ZELALEM TILAHUN (የ እናቱ ልጅ)
በዚህ ድህረ ገፅ በማህበራዊ ህይወት፣ ባህል፣ታሪክ፣ ሐይማኖት ና ጤና ላይ ያተኮሩ መጣጥፎች ይቀርባሉ፡፡
Labels
ሐይማኖት (Religion)
(8)
ማህበራዊ ጉዳይ (Social Affair)
(42)
ሳይንስና ቴክኖሎጂ (Science and Technology)
(4)
ባህል (Culture)
(11)
ታሪክ (History)
(20)
ከመፅሐፍት ዓለም (from books)
(6)
የጉዞ ማስታወሻ (Journey’s log)
(4)
ግጥም (Poam)
(44)
ጤና (Health)
(3)
Tuesday, January 1, 2013
ፓተንቱ ይሰጠው
የትኛው
ነው እብድ የትኛው ነው ደህና
መለየት አቃተን ግሎባላይዜሽን ባመጣው ፈተና
እብድ አሳጥሮ ቀዶ ሲለብስ አይተው
እራቁት ይሄዳሉ ዝመና ነው ብለው
ዝመና ከሆነ እራቁትን መሄድ አጭር ታይት መልበስ
በነፃ መደብደብ ለ ፀሐይ ለ ነፋስ
አለም ሳያስበው ቀድሞን ለዘመነው
ለሀገሬ ገበሬ ፓተንቱ ይሰጠው
Tuesday, December 25, 2012
ጌታ ሆይ ቅደመኝ
በአንድ በኩል ስሰፋ ሌላው ሲያፈስብኝ
ጥሬውን ስቆላ ብስሉ ሲያርብኝ
አንዱን አለፍኩት ስል ሌላው ሲያናቅፈኝ
ቀን በቁሜ ስቃዥ ሌሊት ሲያባንነኝ
አንድ ጊዜ ሲያስቀኝ ደሞም ሲያስልቅሰኝ
ቀኜ ሲበረታ ግራዬ ሲደክም
ራስ ፍልጠት ሲይዘኝ ጨጓራ ሲያገግም
ምን ይሆን መፍትሔው ለዚህ ከንቱ አለም
ጌታ ሆይ ቅደመኝ
ሸክሙን አልቻልሁም
Saturday, December 22, 2012
ተረት ተረት
ተረት በሀገራችን ትልቅ ቦታ አለው፡፡ የማህበረሰቡን ብስለት፣ ኑሮ ፣መስተጋብርና አመለካክት የማሳየት አቅም አለው፡፡ እስኪ ከዚህ በታች ስለ አንድ ብልጥ ልጅ የሚተርክ የአፋር ተረት ላውራችሁ፡፡
ተረት ተረት ---የመሰረት/የላም በረት
በአንድ
ወቅት
በጣም
ብልጥ
የሆነ
የ
15
ዓመት
እድሜ
ያለው
የአፋር
ተወላጅ
ልጅ
ነበር፡፡
ሆኖም
ይህ
ልጅ
በቤቱ
ውስጥ
ይደረግ
የነበረውን
መጥፎ
ነገር
ያውቅ
ስለነበረ
ሁልጊዜ
ያዝንና
ይበሳጭ
ነበር፡፡
አባቱ
ከእናቱ
ገረዶች
ከአንድዋ
ጋር
በድብቅ
ይባልግ
ነበር፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ(Read More)
Friday, December 21, 2012
አንችን ሞት አይንካሽ
የቱን ተናግሬ የትኛውን ልተው
ምን ቋንቋ ልጠቀም በምን ቃላት ላውራው
ምን ምሳሌ ልፍጠር በምን ልመስለው
እንዴትስ ልዘርዝር ከየት ልጀምረው
እፁብ
እፁብ ብዬ ዝም ልበል በአንክሮ
ዘላለም ይኖራል በውስጤ ተቀብሮ
ለዚህ ያደረሰኝ የናትነት ፍቅርሽ
ዛሬም ያፅናናኛል ብለይም ከፊትሽ
የአንችን ክፉ አልስማ
እናቴ
እባክሽ
በእኔ ዕድሜ ኑሪ አንችን ሞት አይንካሽ
F
or my beloved mother,
ኅዳር 2003
Newer Posts
Older Posts
Home
Subscribe to:
Posts (Atom)