Saturday, October 24, 2015

“የእኔና የአንቺ ዓለም”

ለአንዱ ማግኘት ጣጣ 
ከውስኪ ሰገነት ስካር ላይ ሲወጣ
ለአንዱ ማጣት ዕዳ
ኑሮና ህይወቱ የቆሻሻ ገንዳ፤
አንዱ ጉልበተኛ የተጣላ ከእግዜር
ሰውን እንደ ሽንኩርት በስለት ሚመትር
ሌላው እረሃብተኛ
አገጩን ጭኑ ላይ ደግፎ የተኛ፤
አንዳንዱ ቄንጠኛ
በልዑል ሰገነት ልጁን የሚያስተኛ
ሌላው ዕድለቢስ
ከመላጣ እስፋልት ላይ በውርጭ የሚጠበስ፤
እዚያ ዲሞክራሲ 
ነፃነት በኬሻ ሁሉም ሰው ሃያሲ
እዚ አውቶክራሲ
ትንሽ ሰው ደራሲ፣ እራሱ ሃያሲ፤
ማዶ ቀዝቃዛ ብርድ 
የበረዶ ክምር ሰውነት የሚያርድ
ወዲህ የእሳት ምድር 
ጠብታ አልባ መሬት የሚያቃጥል ሐሩር፤
ይች ናት እንግዲህ…………
እግዜሩ ሲፈጥር መከራ ያየባት
በነጭ ወረቀት ላይ እርሳስ የነደፋት፤
ከእሱ ተቀብሎ ምድራዊው ፈላስፋ
የብዕሩን ቀለም ምራቅ እየተፋ፤
አጥፍቶ የሳላት በዥንጉርጉር ቀለም
ይች ናት እንግዲህ የእኔና የአንቺ ዓለም
!
          [ዘላለምየእናቱ ልጅ]

          ጥቅምት 11፣ 2007 ዓ.ም

Wednesday, October 21, 2015

'የሰንደቅዓላማ ቀን'ን…በበርጫ

(ከ'አጠቃ'ዎች አንደበት)

ከሆነ ሰፈር ወደ ፒያሳ እየሄድሁ ነው፡፡ አቤት እነዚህ እረዳቶች ደግሞ….ሳንቲም ጨምር….ጠጋ በልየዕቃ ይህን ያክል ትከፍላለህ….ከዚይ ላይ አይቆምም! አሁን አሁን ታክሲ ውስጥ ያለው ጭቅጭቅ ስለመመረረኝ፤ ቅርብ ከሆነ በሁለት አግሬ ማቅጠን ጀምሬአለሁ፡፡ ራቅ ካለብኝ ደግሞ ጆሮዬ ውስጥ የምጨምረው ጥጥ ይዞ መግባት ጀመርሁ፡፡ ታዲያ ዛሬም እንደተለመደው እርዳቱ እንደ ሐምሌ መብረቅ ተሳፋሪ ላይ መጮህ ሲጀምር ቶሎ ብዬ መከላከያ ጋሻዬን ጆሮዬ ውሰጥ ሰካሁ፡፡ ምን ላድርግ ጆሮዬ ገና ብዙ ክፉ ደግ መስማት አለባት-ቢጠቅማትም ባይጠቅማትም፡፡ ታዲያ በዚህ መሃል ፀጉሩን እንደ ደረቀ ተክል ቅርንጫፍ ያንጨበረረ አንድ ወጣት ከጎኔ መጦ ቁጭ አለ፡፡ በአካል ጠጋ አልሁለት-ሶስተኛ መሆኑ ነው፡፡ በሃሳብ መጠጋጋት ግን በአካል እንደ መጠጋጋት ቀላል አይደልም፡፡ አይገርምም! በአካል እንደምንጠጋጋው በሃሳብም ብንጠጋጋ ምን አይነት ኢትዮጵያ ትፈጠር ነበር? ተውት በቃ፡፡ ይቅርታ ወደ ልጁ ልመለስ፡፡ ታክሲው በአንዴ ከህዝባዊ ሽታ ወደ ጫትና ሲጋራ ማዓዛ ተለወጠ፡፡ ደግሞ ጫትና ሲጋራ ሲቀላቀሉ እንዴት ነው የሚሸቱት!

