ደብልቅልቅ ሃሳቦች
ቃል አልባ ስሜቶች
እንደ ገጠር ሕፃን በ ጀርባዬ
ታዝለው
እንደ ጨቋኝ ገዢ ከ ላዬ ተቀምጠው
ስሄድ ሲመልሱኝ ከ ፊቴ እያለፉ
ስመለስ ሲንጡኝ ከ ኋላ እየገፉ
ወዴት ብዬ ልሂድ ወደ የት ልራመድ
በ ምድር በ ሰማይ በ ታጠረ
መንገድ፤
……….
ስለ ዓለም መፈጠር ስለ ሰው
ህላዌ
ስለ ሰማይ ደስታ ስለ ምድር
ደዌ
ስለ ፍቅር ሃይል ስለ ሰው ልጅ
እድሜ
ስለ መኖር ትርጉም ስለ ሞት
ፍፃሜ
ስለ ፍጥረት ሚዛን ስለ ሰው
ነፃነት
ስለ ጽድቅ ኩነኔ ስለ ዓለም
ኃጢያት
ስለ ንፁሃን ግፍ ስለ መውደድ
መጥላት
በ ቃልና ሐረግ ይህን ሁሉ ስሜት፤
;
ልፅፍ አስብና!
በ ውስጤ ያመቅሁት የ ሃሳብ
ደመና
ናላዬን ያዞረው የ ስሜት ምጥቅና፣
ማረጊያ እስትንፋሶች ቃላት መክነውበት
በ ሰማይ በምድር ጎዳናው ታጥሮበት
ውስጤን ያስጨንቃል እንደ ነፍሰ ጡር ሴት
;
እነዚህ እሳቶች ውስጤን ያከሰሉ
በ አእምሮዬ ጓዳ በ ስስ የተሳሉ
በ ሳይንስ አልባ ህ’መም በ
ማይድን ታክሞ
ቃል አልባ ስሜቶች ልቤ ተሸክሞ፣
ለ እግዜር ይማርህ ለ ሐኪም
የቸገረ
አብሮኝ ለ ዘመናት ከ ውስጤ
እየኖረ
ለ መናገር እንኳ ይኸው ቃል
ታጠረ፤
;
የ ስሜት ልህቅና
የ ሃሳብ ልዕልና
ቋንቋና ፊደላት በ ሚል የብረት
አጥር
እንደ ሙዚየም አንበሳ ዙሪያ
ሲሽከረከር
በ ምናቡ ዓለም ቀላያትን ሲያስስ
በ ክንፍ አልባ እጆቹ አድማስን
ሲዳብስ፤
በ ሃሳብ ውቅያኖስ በ ስሜቱ ባህር
አሁን ገና ገባኝ ሰው ሠጥሞ
እንደሚቀር
አሁን ገና ገባኝ ሞቶ እንደሚቀበር፤
-------------------------------------
© ግንቦት 2009 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment