ወይ አንቺ አድዋ! 
የጥቁር ህዝብ ትንሳኤዋ!
በኩረ ነፃነት ምሰሶዋ!
-------------
የደመና ጥግ~የሰማይ ክሳድ 
የሐበሻ ዘር~የወኔ ሞረድ
ለ አፍሪካ ጭቁን~የነፃነት በር 
መክፈቻ ቁልፏ~የ ‘ይቻላል’ ድር
የማንዴላ ኃይል~የሉተር ህልም 
መነሻ ሃሳብ~ትንቢተ ዓለም
አድዋ አንቺ ነሽ!
አዎን አንቺ ነሽ አድዋ 
የጥቁር ህዝብ ትንሳኤዋ!
በኩረ ነፃነት ምሰሶዋ!
……..
ክብር ለጀግኖችሽ~ለሰማ’ታቱ
ለ ሀገር ፍቅር ብለው በክብር ለሞቱ
ክብር ለአባቶች~አፈር ለላሱ
ለእኛ ነፃነት~ሞት ለቀመሱ!
ክብር! ክብር! ክብር! ክብር!
ሞተው ላዳኑን~ከጥፋት ቀንበር!
~~~~~~~~~~~~~~~~~
© ዘላለም
[ተፃፈ፡ ጥር  25፣ 2008 ዓ.ም፡ አድዋ ከተማ ]

 
 
No comments:
Post a Comment