Saturday, May 18, 2019

ፓስተር፣ወታደርና ዶክተር

ሙጋቤ በአንድ ወቅት እንዲህ አሉ አሉ፡፡ 
ባይሉም እኔአልሁ፡፡ሃቁ ደረቅ ሃቅ ስለሆነ፡፡ የአፍሪካን ተማሪዎች በአራት ካታጎሪ ከፈሏቸው፡፡ ምን ብለው?
1)የአፍሪካ በጣም ጎበዝ ተማሪዎች ሕክምናና ምህንድስና ያጠናሉ፡፡ ሲመረቁም ህዝብ ያክማሉ፣ ሀገርና ከተማ ይገነባሉ፡፡
2)ደከም ያሉት ደግሞ ማህበራዊ ሳይንስ ያጠኑና የፖለቲካዊን መንበር ተቆጣጥረው የህክምና ባለሙያዎችንና መሃንዲሶችን ይመራሉ፡፡ 
3)ውጤት አልሳካ ብሏቸው ኮሌጅ ያልገቡት ደግሞ ፖሊስና መከላከያ ይሆኑና የፖለቲካውን መንበር የተቆጣጠሩ የማህበራዊ ሳይንስ ምሩቃንን አዙረው ይመራሉ፡፡ ሲነሽጣቸው አፈሙዝ አዙረው መንበሩ ላይ ይሰየማሉ፡፡ 
4)ትምህርት አልገባ ብሏቸው፣ ከትምህርት ቤት የተሰናበቱ ተማሪዎች ደግሞ ‹‹ፓስተር›› ይሆኑና የሕክምናውን ስራ ገድል ይከቱታል›› ብለዋል አሉ፡፡ ሐሳዊ ጋዜጠኞችንና አርቲስቶችን ከየት እንደመደቧቸው ግን አልተናገሩም፡፡ ነፍጥ አልያዙም እንጂ መደባቸው ከሶስተኛው ዲቢዚዎን አይዘልም፡፡

Tuesday, April 2, 2019

ዶ/ር አብይ አህመድ-ቲሸርት አልባው መሪ

እንደምንድን አላችሁ፡፡ አለበለዚያስ እንዴት ናችሁ፡፡ ሰሞኑን ነገሩ ሁሉ የጅብ እርሻ ሲሆንብኝ ከራሴ ጋር ለአንድ ሳምንት ሱባኤ ገባሁ፡፡ ከፌስቡክ ጡሉላትም ጦምሁ፡፡ ሱባኤ ገብቼ አንድ ሀሳብ ይጄ መጣሁ፡፡ ‹‹አንድ ጉዳይ-በአንድ ፀሐይ›› የሚል! የሀገሬ ባለሃገር ‹‹ይችንማ በአንድ ፀሐይ እጨርሳታለሁ፣ ቢያቅተኝ እንኳን እስከ ፀሐይ ግባት አፈፅማታለሁ›› ከሚለው የተወሰደ ነው፡፡ ነገሮቹን በየደቂቃው መስቀል ማውረዱ፣ መለጠፍ ማጋራቱ ብዙ የሚያስቀጥለን አልመሰለኝም፡፡ የእስክንድርን ቃል ልዋስና ‹‹መከራችን ገና አላለቀም››፡፡ ላላለቀ መከራ ደግሞ ጅብ ተከትሎ መጮህ ብቻ መፍትሔ አይሆንም፡፡ ነገ ላለመጮህ ሰከን ብሎ በነገሮች ላይ አድምቶ መወያየት፣ መረጃ መለዋወጥ፣ ነገን ማደራጀት፣ አዳዲስ ሃሳቦች ማፍለቅ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በኋላ ሀሳቤን ከሚጋሩ የተወሰኑ የፌስቡክ ወንድምና አህቶቼ ጋር በሰከነ መልክ በአንድ ቀን አንድ ጉዳይ ላይ የሰከነ ውይይት አደርጋለሁ፡፡ ያለኝን አካፍላለሁ፡፡ ከብዙዎች ብዙ እማራለሁ፡፡ መረጃዎችን አሰባስባለሁ፡፡ በጨዋ ወግ እንድንወያይ አለምናለሁ፡

ዛሬ ያነሳሁት ርዕሰ ጉዳይ ‹‹ ከመጋቢት-እስከ-መጋቢት›› እንዲሉ የዶ/ር አብይ የአንድ አመት የስልጣን ጊዜ ላይ እንወያያለን፡፡
‹‹ዶ/ር አብይ አህመድ-ቲሸርት አልባው መሪ›› በሚል ርዕስ መነሻነት የሆነ ነገር ልበል፡፡ አይዟችሁ የዶ/ር አብይን ውስጥ እንጂ አለባበስ ለማየት አልሞክርም፡፡ በወንጌል ‹‹ እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል…›› የሚለውን ቃል ስለማውቅ እራሴን ለሸንጎ ዱላና ገጀራ ላለመጋበዝ ሰውን በአለባበሱ አልተችም፡፡

Thursday, January 3, 2019

‹‹የእኛ አውቶብስ››

ህዝቤ ሆይ ‹‹አውቶብስ ቲኬት ጠፋ፣ ወዲዚያ ወደዚ በምን ልሂድ ብለህ እንዳትጨነቅ! በፍፁም››፡፡ ‹‹የእኛ አውቶብስ›› በአራቱም አቅጣጫ ይዘልቃል፡፡ ምቾቱስ ቢሉ ‹‹እርቡላ›› ያስንቃል፡፡ ጊዜው ‹‹የእኛ ነው›› በማን? በእኛ ልጆች! ሐሙስ በረራ ይጀምራልማለቴ ጉዞ ይጀምራል፡፡ እንዴውም የገና በዓል ጉዞዎን ‹‹በእኛ አውቶብስ›› ይጀምሩ
ትኬቱ የት ይገኛል? እርስዎ እጂ ላይሃሎ ይበሉ፡፡ እንዴ ብቻ ቁጥሩን ካዩት ከጭንቅላትዎ ይጣበቃል፡፡0907-606060
0908-606060
0907-909090
0908-909090
በአካል መቁረጥ ለምትፈልጉ
1)የሃ ሲቲ ሴንተር (ስታዲዮም)
2)
ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲን-ፊትለፊት ያሉ ሱቆች
3)
ልደታ ኮንደሚኒየም-ተንዚት አሉሚኒየም ህንጻ
በኢንተርኔት የሚቆርጡበትንና በባንክ የሚከፍሉበትን ዘዴ እንቀይሳለን፡፡ እርስዎ ብቻ ‹‹ከእኛ›› ጋር ይሁኑ!
‹‹
የእኛ አውቶብስ››