ህይወቴ
ህይወቴ ሜዳ ናት
የጠገበ ሁሉ- ኳስ ሚጫወትባት
ህይወቴ መንገድ ናት
ባለጊዜው ሁሉ የሚደፈጥጣት
ህይወቴ መሬት ናት
ባለጊዜው ቱጃር ቤት የሚሰራባት
ሕይወቴ ባዶ ናት
እኔም ችላ ያልኋት ሰዎችም የናቋት
አንድ እግዜሩ ብቻ ጨክኖ ያልተዋት
የረፋዷ ፀሐይ ህይወቴ ይች ነች
በዘር በሃይማኖት በ ደም የጨቀየች
በነገ በዛሬ እኔም የምኖረው
የህይወቴ ድርሻ 'ጣው እስኪወጣ ነው
ህዳር 2006 ዓ.ም (በስደት ሀገር በግፍ ለተገደሉት
መታሰቢያ)
No comments:
Post a Comment