Wednesday, September 12, 2018

ሀሳብና ሰብዕና ቢለያዩስ?


/ መስፍን ወልደማሪያም ለኢትዮጵያ ውለታ ከዋሉ አንጋፋ ምሁራን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ ከአፄው እስከ አሁኑ ስርዓት ድረስ የታሪክ ማጣቀሻ ሆነው በህይወት ካሉ ምሁራን ውስጥ አንዱ እኒህ ጎምቱ የታሪክ ምሁር ናቸው፡፡ 1960ዎች ኢትዮጵያ በረሃብ አለንጋ ስትገረፍ ከፕ/ ጌታቸው ኃይሌ እና መሰል የወገን ተቆርቋሪዎች ጋር በመሆን ታላቅ ውለታ ውለዋል፡፡ እኒህ ምሁር ‹‹አማራ የሚባል ብሔር/ ነገድ የለም›› በሚል አቋማቸው አማራ ነህ ተብሎ እንደ ኑግ በየቦታው እየተሰለቀ በነበረው ወጣት ዘንድ ትልቅ ተቃውሞ ሲሰነዘርባቸው እንደቆዬ ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡ የአሁኑ ዘመን ትውልድ ከእሳቸው አቋም ጋር መስማማት ቢሳነው በማንም መፍረድ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም በእሳቸው ትርክት እና በእኛ ትርክት መካከል ትልቅ የታሪክ መጋረጃ አለ፡፡ የታሪክ መጋረጃው ደግሞ ሰው በሰውነቱ ሳይሆን የደምና የአጥንቱን መሰረት ተከትሎ በዘውጌ ፖለቲካ እንዲተሳሰር ተደርጎ የተዘጋጀ መጥፎ መጋረጃ ነው፡፡ / መስፍን በሀሳባቸው ልክ ሆኑም አልሆኑም፣ ሰብዕናቸው መከበር አለበት፡፡ 

‹‹ማንነት›› በግለሰቦች ችሮታ ተዘግኖ የሚሰጥ፣ በአምባገነኖች ጉልበት ተነጥቆ የሚወሰድ ንዋይ አይደለም፡፡ ‹‹ማንነት›› አንድ ሰው ወይም ማህበረሰብ እራሱን የሚገልፅበት መገለጫ ነው፡፡ ‹‹አማራ ማንነትም›› ከዚህ የተለዬ አይደለም፡፡ ‹‹እኔ አማራ ነኝ›› ብሎ የሚያምን ሰው የሚያፀናው እውነት እንጂ፣ ባለታሪክ ወይም ፖለቲከኛ የሚሰጠው ዳረጎት አይደለም፡፡ በእርግጥ የታሪክ ማጣቀሻዎች፣ ባህላዊ ዳራዎች እና መሰል ሁነቶች ማንነትን በፅኑ አለት ላይ ለመመስረት ወሳኝ መሆናቸው ሳይገባኝ ቀርቶ አይደለም፡፡ 
/ሩም ለዘመናት የደከሙት መሰል ሀቆችን እየጠቀሱ ነው፡፡ ነገር ግን እሳቸው እንደሚሉት ‹‹የታሪክ ትርክት ላለመክሸፉ›› ጠንካራ ማሳያ የለንም፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ታሪክ በምዕራባውያን እጂ ለሴራ የተፃፈ ነው፡፡ 100 ዓመታት ወደዚህ በእኛው ሰዎች የተጻፉ ታሪኮች ደግሞ ከተወሰኑት በቀር አድርባይነት ያመዘነባቸው ናቸው፡፡ / መስፍን በእራሳቸው ሃቅና ቁመና ልክ ናቸው፡፡ በዚህ አቋማቸው ምክንያት ግን ትውልድ የሰሩትን መልካም ተግባር ሁሉ በአመድ ሊለውሰው አይገባም፡፡ ሁላችንም በሃሳብ ሞግተናቸዋል፡፡ ሰብዓናቸው ላይ መረማመድ ግን ግብረገባዊነትም አይደለም፡፡ ለወጣቶች ከፍ ሲል ቅድመ አያት፣ ዝቅ ሲል ደግሞ አያት የሚሆኑ አዛውንት ናቸው፡፡ በተለይ በዚህ ጤናቸው በታወከበት ሰዓት ላይ -ሰብዓዊና -ሞራላዊ አነጋገሮችን እና ስድቦችን መሰንዘር ከእርግማን ለመቋደስ ካልሆነ በቀር የሚያተርፈው ቢስታቢስቲ ነገር የለም፡፡
ሀሳብና ሰብዕና ቢለያዩስ???
ፈጣሪ በምህረት እንዲጎበኛቸው እመኛለሁ!

No comments:

Post a Comment