠበብቶች ከአንዴም ሁለቴ ተመላልሶ አጥንቷል፡፡ ከዚያም 40 አመታት ያክል ወላጆቹን የነጠቀው መላከ ሞት ጋር ሲታገል፣ የሺዎችን ህይወት ሲቀጥል ኖረ፡፡ 
ይህ ሰው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የቀዶ ጥገና ሐኪም / ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ነው፡፡
ሰለኒህ ታላቅ ሰው ከስም ባለፈ ስለ ማንነታቸው ለማወቅ የቻለሁት 2002 . ባነበብኩት አሰገድ መኮነን በተፃፈነፀብራቅበተሰኘ መፅሐፍ ነው፡፡ አሰግድ መጽሀፍ በዋናነት የሚያተኩረው በፖለቲካዊ ህይወታቸው ስላሳለፉት ውጣውረድ ቢሆንም ስለ ህክምና ሕይወታቸውም ቢሆን አልፎ አልፎ ይዳስሳል፡፡
አሁን ደግሞ ጋሻው መርሻአንፀባራቂው ኮከብበሚል ርዕስ ማወቅ እፈልግ የነበረውን የልጅነት ዘመናቸውንና የሕክምና አገልግሎታቸውን በተመለከተ መረጃ እያጣቀሰ እጃችን ላይ አድርሶናል፡፡ የተሳሳተውን የማቃናት፣ የጎደለውን የማሟላት የአንባቢ ድርሻ ቢሆንም፤ መሰል ዋርካዎችን በቻሉት አቅም ወደ ህዝብ አይን የሚያቀርቡ ደራሲያንን (ፀሀፊያንን) ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
የፕሮፌሰሩን የፖለቲካ ህይወት ብዙ የተባለለት ስለሆነ ለጊዜው ተወት ላድርገውና የህክምና ህይወታቸው ላይ ላተኩር፡፡

አንድ ወቅት ከፕሮፌሰሩ ጋር ትሰራ የነበረች ነርስ አነጋግሬ ነበር፡፡ እንዲህ ነበር ያለችኝ፡
“….ፕሮፌሰር በጣም ደግ፣ ሩህሩህና፣ የዋህ ነበሩ፡፡ ህሙማን በጣም ያዝናሉ፡፡ ሁሉም በሽተኞች ሳይታከሙ በፍፁም ወጠው አይሄዱም፡፡ በሽተኛ እንዲቀጠር አይፈልጉም፡፡ ………ለእነሱ እኮ ተስፋዎቻቸው እኛ ነን፡፡ ለምን መልስን እንሰዳቸዋለን ይሉ ነበር፡፡……..ብቻ….እምባ ያቀረሩ አይኖች……”
ሕክምና ሙያ ብዙዎችን እንደፈወሱ፣ ብዙ ተከታዮችንም እንዳፈሩ ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው፡፡ የተ... ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን “…….አርያነቱን በምሳሌነት እንከተላለን….” ያሉትም ከዚህ ሐቅ የተነሳ ነው፡፡

ለሙያቸውና ለሀገራቸው ትጉህ ሐኪም ያደረጋቸው ምን አልባትም አርበኛው አያታቸው ከቀኝ አዝማች ፅጌ ወረደ ወርቅ ጋር ማደጋቸውና ሐኪም ወርቅነህ እሸቴ ጋር የነበራቸው ግንኙነት ሳይሆን እንደማይቀርም ፀሐፊው /ሚኒስቴር ልጅ ሚካኤል እምሩ የሰጡትን ማስረጃ ጠቅሶ ያስረዳል፡፡ በህክምና ሙያቸው አንቱ የተባሉት እኒህ ሰው በልጅነታቸው ከድንቁርና በሽታ በአቡጊዳ መርፌ የፈወሷቸውን የድሬዳዋውን አለቃ ለማን እሳቸው ደግሞ ከተጣባቸው ደዌ በመሐሪ እጃቸው በቀዶ ጥገና ፈውሰዋቸዋል፡፡ ቀሪውን ታሪክ መጽሀፉን አንቡት፡፡

ፕሮፌሰር አስራት ሰው ናቸው፡፡ ሰው በመሆናቸው ብዙ ስህተቶችን ሰርተው ሊሆን ይችላል፡፡ ስህተቱን እያስተካከሉ፣ መልካሙን እየተከተሉ መሄድ ግን የትውልዱ ድርሻ ይመስለኛል፡፡ ያም ሆነ ይህ የአሁኖቹ የጤና ባለሙያዎች ከፕሮፌሰሩ ስነምግባርና ሰብዕና የሚማሩት ነገር ይኖር ይሆን…….? ምላሹን ለእናንተና ለባለሙያዎች??? እኔ ግን እንዲህ እላለሁ፡
           “ጊዜ የሚገታው ሩቅ የማይታይ
          ስምህ መጠሪያ ምታቆም ድንጋይ
         አስቀምጠህ እለፍ ትውልድ በረከት
         ቦታ ማይወስነው የልብ ላይ ሐውልት
 በኮልታፋ አንደበቴ ከዚህ በላይ ለእሳቸው ክብር የሚሆን ስንኝ መቋጠር አልቻልሁም፡፡እሳቸው ከህመም በገላገሏቸው ህሙማንና የሀገር ፍቅርን በተግባር ባስተማራቸው ትውልዶች ልብ ወስጥ በሰሩት ሐውልት ለዘላለም ሲታወሱ ይቀራሉ፡፡ ለታይታ ለሚኖረው ለእኔ ዘመን ትውልድ ግን መልክቴ ይኸው ነው፡፡


1 comment:

  1. ማነው ሞት ወስዶታል ብሎ የነገረህ፤
    የወልደየስን ልጅ ሞቷል ያልክ ደንብረህ።
    የሞቱት እያሉ ገምተው በቁማቸው፤
    እንዴት እኚህን ሊቅ ሞተዋል አልካቸው።
    በፍጹም አልሞቱም ፕሮፌሰር አሥራት፤
    ለጀግኖች ሰጥተዋል የነጻነት መብራት።
    ጉጅሌም ጠንቅቆ ይህንን ያውቀዋል፤
    ስማቸው ሲነሳ ሁሌም ይጨንቀዋል።

    ReplyDelete