Tuesday, October 17, 2017

ይወለዳል ገና!

 ይሄ ወጣትነት
ከሱስ ላይ ተጥደን፥ ያልፋል እንደዘበት፤
ይሄ ወጣትነት
ያልፋል እንደ ዋዛ
ለሃብታም ስናረግድ፥ ለውሸት ስንገዛ
ይሄን ወጣትነት
የኔ ቢጤ ሁሉ፥ ይሰዋል በከንቱ
ለ አሸሸገዳሜ፥ ለሚጠፋ አምሮቱ


ያ ጀግናው ተሜ ግን፥ የሀገሬ እንቆቆ
ስለ መራራ እውነት፥ ጣፋጭ ዓለም ንቆ
ስለ ነፍሱ ህልው፥ በስጋው የሞተ
ሐር ፀጉሩን ነጭቶ፥ ለ ፍትህ የሸበተ
በሀሰተኛ ዓለም፥ በእውነት የሰከረ
በአንዲት እስክርቢቶ፥ ሺዎች ያሸበረ
ኢትዮጵያዊ ባይሆን፥ ይቆጨኝ ነበረ!
፡
ተሜ!
ግን ኢትዮጵያዊ ነህ፥ ያውም ትንታግ ጀግና
ሺ ትውልድ ከአብራክህ፥ ይወለዳል ገና
ይወለዳል ገና........
ይወለዳል ገና........
ይወለዳል ገና........
~~~~~~~~~~
©
ዘ.ጥ (2010
)

No comments:

Post a Comment