መ ነ መ ነ ች እ ው ነ ት
ብርሀን ደበዘዘ~ጨለማ ደመቀ
ሰው ከሰው ሲቀርብ~ሰው ከእራሱ ራቀ
ማመን መተማመን~ጥለው ተሰደዱ
ፍርሃት ጥርጣሬ~ከ ልብ ተዋሃዱ፤
አይንና አፍንጫ~ጉርብትና እረሱ
መተዛዘን ቀርቶ~ይሙት ሆነ ክሱ፤
ቅትሎ…. ስቅሎ
ቅትሎ….ስቅሎ
ይላል ግብረ ቃኤል~ክፋት በ ጀርባ አዝሎ፤
እም አልቦ ደመና~ዶፍ እየወረደ
ከ አፍላጋት እምብርት ላይ~እ’ሳት እየነደደ
ሳይዘራ ታጭዶ~እ’ህል እየተቦካ
በ ወረቀት ጥቅል~ልብ እየተመካ፤
የ አንዳውላ ምርኩዝ~እየተደገፈ
ሰው እንደ ሰው ኖሮ~ማለፍ ተጠየፈ፤
ንዋይ ብቻ ሆነ~የሰውነት ማሳ
ህሊናም ተከዳ~እግዜሩም ተረሳ
----------------------------------------
© ዘላለም; የካቲት 2009
ንዋይ ብቻ ሆነ~የሰውነት ማሳ
ReplyDeleteህሊናም ተከዳ~እግዜሩም ተረሳ
ቅትሎ…. ስቅሎ
ReplyDeleteቅትሎ….ስቅሎ
ይላል ግብረ ቃኤል~ክፋት በ ጀርባ አዝሎ፤
ማመን መተማመን~ጥለው ተሰደዱ
ReplyDeleteፍርሃት ጥርጣሬ~ከ ልብ ተዋሃዱ፤