Sunday, April 26, 2015

የመንገደኛ ነፍሶች ዋይታ

             ከ ጦቢያው አለም
ከወሎ ከሀረር፣ ከወለጋ ከወላይታ….ወጥተን
የደንበልን ሸለቆ የሱዳንን ጥሻዎች አቆራርጠን
በቀይ ባህር አዞዎች በየመን ግርዶሾች ተውጠን
ሞተን ተርፈን ሳውዲ አረቢያ ገብተን
ጉልበታችንን ሽጠን በልተን
በእንባችን ልብስ እያጠብን
ወዛችን ሽቶ ሆኖን ለራሳችን የነጻን ሲመስለን ለሌሎች ከርፍተን
በረሀ የበላው ጸጉራችንን ነጭተን ማግደን ሳት አንድደን ሞቀን
ነደን አብስለን በልተን አብልተን ሁሌ ሞት ሲፈረድብን

Wednesday, April 8, 2015

መልካም በዓል

“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን” 
                                (ኢሳ. 53፥5፤ 1ጴጥ. 2፥25)

Thursday, April 2, 2015

ተስፋ


 
ሁሌም ይታየኛል አንዳች ሩቅ ተስፋ
የዛሬ ያልሆነ የነገ ያልሆነ በጊዜ ሚገፋ
እንደ ህልም ያለ እውነት የመሰለ
ከመሬት ከፍ ያለ ከሰማይ ዝቅ ያለ
የህሊና ምስል ሰዓሊ ያልሳለው
ደራሲ በምናብ በብዕር ያልከተበው
ምሁር በምርምር ደርሶ ያልጨበጠው
ግብር ማልከፍልበት መንግስት ያላወቀው
ከእኔ ጋራ ያለ ተስፋዬ ብቻ ነው፡፡
             ዘላለም፤ ሰኔ 2006 ዓ.ም፣አዲስ አበባ

Monday, March 30, 2015

የጋሽ ጣሰው ስሞታ (መምህሩ)

 

እባክህን ጉንፋን ጉሮሮየን ተወኝ
ተወኝ ራስ ምታት አባክህ ልቀቀኝ
እባክህ ቁርጥማት እግሮቸን ማርልኝ
ለሀኪም ምከፍለው ገንዘብ በእጄም የለኝ
ተወኝ ተው በሽታ ባክህ ተለመነኝ
ትውልድ አስተምሬ አገር ማቀና ነኝ

Saturday, March 28, 2015

Top 10 Most Peaceful Countries In The World (Best List)


By:  Nelson Nwankwo -Mar 26, 2015 (GPI)
Top 10 Most Peaceful Countries In The World
Very Interesting topic, Most Peaceful Countries In The World? Peace a very hard word to completely define, but briefly we are going to look into whats really the definition of peace, what should a country be doing right for us to totally conclude that the country is one of the Most Peaceful Countries In The World.

Friday, March 20, 2015

ላልኖር እኖራለሁ

አንዴ በደስታ አንዴ በእንጉርጉሮ
ማታ በሳክስፎን ጥዋት በከበሮ
ሲጠፋ በቆሎ ሲገኝም በሽሮ
ደስ ሲለኝ በዘፈን ሲከፋኝ በሮሮ
አንዴ ተስፋ ሳጣ ሌላ ጊዜ ሳገኝ
ቀኖችን ስቆጥር ቀን ያልፋል እያልሁኝ፤
     ይሄ ብቻ አይደለም…..
በጋ ላይ ሲሞቀኝ ክረምት ላይ ሲበርደኝ
ቁልቁል ስበረታ ዳገት ላይ ሲደክመኝ
መባቻ ስጠግብ የገብርኤል ሲርበኝ
ማታ ላይ ስባንን ቀን እንቅልፍ ሲጥለኝ
ላልኖር እኖራለሁ ግዴታ ሁኖብኝ
የጫንቃዬ ሸክም ከእኔ እስኪርቅልኝ
              ጥር 2004 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ

Monday, March 16, 2015

ጀግናው አርበኛ በላይ ዘለቀ (አባ ኮስትር) ክፍል -2


  በላይ ዘለቀና ምቀኞቹ  
መጋቢት 1933 አ.ም. ከበደ ተሰማ (ደጃዝማች )ወዳገራቸው ለመመለስ መንገድ ላይ ከነበሩት ንጉስ ተልከው መጡ ::ከሳቸው ጋር የነበረው ጀኔራል ሳንፎርድ በላይ ዘለቀን ለመጨበጥ እጁን ሲዘረጋ በላይ ዘለቀ "ለፈረንጅ እጄን አልሰጥም "ብለው ሳንፎርድን አግባቡት :: በሁዋላ ልጅ መርድ መንገሻና እንግሊዞች ወደ ደጀን መቱ ::ወደበላይ ዘለቀ ላኩባቸው ::ሄዱ ::"የደጀንን ምሽግ ለመስበር ተባበሩን "ተባለ :: "መድፍ ይዛችሁዋል ?ኤሮቢላ ይዛችሁዋል ?"አላቸው በላይ ዘለቀ :: "አልያዝንም ግን መክበብ ይበቃል "አሉት :: "አይበቃም "አላቸው ::"ከዚህ በፊት ወር ካስራ አምስት ቀን ሙሉ ሞክረን ብዙ ወንድሞቼ አልቀዋል ::መድፍና ኤሮብላ አምጡና ምቱት ሌላውን ለኛ ተዉልን ::አለዚያ ግን እኔ ወንድሞቼን በከንቱ አላስፈጅም ::" ሳይስማሙ ተለያዩ ::