Friday, December 16, 2016

‹‹የማታ የማታ...››

ኢንሴኔ ኢሴራ ተታኤ - ማናሆ ጣጊሳኖ
ሳይኖሩ አለሁ ማለት - ከ ባዶነት ዘግኖ 

እንደ በሬ ማግሳት - ትንኝን ሳይሆኑ 
ከ እኩይ ጊዜ ታቅሮ - መራቅ ከ ዘመኑ
ለ ራሱ አያውቅ ነዳይ -ሚል ተረት ታቅፎ
ከ ራስነት በላይ፣ የ ሰውነት መንፈስ ከ አእምሮዬ ገዝፎ
በ መሰሪ ገመድ፤ በ ህሊና ችንካር እጄ ተቆልፎ 
ነገ እያልሁኝ ኖሬ - በ ከንቱ ይሉኝታ 
ዛሬዬን ገድዬ፣ ከ ነገ እለያለሁ የማታ የማታ
.........(ከ ዘላለም ጥላሁን)...............

No comments:

Post a Comment