The current Ethiopian Prime minster and EPDRF Leader, Hailemariam
Desalegn resigned from his position
የኢትዮጵያ መራሒ መንግስት ክቡር ሐይለማርያም ደሳለኝ ‹‹በሰለጠነ መንገድ›› መልቀቂያ አቅርበዋል-እሳቸው
እንዳሉት፡፡ የእራሳቸውንም መልቀቅ አሁን ላለው የኢትዮጵያ ሁኔታ የመፍትሄ አካል አድርገው አቅርበዋል፡፡ እሳቸው እንዳሉት በታሪክ
ስልጣኑን በፈቃዱ የለቀቀ ሰው ተብዬ እታወሳለሁ ብለዋል፡፡ ነገር ግን ትልቁ የህዝቡ ጥያቄ ከስርዓቱ ወይስ ከሐይለማርያም? የሐይለማርያም
መልቀቅ አንድ እርምጃ ወደፊት ያስኬዳል ወይ?
ነገሮች መልካቸውን እየቀየሩ ሄዱ፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል ሀገር ታሳዝናለች፡፡ ይች ሀገር የምታሳዝነኝ
ግን ‹‹መንቀል እንጂ ማብቀል›› የሚችል ማህበረሰብ መፍጠር አለመቻላችን ነው፡፡ ሁሉም ሰው ‹‹ወደ ገደል መጎተቱ ላይ እንጂ››፣
ጎን ለጎን ‹‹ወደ ተራራው የሚወጡትን›› የመግፋት ነገር ላይ ሲሰራ አይታይም፡፡ ዛሬ እየፈረሰ መሆኑን ከተረዳን ነገን መስራት ላይ ማሰብና መዘጋጀት ያስልጋል፡፡
No comments:
Post a Comment