Saturday, May 18, 2019

ፓስተር፣ወታደርና ዶክተር

ሙጋቤ በአንድ ወቅት እንዲህ አሉ አሉ፡፡ 
ባይሉም እኔአልሁ፡፡ሃቁ ደረቅ ሃቅ ስለሆነ፡፡ የአፍሪካን ተማሪዎች በአራት ካታጎሪ ከፈሏቸው፡፡ ምን ብለው?
1)የአፍሪካ በጣም ጎበዝ ተማሪዎች ሕክምናና ምህንድስና ያጠናሉ፡፡ ሲመረቁም ህዝብ ያክማሉ፣ ሀገርና ከተማ ይገነባሉ፡፡
2)ደከም ያሉት ደግሞ ማህበራዊ ሳይንስ ያጠኑና የፖለቲካዊን መንበር ተቆጣጥረው የህክምና ባለሙያዎችንና መሃንዲሶችን ይመራሉ፡፡ 
3)ውጤት አልሳካ ብሏቸው ኮሌጅ ያልገቡት ደግሞ ፖሊስና መከላከያ ይሆኑና የፖለቲካውን መንበር የተቆጣጠሩ የማህበራዊ ሳይንስ ምሩቃንን አዙረው ይመራሉ፡፡ ሲነሽጣቸው አፈሙዝ አዙረው መንበሩ ላይ ይሰየማሉ፡፡ 
4)ትምህርት አልገባ ብሏቸው፣ ከትምህርት ቤት የተሰናበቱ ተማሪዎች ደግሞ ‹‹ፓስተር›› ይሆኑና የሕክምናውን ስራ ገድል ይከቱታል›› ብለዋል አሉ፡፡ ሐሳዊ ጋዜጠኞችንና አርቲስቶችን ከየት እንደመደቧቸው ግን አልተናገሩም፡፡ ነፍጥ አልያዙም እንጂ መደባቸው ከሶስተኛው ዲቢዚዎን አይዘልም፡፡

ባይሉስ ስህተት የሆነው የቱ ነው፡፡ የጉብዝና መለኪያው ፊዚክስና ሒሳብ ነው ብለን አምነን 100 በማምጣታችን የተኩራራን ጊዜ ተሸውደናል፡፡ አፍሪካ በግምት እንጂ በስሌት የመመራት ሞራል የላትም፡፡ በምላስ እንጂ በሳይንስ የመጓዝ ህልም የላትም፡፡ ስለዚህ የስሌት ትምህርት አፍሪካ ውስጥ ዋጋ እንደሌለው ብዙ ሰው የሚገባው በሞቱ ዋዜማ ነው፡፡ ሞትህም ቅርብ ነውእንዴት? ወይ በሳይንስ (ሎጅክ) ስትከራከር የአፈሙዝ እራት ትሆናለህ፣ አሊያም ያጠናኸው ሳይንስ አጪሶ ይገልሃል፡፡ ለምን? አዋዋልህ ለሞት ስንዝር የራቀ ስለሆነ፡፡ ውሎህ ሞት ከሚተነፍስ በሽተኛ ጎን፣ እድሜህን ከሚያሳጥር ኬሚካል መሃል፣ ጭንቅላት ከሚበሳ ብሎኬት ስር፣ እንደ እንጨት ከሚያደርቅ ኤሌክትሪክ ፊት ነው፡፡ ሶፋ ወንበር ላይ ተጎማሎ ከተቀመጠ ሰው ጋር እኩል የመኖር ተስፋ የለህም፡፡ ተስፋህ ህልምህን ሆነህ መሞት ነው፡፡

በእርግጥ ሀገሬ በስሌት ትመራ ነበር-ድሮ ድሮ፡፡ አሁን ግን ‹‹ሴራ፣ ግምት እና ስሜት›› ቦታውን ከተረከቡ ግማሽ ምዕተ ዓመት አስቆጥረዋል፡፡ የወደፊት ጎበዝ ተማሪዎች ወደ ማህበራዊ ሳይንስ እንዲገቡ ማድረግ ትርፉ ብዙ ነው፡፡ ወደ መከላከያም እንዲሁ!

ሀገሬ አንድ ተስፋ፣ አንድ ስጋት ያላት ይመስለኛል፡፡ ስለ ቀደመው ታሪኳና በዘመን ስላልከሰመው መልኳ ብሎ እሱ የፈጠራት፣ በህያዋን ፀሎት እርዳታ ይታደጋታል፡፡ ወይም ላይ ላዩን ሲያዩት ‹‹ትንቢት›› በሚመስለው፣ በደንብ ሲያጤኑት ግን ‹‹ትዕቢት›› በሚመስለው የሀሳዊ/የመሳያዊ መሪዎች፣ ወታደሮችና ፓስተሮች ምላስና እጂ ትጠፋለች፡፡
‹‹ኢትአርየነ ሙስና ለኢትዮጵያ›› ብሎ መፀለይ ይበጃል፡፡ ለምን ‹‹ያልተሰራ አእምሮ፣ የተሰራ ሀገር ከማፍረስ አይመለስምና››
(#ምስል ፖሊስና ወታደር የሚያስፈራራው ባለሙያ Vs ፖሊስና ወታደር ያጀበው ፓስተር)

No comments:

Post a Comment