Sunday, March 19, 2017

ለ ዝሆኖች ሲባል…

እዚያ ማዶ
ሰማይ ተዋዶ
የታላቅነት ታሪክ..በታዛቢነት ቆሟል
ትናንት ነገ.. አፉን ከፍቶ ይናገራል!
.
ወዲ ማዶ፡
ትውልድ ግራ ተጋብቶ እግሩ ወደ መራው ያዘግማል
ትናንቱን እየሻረ ዛሬውን ያሞግሳል!
;
መሃል ባለው ገደል
አንዱ አንዱን ሲበድል፤
ፈርጣማው ሲወጣ ወደ ትልቅ ማማ
ብዙሃኑ አለከዚያው ገደሉ ብሶት እያሰማ
ምስኪኖች ገድልየብሶቱ ጩኸት
እግዜር ደጅ ቢያንኳኳቢደርስ ፀባኦት፤
.
ተራራው ላይ ላሉትመች ጩኸት ተሰማ
ሸፈኖ እያስቀረው ሌሎች ሚነፋ የመለከት ዜማ፤
;
አያችሁ፤
ወተት ላልጠገቡ እግረ ፈት ህፃናት
ጠጥተው እንዲያድጉ ምናወራው ተረት፣ 
ይሄ ነው ጅግሩ 
አይጥን ጀብዶ አፍኖ አንበሳን ጀግነንት ዘወትር ማስተማሩ፣
ይሄ ነው ጅግሩ 
ጉንዳንና ዋኔ አንድ ላይ ሲኖሩ
ጉንዳን ሞኝ ነበረ ብሎ መናገሩ፤
.
.
.
ከማማው ዝቅ ብሎ ገደሉ ወጦ 
ወደ ሁሉ አቅጣጫ አይኖቹን አፍጦ፤
አፋፉ ላይ ቆሞ
ሰው የመሆን ጥላን ወደ ሁሉ አዝሞ፤ 
ትናንትን ዛሬ በጉልህ ላስተዋለ
በነፃ ህሊና ፍርድ የሚፈርድ ካለ፤

በ ሃገሬ ጉዞ  በ  ዘመናት መሃል
ዝሆኖች ሲባል አይጦች ተረስተዋል!”

-------------------------
(Zelalem T, March 2017)

No comments:

Post a Comment