(ጎዛመን-ደብረ ኤልያስ-አዲስ አበባ-ዳንግላ-ሽሬ-ወለጋ-ጅማ-ከፋ-ሱዳን-ኢጣሊያ-ኢየሩሳሌም-ኒውጀርሲ-ኒዮርክ-ጄኔቫ-እንግሊዝ-ሆላንድ-ኢትዮጵያ)
(ጥንቅር_ዘላለም ጥላሁን)
የ ነፃነት ቀንዲልን ለመቀዳጀት፣ የ ጨለማውን ዘመን ለመግፈፍ፣ የ ጭሰኞችን ቀንበር ለማራገፍ፣ ርትዕት የሆነች ፍትህን ለማስፈን፣ ሀገራቸውን ለማዘመን ሲሉ፤ ጠመኔያቸውን አስቀምጠው በረሃ ለበረሃ፣ ጫካ ለ ጫካ ተንከራተዋል፡፡ በ ጠላት እጂ ለ 7 ዓመት በ ግዞት ታስረዋል፡፡ የ ሾለ ብዕራቸውን አፎት ከፍተው በ ወረቀት ሰሌዳ ላይ አንብተዋል፡፡ ቀን ቀን ሀገራቸውን በ ቅንነት ሲያገለግሉ ውለው፤ ማታ ማታ ደግሞ ጭንቀታቸውንና ራዕያቸውን፣ ብሶታቸውንና ተስፋቸውን በ ብዕራቸው ሲተነፍሱ ያድራሉ፡፡ ሀገራቸውን በ መምህርነት፣ በ ርዕሰ መምህርነት፣ በ አርበኝት፣ በ ዲጵሎማትነት፣ በ ሚንስትርነትና በ ደረሲነት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በ ቅንነት አገልግለዋል፡፡ በ ኢትዮጵያ የዘመናዊ ስነ ፅሁፍ ታሪክ ( በተለይም በ ልቦለድ አፃፃፍ) ታለቅ ብርሃን ፈንጥቀዋል፣ የ ዘመን አይሽሬው ፍቅር እስከ መቃብር ፀሀፊ--ክቡር ዶክተር አምባሳደር ሐዲስ አለማየሁ፡፡
ደራሲ ዶ/ር ሐዲስ ዓለማየሁ ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በ እንጾር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በጥቅምት ፯ ቀን ፲፱፻፪ ዓ.ም. ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት በቤተሰባቸው አጠገብና ባባታቸው አገር ደብረኤልያስ ሄደው የግእዝ ትምሕርት ቤት ቅኔ ተቀኝተዋል። የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣ በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በኋላ ወደ በ፲፱፻፲፰ ዓ.ም. አዲስ አበባ በመሄድ በስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በኋላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ለትንሽ ጊዜ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ። ከዚያም ወደ ጦርነቱ ዘመቱ፡፡ ሐዲስ አለማየሁ ለ ጦርነቱ ያነሳሳቸውን ምክንያት ሲናገሩ በትዝታ መፅሃፋቸው እንዲህ ይላሉ፡
“…ያ
ለዘመቻ
የሚያስፈልጉትን
ነገሮች
ለመግዛት
ሲሽቀዳደም
ያየሁት
ሁሉ፤
ያ
ሲያቅራራና
ሲፎክር
የሰማሁት
ሁሉ
ከጥቂት
ጊዜ
በሁዋላ
ወደ
ጦርነቱ
ሲጓዝ
እዚያ
ከጠላት
ጋር
ገጥሞ
ሲዋጋ
ሲጋደል
ሲሞት
ቆስሎ
ሲጨነቅ
ስዕሉ
ይታየኝና
መንፈሴ
ረፍት
አጥቶ
እየተወራጨሁ
ስነሳ
ተመልሼ
ስተኛ
ቆይቼ
‘ልዝመት
ወይስ
ልቅር?’
