Friday, February 13, 2015

የብሪታንያ ፓርላማና አከራካሪው የጽንስ ምርምር (የስልጣኔ ዕብደት)

የብሪታንያ ፤ የሕዝብ እንደራሴዎች ፣እ.አ.አ የካቲት 4፣ 2015 ዓ.ም ከቀትር በኋላ ፣ በአዲስ የሥነ ተዋልዶ ሥነ ቴክኒክ በመታገዝ ፣ አንድ ሕጻን ከሦስት ግለሰቦች ፤ ማለትም ከእናትና አባት ሌላ የአንዲት ሌላ ሴት ዘረ መል እንዲወርስ ማድረግ የሚቻልበትን ሁኔታ ፤ በድምፅ ብልጫ ፤ በሕግ መምሪያው ም/ቤት 


በኩል ተቀባይነት ለማግኘት በቅቷል። በፓርላማው ክርክር ከተካኼደ በኋላ ፣ 382 የሕዝብ እንደራሴዎች የተጠቀሰው ሥነ ቴክኒክ ሥራ ላይ እንዲውል ሲደግፉ 178 ተቃውመዋል። በሚመጡት ሳምንታት የሕግ መወሰኛው ም/ቤት በተመሳሳይ ሁኔታ በድምፅ ብልጫ ከደገፈው በሕግ ይጸድቃል ማለት ነው።
የብሪታኒያ ፓርላማ ሕጉን በድምፅ ብልጫ የተቀበለው በሰፊው ከተከራከረበት በኋላ ነበር ።ከወግ አጥባቂው ፓርቲ የፓርላማ አባልና ምክትል የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ጄይን ኤልሰን (Jayne Elison)


ሳይንቲስቶች በዚህ ነጥብ ላይ አንድ ዓይነት ድምፅና አመለካከት አላቸው የሚል የለም ። ግን ፓርላማው ማትኮር የሚገባው ፤ በአጠቃላይ የዓለም ዓቀፍ ሳይንቲስቶች የአቋም ሚዛን የሚያጋድለው ለዚህ ሥነ-ቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት ረገድ መሆኑን ነው ። አድካሚ ፤ጥልቅ ምርምርም አድርገውበታል »

በክርክሩ ወቅት ከፓርላማ አባላት የተሠነዘሩ ተቃራኒ አስተያየቶችም ነበሩ ።
«መልሳችን ፤ ይህ በሃገራችን የማንጥሰው ቀይ መሥመር ነው የሚል መሆን አለበት ። በዓለም ዙሪያ በማንኛውም ሃገር እንደሚደረገው ሁሉ ፤ቀዩን መሥመር ማለፍ የለብንም ።»
«ይህን ህገ-ደንብ በሥስት ምክንያቶች እቃወማለሁ ። በሞራል፣ በደኅንነት የአስተማማኝነት ጥያቄና በፓርላማ ጠቃሚ የአሠራር ቅደም ተከተል ሳቢያ !»

ይኽው በቤተ ሙከራ ፤ከአንዲት እናት ዘረ-መል የተበላሸን ንዑስ ክፍል ከአንዲት ሌላ ሴት ወስዶ በመተካት በትልቅ ብርጭቆ ውስጥ(IVF) ጽንስ ጤናማ ሆኖ እንዲፋፋ ማድረግ የxቻልበት አሠራር ፣እጎአ በ1960 ና በ1970 ፣በሮበርt ኤድዋርድስ የተደረሰበትና እርሳቸውም እጎአ በ 2010 በሕክምና ፤የኖቤል ሽልማት ለማግኘት የበኡበት ብልሃት ነው ። ይህን አከራካሪ የፅንስ አያያዝ በይፋ ፣በህግ እንዲፈቀድ በማድረግ ረገድ ብሪታኒያ ፣በዓለም ውስጥ የመጀመሪያይቱ ሃገር ለመባል ትበቃለች ።«የ3 ወላጆች ዘረ-መል ወራሽ ህፃን »የሚሰኘውን ጽንስ በቤተ ሙከራ የማከናወኑን ተግባር፣አጥብቀው ከደገፉት ታዋቂ የአገሪቱ ዜጎች መካከል ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዴቪድ ኬምረን ይገኙበታል ።
Ivan የተሰኘው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወንድ ልጅ በተፈጥሮ የአካል ጉዳተኛ የነበረ ሲሆን እጎአ በ2009 በ6 ዓመቱ ልዩ በሆነ የሚጥል ህመም ሳቢያ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ታውቋል ። ለብሪታኒያ የህግ መምሪያ ምክር ቤት የቀረበው የፅንስ ቴክኒካዊ አያያዝ እርግጥ ነው ፣አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎችና ተቃዋሚዎች በጀብደኝነት ሌላም የማይፈለግ ፅንስ ወደ ማስፋፋቱ ተግባር መሸጋገር እንዳይከሰት ሥጋታቸውን በመግለፅ አጥብቀው መንቀፋቸው ነው የተነገረው ። የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን የሕክምና ስነ ምግባር አማካሪ Brendan McCarthy ሳይንቲስቶች ፤የስነ ምግባርንም ሆነ ሞራልን ገደብ ሳያልፍ ምርምርን መቀጠል ተገቢ ተግባራቸውን ነው ነው ያሉት ። አያይዘውም ፤«ወደ መጨረሻ ውሳኔ ከማምራት አስቀድሞ ፤ለአያሌ ጥያቄዎች መልስ መሻት ብልህነት ነው »በማለት ነበር ፣ፓርላማው ድምጽ ከመሥጠቱ በፊት ቀደም ሲል ምክራቸውን የለገሡት ። አዲሱን የጽንስ አያያዝም ሆነ አንድ ህፃን ከ3 ግለሰቦች (ከወላጆችና ካንዲት ሌላ ሴት ጭምር) ዘረ-መል እንዲወርስ የሚደረግበት አሠራር ያስፈለገው ከ200 ህጻናት አንዱ ወይም አንዷ ፣በእናት በኩል ፍጹም ወይም መቶ በመቶ ጤናማ ያልሆነ ዘር ስለሚወርሱ ነው ሲሉ የሥነ ቴክኒክኩ አራማጆች ይናገራሉ ። በጽንስ ወቅት በዘረ-መል የሚወረስ በሽታ ከየ6,500 ው፤አንዱን ፈውስ በማይገኝለት እንከን ውስጥ እንዲኖር አለያም ለሞት እንደሚዳርግ በ«ኒew ካስል»ዩኒቨርስቲ ምርምር ያደረጉ ሳይንቲስቶች ገልጸዋል

