Sunday, December 24, 2017

አዲስ አበባ (በረራ)

እንዲህ ብሎ መጣፍ አሰኘኝ፡፡
የአዲስ አበባ ሰማይ ጎህ ሲቀድ፥ ካድሬም ቢሆን የሚያሳቅፈውን የታህሳስን ውርጭ እንደምንም ታግዬ ከምኝታዬ ታፋታሁ፡፡ፀጥ ባለው የአዲስ አበባ ሰማይ ስር፥ የሰንበት ቅዳሴ አድማሱን ተሻግሮ ከብርዱ ጋር የሚታገለውን የአማንያንን ልብ በሐሴት ይጠራል፡፡
"እምነ በሐ....ቅድስት ቤተክርስቲያን......አረፋቲሃ......"
;
ይቀጥላል፡፡
ከገደል ማሚቶው ቀጥሎ የሌላ ደብር ምስጋና የብርዱን ቆፈን እንደ ሰም ያቀልጣል፡፡ አማኒያን ነጠላቸውን መስቀለኛ አጣፍተው ውር ውር ይላሉ፡፡
አዲስ የሁላችንም ናት፡፡ የካድሬው፥ የወሬኛው፥ የሃብታሙ፥ የድሃው፥ የዘረኛው፥ የኢ-ዘረኛው፥ የለፍቶ አዳሪው፥ የአማኙ፥ የቀማኛው፥ የአሳሪው፥ የታሳሪው፥ የምሁሩ፥ የባዶ ጭንቅላቱ፥ የእግረኛው፥ የባለ ሐመሩ፥ የጦም አዳሪው፥ የሰክሮ አደሩ ከተማ ናት፡፡

Friday, December 8, 2017

የሰፊው ህዝብ ግጥሞች

አንቺን የለመዱ ብዙ ሰዎች ሳሉ
የቤቱ ሙሉ አዛዥ እንግዳ ነው አሉ
አንቺ አሽከር ነገርሽ ከኮሶ ባሰሳ
ያስቀምጠኝ ጀመር ሌሊት እያስነሳ
አዋዜው በዛና ምላሴን ተኮሰው
አነካክቶ መብላት፥ መች አውቅና እንደ ሰው
አየሁ አዝመራሽን አውሬ ሲጨርሰው
እንዲህ ሆነሽ ቀሪ፥ ይመስለዋል ለሰው
አጎንብሰሽ መሄድ አላውቅ ብዬ እንደ ሰው
እቀና ብዬ ነው ቤቴ የፈረሰው
እኔን ከፋኝ እንጂ ሀገሬን ምን ከፋው
ግራር አበቀለ ዝሆን የማይገፋው

እኔ ልኮራመት እኔ ከሰል ልምሰል
ስቀሽ አታስቂኝ የደላሽ ይመስል


ሌላ ጨምሩ እስኪ?

Monday, November 27, 2017

‹‹አንድም እናት በወሊድ ምክንያት…..››

-----------------------------------
‹‹
ሌሊት ላይ ታመመች
ምጤ መጣ ብላ፣ ሆስፒታል ውስጥ ገባች
አማጠች አማጠች
ሌሊቱ ጎህ ሳይቀድ፣ ሞት ተገላገለች፤
ሁሉም ሰው አዘነ፣ ዘመድ አለቀሰ
ሁለት ነፍስ፣ በአንድ ጉድጓድ፣ ቀብሮ ተመለሰ››
በቃ!

--------------------------------------------
ይህ ዜና በጓደኛዬ እህት ደርሶ ሐዘኑ ምን ያህል ልብ ሰባሪ መሆኑን በአይኔ ልመልከት እንጂ የብዙ ኢትዮጵያውያንን ቅስም ለዘመናት ሲሰብር የኖረ ሰቆቃ ነው፡፡ የነፍሰጡር ሞት አንድ ሞት አይደለም፣ የብዙ ሞቶች ጥርቅም ነው፡፡

Tuesday, October 31, 2017

ኢትዮጵያ ማለት………

(ከታዋቂ ሰዎች አንደበት)
‹‹ኢትዮጵያዊነት እንደ እንጉዳይ በአንድ ማታ የበቀለ አይደለም››
‹‹
ኢትዮጵያ ውስጥ የመደብ እንጅ የብሔር ጭቆና ኑሮ አያውቅም››
‹‹
ኢትዮጵያ የአስተሳሰብ ቆሻሻን የማፅዳት ጦርነት የሚያስፈልጋት ሃገር ናት……››
‹‹
ኢትዮጵያዊነት ሁሉን የመሳብ አቅም ያለው ልዩ ሃይል ነው››
‹‹
ገዥው ኢህአዲግ ሁለት ምርኩዝ አለው፡ ጠብ መንጃና ምርጫ ቦርድ››

‹‹ኢትዮጵያዊነት ቢገፉት የማይወድቅ፣ ቢከፍሉት የማይሰነጠቅ፣  በፅኑ ዓለት ላይ ፀድቆ የኖረ፣ በአጥንትና በደም የተሳሰረ ህያዊነት ነው››
ኢትዮጵያ ዘላለም ትኑር!

Tuesday, October 17, 2017

ይወለዳል ገና!

 ይሄ ወጣትነት
ከሱስ ላይ ተጥደን፥ ያልፋል እንደዘበት፤
ይሄ ወጣትነት
ያልፋል እንደ ዋዛ
ለሃብታም ስናረግድ፥ ለውሸት ስንገዛ
ይሄን ወጣትነት
የኔ ቢጤ ሁሉ፥ ይሰዋል በከንቱ
አሸሸገዳሜ፥ ለሚጠፋ አምሮቱ


ጀግናው ተሜ ግን፥ የሀገሬ እንቆቆ
ስለ መራራ እውነት፥ ጣፋጭ ዓለም ንቆ

Saturday, October 7, 2017

ኧረረረረ ወገቤ……................

አንቺ ማንጠግቦሽ አተላውን ቶሎ አምጪው ባክሽ
ምን ይች ልጅ ተጨማሪ ህመም ሆነችብኝሳ!


Friday, September 22, 2017

የጋሽ በጋሻው ነገር!

‹‹ ሳይማር ያስተማረና ሳይተርፈው የደገሰ ትርፉ ፀፀት ነው››
                    መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
ሰሞኑን የማህበራዊ ሚዲያዎች ‹‹ጋሽ በጋሻው ለምዱን ገፎ በገሃድ ኦርቶዶክስ ይደለሁም አለ››…….አንዳንዶች ደግሞ ‹‹እምነት የለኝም አለ›› ሌሎች ደግሞ ‹‹ፕሮቴስታንት ነኝ አለ›› ይላሉ፡፡ ነገ ደግሞ ይህ ሰውዬ ‹‹ሰው አይደለሁም›› ብሎ እንዳይመጣ እፈራለሁ፡፡
አንድ ሰው የየትኛውም እምነትና ሐይማኖት (ሁለቱ የተለያዩ ናቸው) አማኝና ተከታይ ከመሆኑ በፊት ሰው መሆን አለበት፡፡ አንድ ሰው ‹‹ሰውነት›› ከተላበሰ ያውም በሐይማኖት ስም ለብዙዎች መሰናከያና መወናበጃ ምክንያት መሆን የለበትም፡፡ የሚያምንበትን ነገር ከስር መሰረቱ ግልፅ አድርጎ የፈለገውን ሃይማኖት መከተል መብቱ ነው፡፡ በሌሎች ጓዳ እየገቡ መፈትፈት ግን ኢሞራላዊ ነው፡፡