እላለሁ።
ለዚህ
ጥያቄ
በቀላሉ
መልስ
ለማግኘት
አልቻልሁም።…ያ
ሁሉ
ሰው
እንዲሁ
በተለምዶ
ወይም
‘ሀይማኖት
የሚያስለውጥ
ርስት
የሚነቅልና
ነፃነት
አሳጥቶ
እንደ
ባሪያ
የሚገዛ
ጠላት
መጣብህ’
ተብሎ
የተነገረውን
እንዲሁ
በጭፍኑ
አምኖ
ለመዋጋት
ሲዘምት፤
እኔ የነፃነትን ትርጉም ከብዙዎቹ የተሻለ የማውቀው ወደ ሁዋላ መቅረት የማይገባ መስሎ ይሰማኛል…”
ከዚያም ሐዲስ ዳንግላ ከተማ ያስተምሩበትና በሃላፊነት ይመሩት የነበረውን ት/ቤት ትተው ከ ጎጃሙ ገዥ ከ ራስ እምሩ ኃ/ ስላሴ ጦር ጋር ወደ ሽሬ ለመዝመት ተነሱ፡፡ በ ወቅቱ ባጠራቀሟት ደሞዝ ያደረጉትን ዝግጅትም እንዲህ ሲሉ ይገልፃሉ፡፡
“አቶ ዘውዴ
ጤናውና
እኔ
የየራሳችን
ጠመንጃና
ጥይት
ነበረን።
ለረዥም
ዘሪሁንና
ላጭር
ዘሪሁን
ሁለት
ጠመንጃዎችን
ከሚያስፈልጋቸው
ጥይት
ጋር
እኔ
እዚያው
ዳንግላ
ገዛሁ።
እንዲሁም
አንድ
መጠነኛ
ሸራ
ድንኩዋን
ለራሴ
አንድ
መጠነኛ
አቡጀዲድ
ድንኩዋን
ላቶ
ዘውዴና
ለጤናው
ሌላ
አቡጀዲድ
ድንኩዋን
ለሁለቱ
ዘሪሁኖችና
ለገላው
ገዛሁ።
የኮርቻ
በቅሎ
ፊቱንም
ስለነበረኝ
ለድንኩዋኖቻችንና
ለስንቅ
መጫኛዎች
የሚሆኑ
አንድ
የበቅሎ
አጋሰስና
አንድ
ስናር
አህያ
ገዛሁ።…”
በ ራስ እምሩ ይመራ ስለነበረው የጦር ብዛትና ዝግጅትም እንዲህ ይላሉ፡
“በ1928 ዓ/ም
በራስ
እምሩ
አዝማችነት
ወደ
ሽሬ
ግንባር
የዘመተው
የጎጃም
የጦር
ሠራዊት…በግምት
ሰላሳ
አምስት
ሺህ
ያክል
ይሆናል
ይባል
ነበር።
የያዘው
መሳሪያም
ከክብር
ዘበኛው
በቀር
(ቁጥራቸው
ከ800
– 1000 ይሆናል)
እንዲሁ
ከያይነቱ
የተደበላለቀ
ከመሆኑ
ሌላ
አብዛኛው
የማያስተማምን
አሮጌ
ነበር።
ባላገሩና
ከተራው
ወታደር
የሚበዛው
የያዘው
ጠመንጃ
ናስ
ማስር፤
ውጅግራ፤
ወጨፎ፤
ስናዲር፤
መስኮብና
እነሱን
የመሳሰለ
ጊዜው
ያለፈበት
መሳሪያ
ነበር።
ለዚያውም
በቂ
ጥይት
የነበራቸው
ጥቂት
ይሆናሉ። መኩዋንንቱና
ባለሟሎቻቸው
ብቻ
እንደ
መውዜር
ዲሞትፈር
(ሊመትፈር)፣
ለበን
ያለ
ጠመንጃና
በቂ
ጥይት
ነበራቸው።
በመሳሪያ
በኩል
የክብር
ዘበኞች
ስድስት
መትረየሶችና
አንድ
ያይሮፕላን
ማውረጃ
ነበራቸው።”
ሀዲስ ከ ሰራዊቱ ጋር ከ ተቀላቀሉ በኋላ ወታደሩን የሚያነቃቁ ንግግሮችን በ ተደጋጋሚ ያደርጉ ነበር፡፡ ይንንም በ መፅሀፋቸው በ ሃቀኝነት እንዲህ ሲሉ ይገልፃሉ፡
“
የራስ
እምሩ
ሠራዊት
ከዳንግላ
ባቸፈር
በዱርቤቴና
በደንገል
በር
አልፎ
በጌምድር
ግዛት
እስኪገባ
ድረስ
በየሰፈሩበት
ቦታ
አካባቢ
የሚኖረው
ዘማች
እየመጣ
ሰልፍ
ባሳየ
ቁጥር
ረዥም
ለበኔን
እያነገትሁ
ያን
ረዥም
ንግግሬን
ስደግም
አፌ
እንደ
‘አቡነዘበሰማያት’
ለምዶት
አይኔን
ንግግሩ
ወደ
ተፃፈበት
ወረቀት
መመለሱን
እንኩዋ
ረስቼው
ነበር”
በ ወቅቱ ከሚያነቧቸው ማነቃቂያዎች ውስጥ የ ‹‹ኢትዮጵያ ልቅሶ›› የተሰኘው ግጥም በ ቀዳሚነት ይጠቀሳል (የግጥሙ ቅንጫቢ ይህን ይመስላል)
“ጀግና አልተተካም ወይ በቴዎድሮስ ስፍራ፤
ጎበዝ አልቆመም ወይ በዮሀንስ ስፍራ፤
ሰው የለበትም ወይ በምኒልክ ስፍራ፤
ጠላቴ ሲወረኝ ከቀኝ ከግራ፤
የሚሰማኝ ያጣሁ ብጣራ ብጣራ።
ወይ እኔ ኢትዮጵያ የጀግኖች እናት፤
ሁሉም አለቁና ትተው ባዶ ቤት፤
ደርሶብኝ የማያውቅ አገኘኝ ጥቃት።
አየ ዋዬ ልጆቼ አየ ዋዬ ከዳችሁኝ ወዬ።
ሀዲስ
አብረው
ካሳለፏቸው
ከ
ጣሊያን
ጋር
ከተደረጉት
የ
ዳባት፣
የሽሬ፣
የ
ተከዜና
የ
ደባጉና
ውጊያዎች
ውስጥ
በ
ህሊናቸው
ሁሌ
የሚመላለሰውን
የተከዜውን
ሁኔታ
እንዲህ
ሲሉ
ይገልፃሉ፡
“…ስለ
ሽሬ
ግንባር
ጦርነት
ሳስብ
ባይነ
ህሊናየ
ፊት
ጎልተው
ከሚታዩኝ
ትርኢቶች
አንዱ
/ተከዜ
ወንዝ
ውስጥ
የሆነው/
ነው።
የተከዜ
ውሃ
እመሻገሪያው
ላይ
ሰፊና
ፀጥ
ያለ
ነው።
ታዲያ
ያ
ሰፊ
ውሃ
ገና
ከሩቅ
ሲያዩት
ቀይ
ቀለም
በ
ከባዱ
የተበጠበጠበት
ይመስላል።…መሻገሪያው
በቁሙም
በወርዱም
ከዳር
እስከ
ዳር
ሬሳ
ሞልቶበት
የዚያ
ሬሳ
ደምና
ፈርስ
ነው!
የሰው
ሬሳ
የፈረስና
የበቅሎ
ሬሳ
ያህያ
ሬሳ፣
ያውሬ
ሬሳ
ሬሳ
ሬሳ
ሬሳ
ብቻ!