Monday, October 19, 2015

ለምን አታገባም? (ክፍል-01)

ባለፉት ድፍን ሃያ አመታት በት/ቤት ህይወቴ ከተጠየቅኋቸው ጥያቄዎች ቀጥሎ በብዛት የተጠየቅሁት ጥያቄለምን አታገባም?” የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ጎበዝ ማግባት ግንለምን አታገባም?” የሚለውን ጥያቄ እንደመጠየቅ ቀላል አይደለም፡፡ የሂሳብን፣ የፊዚክስን፣ የኬሚስትሪን ጥያቄ ፎርሙላውን በመጠቀም መፍትሔ መፈለግ ወይምፕሩፍማድረግ ይቻላል፡፡አግባየሚለውን ጥያቄ ግን ሚስት አግብቶ ለመመለስ ፎርሙላ አልባ የሆኑ ውስብስብ ጥያቄዎችን መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ሰውአግባ አግባ…..” ብሎ መስመር ውሰጥ ያስገባህና ነገ ግራ ስትጋባአይዞህ ቻለውብሎህ የፌዝ ሳቅ እየሳቀ ይሸሽሃል፡፡ ምሽት ላይጉሮ ወሸባንአስጨፍሮ በነጋታው ጥዋት ጫጉላ ሳይፈርስ የነገር ጦር ከመማዘዝ ዝግ ብሎ አስቦ፣ አጥንቶ ማግባት ይሻላል፡፡ ስንቶች ናቸው ተጋብተው አመት ሳይደፍኑ የሚፋቱት፤ ስለዚህ እኔ ረጋ ብዬ፣ በደንብ አጥንቼ ነው የማገባ ብየ እከራከራለሁ፡፡

አንድኛው መጦ ደግሞየአዲስ አበባ ልጅ እንዳታገባአለኝ፡፡
ኮስተር ብዬ ምነው አልኩት?

Monday, October 12, 2015

[ይድረስ ለአፍሪካ]


እንዴት ነሽ ሀገሬ እንዴት ነሽ አፍሪካ
የምስኪኖች ቋጥኝ የክፉች ዋርካ”
የምትል ግጥም ፅፌ ልልክልሽ አስቤ ነበር፡፡ ነገር ግን አንዱ አድርባይ አጎብዳጅ ስም አጠፋህ ብሎ ጆካ እንዳይለይ ብዬ ስለፈራሁ ለስለስ ባለ አማርዚኛ የሰላምታ ደብዳቤየን ልልክልሽ አሰብሁ፡፡ አኔ ምለው አፍሪካ እንዴት ነሽ ባያሌው? ኑሮ፣ ጤና እንዴት ነው?…ይሄ ፈረንጆቹ “undefined word” የሚሉትን ቃል እንዳትጠቀሚ፡፡ ማለቴ “ምንም አይል”፣ “cool” ምናምን እንዳትይኝ፡፡ እናቴ እኛም “ምንም አይል!” እያልን ነው ኑሮ ምናምንቴ አድርጎን የሄደው፡፡ አሁንማ “ኑሮ” የሚለውን ቃል ሲሰማ ሁሉ የሚበረግግ ምስኪን አፈር ነው፡፡ ብዙ ነው ማለቴ ነው፡፡ እባክሽ ደግሞ ተረት እንዳታወሪ፡፡ ይሄ ምንድነው እሱ…… “ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል” ….ምናምን እንዳትይ፡፡

Thursday, October 8, 2015

[“የእንቅልፍ ዘመን”]









ድሃ እንዳትሆን እንቅልፍህን አትውደድ” 
       መፅሐፈ ምሳሌ 20፡13



ጠቢቡ ሰለሞን በዚህ ዘመን ቢኖር ኖሮ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ የድሃ ድሃ እንዳትሆኑ እንቅልፋችሁን አትውደዱ” ብሎ ይናገር ነበር፡፡ እነሆ ይች ዓለም የበረዶ ዘመን፣ የነሃስ ዘመን፣የብረት ዘመን፣ የጨለማው ዘመን፣ የአብዮት ዘመን፣ የጦርነት ዘመን ፣ የሳይንስ ዘመን እያለች ብዙ አያሌ ዘመኖችን አሳልፋለች፡፡ እነሆ የእንቅልፍ ዘመን ደረሰ! እናት አህጉር አፍሪካ የ 50 ዓመት መፃኢ ራዕይዋን የምታሳካበት የስራ ዘመን ሳይሆን በድጋሜ ተኝተን ቅኝ የምንገዛበት የ "እንቅልፍ ዘመን" ውስጥ የገባች ይመስላል፡፡ ድህነት፣ ረሃብ፣ በሽታ፣ ጦርነት፣ ብጥብጥና ጥላቻ አፍሪካን ቅኝ የሚገዙበት የእንቅልፍ ዘመን!