በተጠቀሰው የፅንስ ምርምር ላይ ያተኮሩት ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ከሆነ ፤ የ3 ሰዎች ዘረ-መል ፅንስ ፤ ከ 99 ከመቶ በላይ ውርሱ የአባትና እናት ነው ። በፅንስ ጊዜ ለሕዋሳት ዕድገት ኃይል ሰጪ ወይም አመንጪ ክፍሎች (Mitochondria) እክል ሲያጋጥማቸው ነው የተሟላ ጤንነት የሌላቸው ልጆች የሚወለዱት። በብሪታንያ በያመቱ የተጠቀሰው እክል የሚያጋጥማቸው በግምት 125 ያህል ሕጻናት ይወለዳሉ። የ«ሚቶቾንድሪያ» እክል አጋጥሟቸው የሚያድጉ ሕጻናት የክንድ መስለል ወይም የጡንቻ ልፍስፍስነት፤ የልብ፤ ኩላሊትና ጉበት እክል እንዲሁም ብርቱ የጡንቻ ድክመት ይደርስባቸዋል።
ከዋናው የአውሮፓ ክፍለ ዓለም ማዶ በምትገኘው ደሴት ፤ ብሪታንያ፣ ለ 19ኛውና ለ 20ኛው ክፍለ ዘመን ሥልጣኔ መደላድል የሆኑ በዛ ያሉ ግኝቶች ፣ (የፈጠራ ውጤቶች ) መከሠታቸው የታወቀ ነው። እጅግ በዛ ካሉት በጣም ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፤ የባቡር ሐዲድ እ ጎ አ በ 1825 በጆርጅ ስቲፈንሰን፤ ስሚንቶ በ 1824 በጆሰፍ አስፕደን ፣ ኤልክትሪክ ሞተር በ 1821 በማይክል ፋራዳይ፤ በእንፋሎት የሚሠራ ሞተር በ 1801 በሪቻርድ ትሬብ*ሲክ፣ ፎቶግራፍ ማንሳት በ1837 በቻርለስ ዊትስተን እና ዊልያም ኩክ፤ በጦር ኃይል ረገድም ታንክ በ 1914 በኤርንስት ስዊንተን፤ በባሕር ውስጥና ላይ ላዩን የሚምዘመዘግ በባህር ላይ የሚንሠፈፉ መርከቦችንና የመሳሰሉትን ባሕር ሰርጓጅ መርከቦችን የሚያነጉድ ዘመናዊ ቶርፒዶ ወይም ሮኬት፤ እነዚህን ሁሉ ለዓለም ያበረከተች ናት ብሪታንያ !

የሞራል ጥያቄ ካስነሱት መካከል፤ በዚያው በብሪታንያ ፤ በቤተ ሙከራ የመስታውት ቱቦ ውስጥ ከጽንስ እስከ ውልደት በዚያ ያለፈችው እ ጎ አ በ 1978 ባልተለመደ ሁኔታ እንደተወለደች የሚነገርላትን ፣ የሉዒስ ብራውንን ታሪክ መጥቀስ ይቻላል።
እ ጎ አ ሐምሌ 5 ቀን1996 ፣ ከአንዲት በግ አካል ከተወሰደ ሕዋስ በቤተ ሙከራ መሰል ግልባጭ እንዲኖራት ተደርጎ የተወለደችውንና 6 ዓመት ከ 4 ወር ገደማ ከኖረች በኋላ የሞተችውን «ዶሊ» የተባለችውን በግም ማውሳት ይቻላል። አሁን ለ 3ኛ ጊዜ የዓለምን ትኩረት የሳበ ከአንድ ቤተሰብ ውጭ ከአባትና እናት የ 3ኛ ሰው መለስተኛ ዘረ-መል የሚኖራቸው ሕጻናት እንዲወለዱ መንገድ ሊጠርግ የሚችለው የቤተ ሙከራ ውጤት በብሪታንያ ሕግ መወሰኛ ም/ቤት ትናንት ተቀባይነት ያገኘበት ሁኔታ ነው።
የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ መስፋፋት በአመዛኙ ለሰዎች ሰፊ ጠቀሜታ ቢሰጥም ፣ አንዳንዱ ለምሳሌም ያህል ፤ ከዘረ- መል ጋር የሚያያዙ ምርምሮች ፣ እንዳጠያየቁና ጥርጣሬም እንደደቀኑ ይገኛሉ። አንደኛውና በዋናነት የሚነሣው የሞራል ጥያቄ ሲሆን ፤ ሌላው የምርምሩ ውጤት ከአነአካቴው እንከን እንደማይኖረው ምን ዋስትና አለ? የሚለው ነው።
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ (Dochebel radio-Amharic program)

No comments:

Post a Comment