እግር
ከራስ
ራስ
ከግር
እየተመሰቃቀለ
እየተደራረበ
ሞልቶበት፤
የዚያ
ሁሉ
ሬሳ
ደምና
ፈርስ
ነው።…ያ
የሬሳ
ክምር…ከጦርነቱ
ግንባር
ሽሽት
ከተጀመረበት
ቀን
ጀምሮ
መሰንበቻውን
ሰውና
ከብቱ
ሊሻገር
ሲገባ፤
አውሬ
ውሃ
ሊጠጣ
ወይም
ሬሳ
ሊበላ
ሲመጣ
ሁሉም
ባንድ
ላይ
እዚያ
በ
ቦምብ
ሲያልቅ
የሰነበተ
መሆን
አለበት።…”
ይላሉ፡፡
በተለይ
ጣሊያን
እስካሁን
ድረስ
ተገቢውን
ካሳና
ይቅርታ
ያልከፈለችበትንና
በ
ዘመናችን
በ
ፅኑ
የሚወገዘውን
መስተርድ
ጋዝ
በ
ወቅቱ
በ
ኢትዮጵያ
ሰራዊት
ላይ
መጠቀማቸውን
እንዲህ
ሲሉ
ይገልፃሉ፡
“…ያንለታ
የተጣለው
ቦምብ
ዳባት
ሜዳ
ከተጣለው
የተለየ
በጣም
ትልልቅ
ነበር።
ስለዚህ
ካይሮፕላን
አካላት
አንዳንድ
ክፍል
እየተሰበረ
የወደቀ
መስሎት
ብዙ
ሰው
ወደዚያ
‘ያይሮፕላን
ስባሪ’
ወደተባለው
ነገር
እየሮጠ
እየሄደ
ከብቦ
ሲመለከት
ቆየ።
በኒያ
ያይሮፕላን
ስባሪ
መስለውት
ሰው
ተሰብስቦ
በሚመለከታቸው
ነገሮች
አካባቢ
አየሩ
እንደ
ሰናፍጭ
በሚከነክን
ትናኝ
ተበክሎ
እዚያ
የተሰበሰቡትን
ሰዎች
ሁሉ
አይናቸውን እየለበለበ
ወዲያው
ያስላቸውና
ያስነጥሳቸው
ጀመር።
የዛፎቹ
ቅርንጫፍ
ቅጠሎችና
ሳሩም
ሁሉ
የዘይት
ጠባይ
ያለው
ፈሳሽ
አቁሮ
ስለነበረ፤
ያ
ፈሳሽ
እየተንጠባጠበ
ራቁት
አካላታቸውን
የነካቸው
ሁሉ
የተነካው
አካላታቸው
እሳት
እንደፈጀው
መጉረብረብና
ማበጥ
ጀመረ።
ከዚያ
የ
ግሪኩ
ሀኪም
አይተው
ያንለት የተጣለው ‘ማስታርድ ጋዝ የተባለው የመርዝ
ጋዝ ስለሆነ
ሰውም
ከብትም
ካጠገቡ
እንዲርቅ
ካስታወቁ
በ
ሁዋላ
ይህ
በየሰፈሩ
ተለፈፈ”
በ መጨረሻ ሐዲስ ከ ልዑል ራስ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ ጋር በ ምዕራብ ኢትዮጵያ በ አርበኝነት ሲዋጉ በ ጣሊያኖች እጅ በመያዛቸው በ ግዞት ለሰባት ዓመታት በፖንዞ ደሴትና በሊፓሪ ደሴት ታስረው ቆይተዋል። ከ ዚያም የተባባሪ ኃያላት ወታደሮች በ1935 ዓ.ም. ሲያስመልጧቸው በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና በ ኦክስፎርድ ከገፉ በኋላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል። ካገለገሉባቸው የኃላፊነት መስሪያ ቤቶች መካከል፡
v 1952
- የትምህርት ሚኒስትር
ከዚኅ ጎን ለጎን ሐዲስ ዓለማየሁ በርካታ የስነጽሑፍ ሥራዋችን አበርክተዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቅ አድናቆትንና እውቅናን ያተረፈው ሥራቸው ፍቅር እስከ መቃብር አንዱ ነው፡፡
v «የአበሻና የወደኋላ ጋብቻ
v ተረት ተረት የመሠረት
v ወንጀለኛ ዳኛ
v የልም ዣትና
v ትዝታ ሌሎች የ ሐዲስ የ አዕምሮ ጭማቂዎች ናቸው፡፡
መታሰቢያ
v በ ስማቸው በ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ተቋም ተመስርቷል፡፡
v ሚያዚያ 28፣
2009 ዓ.ም የ ነሃስ የ መታሰቢያ ሐውልት በ ደብረ ማርቆስ ከተማ ቆሞላቸዋል፡፡
በዚሁም ‹‹ኋለኞችን መዘከር ለ ፊተኞች
ጉልበት ስለሆነ›› ደስ ብሎናል፣ ይበልም ብለናል!
ሻሎም!
(ክብር ለ ኢትዮጵያ አርበኞች!)
© 2009 ዓ.ም
Thanks Dear!
ReplyDelete