አያቶቻችን፤
በ ሀገር ፍቅር የሰከሩ
አንበሳ ያሰገሩ
ጥሊያንን የገሩ
ሰንደቋን አንግበው 
ረሃብ መከራን ታግሰው
ስለ ወገን  የሞቱ~ድንበር ያስከበሩ
እውነትም ጀግኖች ነበሩ!
እውነትም ፃድቆች ነበሩ!
አባቶቻችን
፤
በ እንጥፍጣፊ ፍቅር 
ተዋድቀዋል ለ ሀገር!
አልፎ አልፎ 
ራስነት ገዝፎ
ልዩነት ሲዘሩ
አጭደው ሲከምሩ
ዘር እየቆጠሩ 
ድንበር እያሰመሩ
እኛን ልጆችን አፈሩ!
እኛ ልጆች፡
የ ሀገር ፍቅር ጠፍቶ~ፍቅረ ንዋይ ነግሶ
በ ልዩነት የ እሾህ አጥር~ጥላቻ ተለብሶ
በ እኛነት መቃብር~እኔነት ሰልጥኖ
ውሸት ብርሃን ለብሳ~እውነቱ ተከድኖ
ልባችን ከ አያቶች 
እግራችን ከ አባቶች 
መሆን እየሻተ
መሰረቱ ጠፍቶት~ሰርክ እየዋተተ
እንደ ቻይና በራድ~በ ቶሎ የሚሞቅ
እንደ በጋ ቅጠል~በ ቶሎ የሚደቅ
ስስ ወኔ ታቅፈን 
የ አርበኞቹ  ልጆች መባሉ ተረፈን!

 
 
No comments:
Post a Comment