Thursday, January 26, 2017

ሶስቱ_ወፎች...

 ቀኑ ጥቁር ነበር~ደመና ያዘለ
ተጓዥን የሚያደርስ~ከታች መንገድ አለ
እንደ እየሱስ መስቀል~የተመሳቀለ፤

ረጅም ጉዞዬ~ስሄድ በመንገዴ
አእዋፍትን ዛፍ ላይ~አያለሁ አንዳንዴ

ከነዚህ መካከል~በውበት የሚያምሩ
ቀልቤን የወሰዱ~3 ወፎች ነበሩ፤
ከዛፉ ወጥቼ~ትንሽ ስረጋጋ
ክንፋቸውን ልይዝ~እጄን ስዘረጋ

አንድ ሲሉ.....
.......አንድ ሲሉ
ሁሉም በየተራ~ጥለውኝ በረሩ፤

ቁጭትና ንዴት~ እልህ ተደምሮ

እንቅልፍ ቢጤ ጣለኝ~በድካም አስክሮ፤
ግንባሬ በታች~አንዲት ፍሬ ወድቃ

ዘራፍ ወንዱ ብዬ~ እንቅልፌ ስነቃ
በህይወቴ ዛፍ ላይ~ብዙ አእዋፋት ሰፈሩ
ቀልቤንም ላይስቡት~አብረውም ላይኖሩ፤

በዚህ ሁሉ ሂደት~አውቃለሁ አንድ ሃቅ
እውነተኛ ብዕር~የፃፍሁት በደማቅ

"ለማዳም ፍጥረታት ክንፍ ያላቸው ሁሉ
ጊዜውን ጠብቀው ሁሉም ይበራሉ"
"በዚህ ግዑዝ ዓለም~የለም ትልቅ ቅጣት
እንደ መካ` እና~ፈልጎ እንደ ማጣት!"

[#ጥር_2009: ዘላለም]


No comments:

Post a Comment