‹‹ ሳይማር ያስተማረና ሳይተርፈው የደገሰ ትርፉ ፀፀት ነው››
መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
ሰሞኑን የማህበራዊ ሚዲያዎች ‹‹ጋሽ በጋሻው ለምዱን ገፎ በገሃድ ኦርቶዶክስ ይደለሁም አለ››…….አንዳንዶች ደግሞ ‹‹እምነት የለኝም አለ››፣ ሌሎች ደግሞ ‹‹ፕሮቴስታንት ነኝ አለ›› ይላሉ፡፡ ነገ ደግሞ ይህ ሰውዬ ‹‹ሰው አይደለሁም›› ብሎ እንዳይመጣ እፈራለሁ፡፡
አንድ ሰው የየትኛውም እምነትና ሐይማኖት (ሁለቱ የተለያዩ ናቸው) አማኝና ተከታይ ከመሆኑ በፊት ሰው መሆን አለበት፡፡ አንድ ሰው ‹‹ሰውነት››ን ከተላበሰ ያውም በሐይማኖት ስም ለብዙዎች መሰናከያና መወናበጃ ምክንያት መሆን የለበትም፡፡ የሚያምንበትን ነገር ከስር መሰረቱ ግልፅ አድርጎ የፈለገውን ሃይማኖት መከተል መብቱ ነው፡፡ በሌሎች ጓዳ እየገቡ መፈትፈት ግን ኢሞራላዊ ነው፡፡