የጠቅላዮች ምረጡኝ ቅስቀሳ (ምረጧቸው ቅስቀሳ) ተጧጡፏል፡፡ የ<ለማ>ንና
የ <ዶ/ር አብይ>ን 'ሲንግል' ዘፈኖች አደመጥሁ፡፡ ዘፈኖቹ ‹‹ሃሳብ አለው ለማ›› እና ‹‹አብይ ዜማ›› ይሰኛሉ፡፡
የ<ደመቀ> እና የ <ሲራጅ> ይቀረኛል፡፡ ያደመጣችሁ
ጀባ በሉኝ፡፡ ዘፈን ለመስራት ያሰባችሁ ደግሞ ግጥሙን ከአዝማሪ፥ ዜማውን ከህዝብ አጣምሩና በቶሎ በሉ፡፡ በእርግጥ ደህዴንና ህዋሃት
ያየር ሰዓቱን በዝረራ ያስረከቡ ይመስላል፡፡ እንቅስቃሴው ደከም ያለ ነው፡፡
አጋር ድርጅቶች ደግሞ እስከ ብብት እንጂ ጭንቅላት ድረስ መውጣት አልተፈቀደላቸውም፡፡
ጠ/ሚንስትር መሆን የሚፈልግ ባለምጡቅ ጭንቅላት ሶማሊያዊ፥ አዳል ወይም ጋምቤላዊ መጀመሪያ የዘር ካርዱን ከትግሬ፥ ከኦሮሞ ወይም
ከአማራ የደም ማህተም ማስመታት ይኖርበታል፡፡ ይች ናት እንግዲ-የብሔር እኩልነት የነገሰባት ሀገር!
ጭንቅላት ብቻውን ጭንቀት ከመፍጠር ያለፈ ዋጋ የለውም፡፡
<<የሀገሬ ዳቦና፣ የዘር ፖተሊካ
ለአንዳንዱ ባካፋ፣ ለአንዳንዱ በሹካ>> አይነት ነገር ነው፡፡ ለማንኛውም፥ ኢህአዲግዬ የመጨረሻውን ጥይት ለመተኮስ የተዘጋጀ ይመስለኛል፡፡
ዶ/ር አብይ አህመድን!
ቀሪውን፥ ቀሪው ቀን ያውቃል!!!
No comments:
Post a Comment