ከ ቤተስኪያን ታዛ~ከ ካቡ ስር ቆሜ
ከ እግዜሩ አስተብርኮ~ለ አንቺም ተሳልሜ
ስምሽን እጠራለሁ~በ ዜማ ውዳሴ
ከ ደም ከ ስጋሽ ጋር~ተቆራኝታ ነፍሴ፤
እንደምን ዝም ልበል~እንዴት ብዬ ልሽሽ
ሰርክ ያባክነኛል፣ ከ እናቴ ጡጦች ጋር~የጠባሁት ስምሽ
ከ ገንቦሽ ሳልጠጣ~በ ቅቤሽ ሳልወዛ
በ ምስለኔ ጅራፍ~ወገቤ ተይዛ
እንደ ሲኦል ግዞት~ነፍሴ ተገንዛ
ለምን ነው ዘወትር~በ ስምሽ ምገዛ???
ይኸውልሽ ውዴ፡
ከ ውበትሽ ጠቅሰው
ከ ታሪክሽ ነቅሰው
ስለ ስምሽ ክብር~እልፎች ሲናገሩ
በ አርያም ዜማ~ሁሉም ሲዘምሩ
የ ሰገነት ግርማሽ~ሲታየኝ ስዕሉ
የ ገደሉሽ እንጂ~ያዳኑሽ የት አሉ???
........................................
((ዘላለም ጥላሁን-ሸገር-ኢትዮጵያ))
(ለ አንቺ……© 2009 ዓ.ም)
No comments:
Post a Comment