Thursday, February 23, 2017

"አክሚኝ...፩"

አመመኝ
አልችል ስል ተኛሁኝ
.
.
ተኝቼም ሲብሰኝ~በሽታዬ ሲከር
ሄድሁኝ ወደ ሃኪም~ህመሜን ላማክር
.
.
.
ሆስፒታል ገብቼ~ደሜን መረመሩኝ
ትዝታሽ ነበረ~እኔን ያሳመመኝ

.
.
.
.
ሐኪሙም፡ 
የልቤን ስሞታ~በጆሮው አዳምጦ
ምን ልስጠው እያለ~በብዙ አምጦ
....
አ
........
ም
.............
ጦ
.
.
....................
አ
.........................
ም
..............................
ጦ
.
.
.
በ አንድ ሳምንት መድሃኒት~እንደማልድን ሲያውቀኝ
እድሜ ልክ እንድወስድ~አንቺን አዘዘልኝ
.
.
.
ህመሜን ባሰሚ~ልቤን ባታደምጪ
ማዘሻው ባይደርስሽ~ለ እኔ እንድትሰጪ
.
.
.
እባክሽ ነይልኝ~ይኸው ቃሌን ስሚ
አልሻም መድሃኒት~አልሻም አስታማሚ
እንድድን አውቃለሁ~ከፊቴ ስትቆሚ
.
.
.
.
በጣር ላይ ነኝና~አይወላውል ልብሽ
ግዴለም አክሚኝ~ለ ነፍስ እንዲሆንሽ
በአንቺ ሰቨቭ ብሞት~በኋላ እንዳይቆጭሽ!

----------------------------------------
(
ለ ህመሜ)
©
ዘላለም ጥላሁን (የእናቱ ልጅ)



No comments:

Post a Comment