የሳጥናኤል ምንዝር የጥንተ ፍጡራን
በጠሊሃ ሀገር በአፍቅሮተ ስልጣን
በከፊሎተ ዘር ህዝብን በመጨቆን
የአፍሪካን መሪዎች የለከፍከው ሰይጣን
አላማህ ምንድን ነው?
መኖሪያህ ወዴት ነው?
ዘመንህ ስንት
ነው?
መቼ ትወጣለህ ከ ምድረ አፍሪካ
መፃኢውን ትውልድ ወጣቱን ሳትነካ
ፀሎት ያስወጣሃል የቅዱሳን ፀበል
ነው ነፍጥ ይሻልሃል የመሳሪያ ትግል
እባክህ ንገረን አንተ ረቂቅ መንፈስ
ውጣ ከነግብርህ ከአምባገነኖች ነፍስ
እባክህ ተለመነን
ከአፍሪካ ውጣልን
እስከማይዜኑ መከራ ታሳየን
No comments:
Post a Comment